2018-05-07 09:43:00

ጳጳሳት ምዕመኑን ግራ ከሚያጋቡዋቸው ሰዎች በሙሉ ሊታደጉዋቸው ይገባል።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሚያዝያ 25/2010 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት ጳጳሳት ምዕመኑን ግራ ከሚያጋቡዋቸው ሰዎች በሙሉ ሊታደጉዋቸው እንደ ሚገባ ጠቅሰው የአንድ ጳጳስ ተግባር ሊሆን የሚገባው እመነትን መጠበቅ እና ማጽናት እንደ ሆነ ገለጸው ቤተክርስቲያን መቼም ጊዜ ቢሆን የእረኞ ጠበቃ ሊለያት አይገባም ብለዋል።

እመነትን መጠበቅ እና እምነትን ማጽናት የሚሉት ሁለት ጭብጦች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በእለቱ በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙት ስብከት ዋነኛ ጭብጦች እንደ ሆኑ የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያደረጉት ስብከት መሰረቱን አድርጎ የነበረው በወቅቱ ከሐዋሪያት ሥራ ከምዕራፍ 15፡22-31 ላይ ተወስዶ በተነበበው እና በወቅቱ በአንጾኪያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተከስቶ በነበረው አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ትኩረቱን ያደርገ እንደ ነበረም ለመረዳት ተችሉዋል።

“ከእኛ መካከል አንዳንድ ሰዎች ሳናዛቸው ወደ እናንተ መጥተው በነገሩዋችሁ ቃል እንዳስቸግሩዋችሁና ግራ እንዳጋቡኣችሁ ሰምተናል” በማለት በወቅቱ የነበሩት የአንጾኪያ ክርስቲያኖች በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ውሳኔ ላይ በመድረስ  ለሐዋሪያው ጳውሎስ እና ለሐዋሪያው ጴጥሮስ ደብዳቤ ጽፈው እንደ ነበር በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህንን ያደርጉበት ምክንያት በቤተክርስቲያናቸው ውስጥ ሰላም ይሰፍን ዘንድ በማሰብ ያደርጉት ተግባር እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

የእዚህ ደብዳቤ ምላሽ ከአንጾኪያ በጳውሎስ እና በባርናባስ እዲሁም በሌሎች ታማኝ በነበሩ አማኞች አማክይነት ምላሽ ተሰጥቶ እንደ ነበረ በማስታወስ ስበከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በወቅቱ በአንጾኪያ የነበሩ ክርስቲያኖች ለጥያቄያቸው የተሰጣቸው ምላሽ በተነበበበት ወቅት እጅግ ደስ ብሎዋቸው እንደ ነበረ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው በተለይም በምላሹ ላይ የነበረው የማበረታቻ መልእክት አምኞችን በጣም አስደስቶዋቸው እንድ ነበረ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

“እውነትኛ የሆነ አንቀጸ-እምነት ወይም ዶክትሪን የያዙ በመምሰል” በሕዝቡ መኃል ገብተው ትክክለኛውን የክርስትና እመንት ነገረ መለኮት አስተምህሮን የያዙ በመምሰል ሕዝቡን ከሚያደናግሩ እና ግራ ከሚያጋቡ ሰዎች አማኞችን በመታደግ እምነትን ማጽናት የሚገባቸው የዛሬው ዘመን ደቀ-መዛሙርት እና ጳጳሳት ሊሆኑ እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

በእዚህም መሰረት ጳጳሳት “መቆጣጠር እና ነገሮችን በንቃት መከታተል እንደ ሚኖርባቸው” የገለጹት ቅዱስነታቸው አማኞችን ለመንጠቅ ከሚመጡ ተኩላዎች  ጳጳሳት መንጋዎቻቸውን መታደግ እና መጠበቅ ይኖርባቸዋል ብለዋል። የአንድ ጳጳስ ሕይወት ከምዕመኑ ሕይወት ጋር የተሳሰረ መሆን እንደ ሚገባው በመገልጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ጳጳሳት ከእዚህም ባሻገር በመሄድ መንጋዎቻቸውን በንቃት መጥበቅ እንደ ሚገባቸው ገለጸው ጳጳሳት የተሰጣቸውን ኃላፊነት እና ጥሪ በተመለከተ የሚከተለውን ብለዋል…

ነቅቶ መጥበቅ ማለት በመንጋው ሕይወት ውስጥ ተሳትፎ ማድረግ ማለት ነው፣ ኢየሱስ መልካም እረኛውን ከቅጥረኛው እረኛ በመለየት አስቀምጦልናል፣ ቅጥረኛ የሆነ እረኛ ተኩላ መጥቶ ከበጎቹ አንዱን ወስዶ ቢበላ ምንም ግድ አይሰጠውም፣ ብዙም አይጨነቅም። ነገር ግን እውነተኛ የሆነ እረኛ ግን ራሱን በመንጋው ሕይወት ውስጥ ተሳታፊ ስላደረገ ሁሉንም በጎች ብቻ ሳይሆን የሚታደጋቸው እያንዳንዱን በግ ያታደጋል፣ እያንዳንዱን በግ ይቆጣጠራል፣ ከመካከላቸው አንዱ እንኳን ቢጥፋ ሄዶ ፈልጎ መልሶ ያመጣዋል። የእርሱ ሕይወት በበጎቹ ሕይወት ውስጥ ጠልቆ በመግባቱ የተነሳ አንድ እንኳን እዲጠፋ አይፈልግም።

“ስለዚህ አንድ እውነተኛው ጳጳስ የእያንዳንዱን በግ ስም ለይቶ ያውቃል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ አንድ ለሕዝቡ ቅርብ የሆነ ጳጳስ ምን ዓይነት ጳጳሳ እንደ ሆነ ቁልጭ አድርጎ አሳይቶናል ያሉት ቅዱስነታቸው እናም መንፈስ ቅዱስ ለክርስቲያኖች ግልጽ በሆነ መልኩ አንድ እውነተኛ ጳጳስ የት እንደ ሚገኝ ለይተው የማወቅ ችሎታን ሰጥቱዋቸዋል ካሉ በኃላ ይህንን በተመለከተ ደግሞ የሚከተለውን ብለዋል . . .

“አይይይይይይይይ ይህ ጳጳሳ!!!” ሲባል ስንት ጊዜ ሰምታችኃል! ይህ ጳጳስ በጣም ጥሩ ጳጳስ ነው፣ ነገር ግን እኛን በደንብ እየተንከባከበን ግን አይደለም፣ ሁልጊዜም በጸሎት የተጠመደ ጳጳስ ነው ወይም ደግሞ ይህ ጳጳስ በሌሎች ሰዎች ሥራ ውስጥ ጣልቃ ይገባል . . . በሥራ የተጨናነቀ ይመስላል ይህ ደግሞ ጥሩ የሆነ ነገር አይደለም፣ ይህ ጳጳስ ደግሞ ከእርሱ ተልዕኮ ውጭ በሆኑ ነገሮች ላይ ተጠምዱዋል ወይም ደግሞ ይህ ጳጳስ ሁል ጊዜ በእጁ ቦርሳ አንጠልጥሎ በማያዝ ሁልጊዜ በጉዞ ላይ ነው፣ ሁሌም በሁሉም ስፍራ በዙረት ላይ ነው . . .በእርግጥ የእግዚኣብሔር ሕዝብ  እረኛው መቼ እረኛ እንደ ሆነ ያውቃል፣ እረኛው ለሕዝቡ ቅርብ ሲሆን እረኛው በጎቹን ነቅቶ መጠበቅ እንዳለብት ያውቃል፣ የገዛ ራሱን ሕይወት ለበጎቹ አስልፎ ይሰጣል። ምክንያቱም ለበጎቹ ቅርብ ስለሆነ ነው።

የአንድ ጳጳስ ሕይወት እና ሞቱም ሳይቀር በእዚሁ መልክ ሊሆን እንደ ሚገባው የገለጹት ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን ከማጠቃለላቸው በፊት የሚከተለውን ብለዋል . . .

ያለእነርሱ ወደ ፊት መረማድ ስለማይቻል ቤተክርስቲያን የመልካም እረኞች ጥበቃ እንዳይለያት መልካም የሆኑ እረኞችን ጌታ ይሰጠን ዘንድ ልንጸልይ ይገባል። እረኞች ሰራተኛ የሆኑ ሰዎች፣ የጸሎት ሰው፣ ለሕዝቡ ቅርብ የሆኑ፣ ለእግዚኣብሔር ሕዝብ ቅርብ የሆኑ በአጠቃላይ በአንድ ቃል ስናጠቅልለው ነቅተው መጠበቅ የሚችሉ ሰዎች እንዲሰጠን ወደ ጌታ ጸሎታችንን ማቅረብ ይገባናል።
All the contents on this site are copyrighted ©.