2018-04-21 10:08:00

“ከክርስቶስ በላይ የሆነ ነገር በሕይወታችሁ ውስጥ አይኑር”


የቅዱስ በነዴክቶስ መነኩሳት ማኅበር ከክርስቶስ ልደት በኃላ 480 ዓ.ም. በተወለደው ቅዱስ በነዴክቶስ ዘ ኖርቺያ የተመሰረተ ማኅበር እንደ ሆነ የሚታወቅ ሲሆን ከእዚያም ጊዜ በኃላ ባሉት አመታት ውስጥ በቅዱስ በኔደክቶስ ዘ ኖርቺያ ስም እና መነፈሳዊ ዓላም የተቋቋሙ በርካት ማኅበራት እንዳሉ ይታወቃል። በቅዱስ በነዴክቶስ ዘ ኖርቺያ ስም እና መንፈሳዊ ዓላማን በማንገብ በርካታ መንፈሳዊ መኅበራት በአንድ ቅዱስ ስም እና መነፈሳዊ ዓላማ በማንገብ በተለያዩ ጊዘያት የተቋቋሙ በመሆናቸው የተነሳ የዛሬ 125 አመት ገደማ ውህደት በመፍጠር የቅዱስ በነዴክቶስ መነኩሳት ማኅበር በሚል መጠሪያ ሕበረት መመስረታቸው ይታወቃል። ይህ ውህደት የተፈጠረበት 125ኛው አመት ኢዩቤሊዩ በሚያዝያ 11/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው የቅለሜንጦስ አዳራሽ ተከብሮ ማለፉ የተገለጸ ሲሆን በእዚህም መሰረት የበነዴክቶስ መነኩሳት ማኅበር አባላት እና ወዳጆቻቸው ዛሬ ረፋዱ ላይ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ጋር በቫቲካን መገናኘታቸው ታውቁዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸሶ የበኔዴክቶስ መንኩሳት ማኅበር ሕበረት የፈጠሩበትን 125ኛው ኢዩቤሊዩ በዓል በተከበረበት በዛሬው ቀን ለመነኩሳቱ እና ለወዳጆቻቸው አድርገውት የነበረውን ንግግር ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው እናቀርብላችኃለን። አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንናጋብዛለን።

የተከበሩ የአበምኒዬት የተከበራችሁ መነኩሳት የተከበራችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ!!

የበኔዲክታዊያን ገዳማዊያን ማኅበር ውህደት የፈጠሩት 125ኛውን አመት ኢዩቤሊዩ በዓል ለማክበር እዚህ በመገኘታችሁ እያመሰገንኩኝ በተጨማሪም የገዳሙ አበ ምንዬት እዚህ ተገኝተው ላደረጉልን ንግግር ከልብ ለማመስገን እወዳልሁ። የቅዱስ በነዲክቶስ ማኅበር ላለፉት 1500 ዓመታት (የቅዱስ በኔዲክቶስ መነኩሳት ማኅበር ከክርስቶስ ልደት በኃላ 480 .. በተወለደው ቅዱስ በነዴክቶስ ኖርቺያ የተመሰረተ ማኅበር እንደ ሆነ የሚታወቅ ሲሆን ከእዚያም ጊዜ በኃላ ባሉት አመታት ውስጥ በቅዱስ በኔደክቶስ ኖርቺያ ስም እና መነፈሳዊ ዓላማ የተቋቋሙ በርካት ማኅበራት እንዳሉ ያታወቃል እነዚህ በርካታ ማኅበራት በአንድ ቅዱስ ስም የሚጠሩ እና አንድ ወጥ የሆነ ዓላማ ያነገቡ በመሆናቸው የዛሬ 125 ዓመት ገደማ ውሕደት ፈጥረዋል) ያህል ለቤተ ክርስትያን ሕይወት ስላበረከቱት ጠቃሚ ድርሻ ያለኝን አጠቃላይ ምስጋና እና እውቅና ለመግለጽ እወዳለሁ። ይህ የበነዲክታዊያን የመነኩሳት መኅበር ውሕደት የፈጠሩበት 125ኛው ኢዮቤልዩ በሚከበርበት በአሁኑ ወቅት ለየት በላ አሁኔታ በወቅቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ልዮ 13 1893 .. ይህ ውሕደት እንዲፈጠር፣ አንድ የጋራ የሆነ የጸሎት ቤት እና የጋራ የነገረ መልኮት ትምህርት የሚሰጥበት ስፍራ እዚሁ በሮም እንዲመሰረት ላደርጉት ጥረት ከፍተኛ ምስጋና ልናቅርብላቸው የገባል። ይህ ውሕደት እንዲፈጠር ያነሳሳውን  እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፣ ምክንያቱም የመላው ዓለም የበኔዲክታዊያን መነኩሳት ማኅበር እርስ በእርሳቸው የጠለቀ የኅብረት መንፈስ እንዲኖራቸው እና ከቅዱስ ጴጥሮስ መንበር ጋር ሳይቀር ሕበረት እንዲፈጥሩ አድርጓዋቸዋል። የበነዴክታዊያን የመነኩሳት ማኅበር በላቲን ቋንቋOra et labora et lege” በአማሪኛው ጸሎት፣ ሥራ እና ትምህርት የሚሉትን ሦስት መንፈሳዊ እሴቶችን በዋነኛነት መርህ አድጎ የሚንቀሳቀስ ማሕበር ነው። ጸሎት፣ ሥራ እና ትምህርት። በአስተንትኖ ሕይወት ውስጥ ብዙን ጊዜ እግዚኣብሔር ባልተጠበቀ መንገድ እግዚኣብሔር በእዛ መኖሩን ይገልጻል። በስተንትኖ እና በእለታዊ ጸሎት አማክይነት የእግዚኣብሔር ቃል ማሰላሰላችን በቋሚነት እና በደስታ በመታዘዝ መነፈሳዊ የሆኑ ድምጾችን በመከተል እንድንኖር ተጠርተናል። በየዕለቱ ሥራዎቻችን ወደየ ገዳሞቻችሁ እግዚኣብሔርን በመፈለግ የሚመጡ ሰዎችን እና በየትምህርት ቤቶቻችሁ፣ በየኮሌጆቻችሁ እና በየዩኒቬርሲቲዎቻችሁ የሚማሩ ሰዎች የእግዚአብሔርን የጥበብ ስጦታዎች ለእነርሱ ለማካፈል እንዲረዳን፣ እግዚአብሔር ሁልጊዜ ሊሰጠን የተዘጋጀውን ድንቅ ስጦታዎች ለመቀበል ፈቃደኛ እንድንሆን ልባችንን ያነሳሳል። በዚህ መንገድ ሁሌም የታደሰ እና የተገነባ መንፈሳዊ ሕይወት ይፈጠራል። አሁን ባለበት እና እየኖርንበት በምንገኘው የፋሲካ በዓል ሰሞን ፈጣን ምላሾች እና የእግዚኣብሔርን ስጦታዎች ለመቀበል ዝግጁ እንድንሆን ልብ የሚነካ የበዓለ-ትንሣኤ በዓል ስነ-ስርዓት ውስጥ ያሉ አንዳንድ ባህሪያት በእርግጥ በየቀኑ የቤኔድክታዊያን መነኩሳት ማኅበር እለታዊ በሆነ መልኩ የሕይወታቸው አካል ነው። ቅዱስ በነዴክቶስ በሰጣችሁ ሕግ ውስጥከክርስቶስ በላይ የሆነ ነገር በሕይወታችሁ አይኑርየሚል ሕግ የሚገኝ ሲሆን ምክንያቱም ሁሌም ጠንቃቃ ሁናችሁ፣ ለማዳመጥ ዝግጁ እና በትህትና እርሱን ትከተሉ ዘንድ ለማሳሰብ በማሰብ የተናግረው ነው። ለስርዓተ አምልኮ ያላችሁ ፍቅር በመነኩሳን ሕይወት ውስጥ ያለ በጣም መስረታዊ እና አስፈላጊ የሆነ ነገር ሲሆን፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ ጌታ ሕይወ በሆነ መልኩ በእናንተ እንዲኖር የሚያደርግ በመሆኑ የተነሳ ለእናንተ በጣም አስፍላጊ የሆነ ነገር ሲሆን ለዘመናት በቤተክርስትያን ውስጥ ውድ በሆነ መልኩ ለብዙ መቶ ዓመታት እንደ ምንጭ ውሃ የሚያጠጣ እና ፍረያማ የሚያደርግ በመሆን፣ በግልና በማህበረሰብ ውስጥ ከሞት የተነሳው ጌታን ለመገናኘት አስችሉዋል።

ታላቁ ቅዱስ ግሪጎሮዮስ ቅዱስ በኔድክቶስን የምያበራ ኮኮበ በማለት ይጠርው እንደ ነበር የሚታወቅ ሲሆን ምክንያቱም በጊዜው የሥነ-ምግባር እሴቶች እና ተቋማት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ቀውስ ተከስቶ የነበረ ሲሆን ይህንንም ለመፍታት በመንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ በጣም አስፈላጊ እና ሁለተኝእ የሆኑ ነገሮችን መለየት የቻለበት ምክንያት ጌታን በጥብቅ በመከተሉ የተነሳ ነው። እናንተ የእርሱ ተከታይ የሆናችሁ ልጆቹ በእኛ ዘመን ከመንፈስ ቅዱስ የሚመጣውንና ከዓለም መንፈስ ወይም ከዲያቢሎስ መንፈስ የሚመጣውን ነገር ለይታችሁ ለማወቅ አስተዋይ መሆን ይኖርባችኃል። የማመዛዘን ችሎታ ምክንያትዊ የመሆን ችሎታን አይጥይቅም ነገር ግን ከመንፈስ ቅዱስ የሚገኝ ስጦታ ነው እንጂ። የማመዛዘን ችሎት የለለን ከሆንን ግን በጊዘው ባለው ሁኔታ እየተነዳን እንሄዳለን ማለት ነው። በዚህ ዘመን ሰዎች በጣም ሥራ ስለሚባዝብን  የእግዚአብሔርን ድምጽ ለመስማት በቂ ጊዜ የለኝም በሚሉበት በአሁኑ ወቅት፣ የእናንተ ገዳማት በበረሃ መካከል የሚገኝ አንድ በውሃ የተሞላ ሥፍራ ነው፣ የተለያየ የእድሜ ደረጃ ያላቸው፣ ከተለያዩ ባህሎች እና እምነቶች የተውጣጡ ሰዎች በእዛ የሚገኘውን ውብ የሆነ ጸጥታ እንዲያጣጥሙ እና ራሳቸውን እንዲያገኙ፣ ከፈጣሪ ጋር በመሆን ከእርሱ ጋር በመስማማት የተረጋጋ ሕይወት እንዲኖራቸው ይረዳቸዋል። እናንተ በኔዲክታዊያን ሰዎችን ለመቀበል ያላችሁ መነፈሳዊ ጥሪ አሁን ባለንበት ዓለማችን ውስጥ እየተደረገ ላለው ወንጌልን የማስፋፋት ሂደት በጣም ተቃሚ የሆነ ነገር ሲሆን፣ ይህም እያንዳንዱን ሰው አማካይነት ክርስቶስን ለመቀበል ለመቀበል የሚያስችላችሁ በመሆኑ እና ክርስትሶን በመፈለግ ላይ ለሚገኙ ሰዎች ክርስትሶ ለእያንዳንዳችን የሚሰጠንን መነፈሳዊ ስጦታ እንዲቀበሉ ስለምታስችሉ ነው በለዋል። የበነዲክታዊያን መነኩሳት ማኅበር ከሌለኦች ኃይማኖቶች ጋር ይደርጉ የአበሩ ውይይቶችን እና ድርድሮችን በተመለከተም ከፍተኛ አስተዋጾ አድርገዋል። በእዚህ በጀመራችሁት ጎዳና መጓዛችሁን በመቀጠል ለቤተ ክርስቲያናችሁ እና ለመላው ዓለም የነበራችሁን መልካም አቀባባል የማድረግ ባሕላችሁን በመቀጠል ይህንን አስተዋጾ ማድረጋችሁን መቀጠል ይኖርባችኃል። የበኔዲክታዊያን ማኅበር በከተማ ውስጥ ይሁን በገጠርማ ቦታ የእናንተ ገዳማት የጸሎት እና መልካም አቀባበል የሚደርግበት ሥፍራ ነው። የእናንተ መረጋጋት እናንተን ለማግኘት ለሚመጡ ሰዎች አስፈላጊ ጉዳይ ነው። በእዚህ ግንኙነት ውስጥ ክርስቶስ ይገኛል፣ ክርስቶስ በመነኩሴው ውስጥ የገኛል፣ ክርስቶስ በተቸገረ ሰው ውስጥ ይገኛል።

በሮም ከተማ ውስጥ በትምህርትና በሕነጻ ዘርፍ እያበረከታችሁት ለምትገኙት አገልግሎት እንዲሁም በመላው ዓለም እያደርጋችሁት ለምትገኙት አገልግሎት ከፍ ያለ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ።የበነዲክታዊያን መነኩሳት ማኅበርየጌታ ትምህርት ቤተበመባል ይታወቃሉ። ለተማሪዎቻችሁ፣ አስፈላጊውን እውቀት በመስጠት እና የእውቀት ማስተላለፊያ መሳሪያ በመሆን ተማሪዎቹ በሕይወታቸው እግዚአብሔርን ያለማቋረጥ እንዲፈልጉ የሚያነሳሳቸውን፣ በጥበብ እንዲበለጽጉ እና እንዲጎለብቱ ማድረግ እንደ ሚገባቹ እመክራችኃለሁ።

ወንድሞቼ እና እህቶቼ በመጨረሻም ውህደት የፈጠራችሁበት 125 አመት ኢዩቤሊዩ እግዚኣብሔርን እና የእርሱን ጥበብ እንዴት መፈለግ እንደ ሚገባ፣ የእርሱን ብርቅ የሆኑ እሴቶች ብቃት ባለው ሁኔታ ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ እንደ ሚገባችሁ እንድታሰላስሉ አጋጣሚ ይፈጥርላችኃል ቢዬ ተስፋ አደርጋለሁ። የቤተ ክርስትያን እናት በሆነችሁ በእመቤተች ቅድስት ድንግል ማሪያም አማላጅነት፣ ከሰማያዊቷ ቤተ ክርስቲያን ጋር በመተባበር እና ከቅዱስ በነዴክቶስ ጋር በመሆን በእያንዳዳችሁ ላይ ሐዋሪያዊ ብራኬዬ ይወርድላችሁ። እባካችሁን ለእኔ መጸልይ እዳታቋርጡ። አመስግናለሁ። 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.