2018-04-03 11:03:00

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ዘንድ የስቅለት ቀን በታላቅ መንፈሳዊነት ተከበረ


የጎርጎሮሳዊያኑ  የቀን ቆጣጠር በሚከተሉ ክርስቲያኖች ዘንድ አሁን ያለንበት ወቅት የሕማማት ሣምንት እንደ ሆነ ይታወቃል። በእዚህ የሕማማት ሳምንት ውስጥ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ስርዐተ አምልኮ ደንብ መሰረት እኛን ለማዳን እና ከእግዚኣብሔር ጋር እኛን ለማስታረቅ ራሱን መስዋዕት አድርጎ ያቀረበው ክርስቶስ ተላልፎ መሰጠቱን፣ መንገላታቱን፣ በመስቀል ላይ እንደ ሌባ መሰቀሉን፣ መሞቱን፣ መቀበሩን እና ከሙታን መነሳቱን እነዚህ ሁሉ ነገሮች የተከናወኑባቸው ሦስት ዋና ዋና ቀኖች በተለየ ሁኔታ በታላቅ መንፈሳዊነት ይከበራሉ። እነዚህም ሦስት ቀኖች የሚከተሉት ናቸው።

ኢየሱስ መከራውን ከመቀበሉ በፊት  ከደቀ-መዛሙርቱ ጋር የመጨረሻውን ራት ከመብላቱ በፊት የሐዋሪያቱን እግር ያጠበበት፣ እርሱ በምድር ላይ በነበረበት ወቅት የጀመረውን መንፈሳዊ ተልዕኮ እንድያስቀጥሉ በማሰብ ምስጢረ ክህነትን የመሰረተበት፣ የመጨረሻ ራት ከደቀ-መዛሙርቱ ጋር የተካፈለበት የጸሎተ ሐሙስ ምሽት በቀዳሚነት ይጠቀሳል።

በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞት የተፈረደበት፣ የተሰቃየበት፣ በመስቀል ላይ ተስቅሎ የሞተበት እና የተቀበረበት የስቅለተ ዐርብ እለት ይጠቀሳል። ይህም የስቅለተ ዓርብ እለት የላቲን ስርዓት አምልኮን በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በትላንትናው እለት በታላቅ መነፈሳዊነት፣ በጾም እና በጸሎት አክብረውት ማለፋቸው ታውቁዋል። ይህ እለት በሮም ከተማ እንብርት ላይ በሚገኘው እና በጥንት ጊዜ በነበረው የሮም ንጉሥ ክርስቲያኖች ላይ ከፍተኛ ግፍ የፈጸመበት፣ ክርስትያኖችን ከአንበሳ ጋር እንዲታገሉ ባደርገበት ኮሌሴዎ በመባል በሚታወቀው ስፍራ የመስቀል መንገድ ጸሎት ወይም ፍኖተ መስቀል ጸሎት በማድረግ ተከብሮ አልፉዋል። በትላንትናው ምሽት በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 4 ሰዓት 15 ላይ በእዚሁ ኮሌሴዎ በሚባል ሥፍራ በታካሄደው የመስቀል መንገድ ሥርዓት ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ተገኝተው የነበረ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ይህንንም ጸሎት በመሪነት አሳርገዋል። በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ስረዓት አምልኮ ደንብ መሰረት የመስቀል መንግድ ወይም የፍኖተ መስቀል ጸሎት 14 ማረፊያዎች ያሉት ጸሎት ነው። እነዚህም ማረፊያዎች የሚከተሉት ናቸው።

በትላንትናው እለት በእዚሁ በሮም ከተማ በሚገኘው ኮሌሴዎ በሚባልበት ስፍራ በሺዎች የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች በተገኙበት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መሪነት በተደረገው የመስቀል መንገድ ጸሎት ላይ የተደረገው አስተንትኖ በ15 ከ16-27 እድሜ ባላቸው ወጣት ተማሪዎች መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ወጣቶቹ ይህንን አስተንትኖ ያዘጋጁት ከሐይማኖት አስተማሪዎቻቸው እና ከነፍስ አስተማሪዎቻቸው ጋር በጋር በመሆን እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ይህንን ከመስቀል መንገድ ጸሎት ቀጥሎ ያለውን አስተንትኖ ወጣቶቹ እንዲያዘጋጁ የተደረገበትም ምክንያት በመጪው ጥቅምት ወር 2010 ዓ.ም. በወጣቶች ላይ ትኩረቱን ያደረገ፣ “እምነት፣ ወጣቶች እና በጥሪ ላይ በማስተዋል ጥበብ የተሞላ ውሳኔ ማድረግ በሚል መሪ ቃል ለሚካሄድው 15ኛው የካቶሊካዊያን ብጹኣን ጳጳሳት አጠቃላይ መደበኛ ሲኖዶስ ወጣቱን ትውልድ ያሳተፈ ቅድመ ዝግጅት በሚደርግበት በአሁን ወቅት እንደ ሆነም ተገልጿል። በዚህም መስረት እነዚህ 15 ወጣቶች ውስጥ  በአሁኑ ወቅት በእርስ በእርስ ጦርነት ከደቀቀችው ከሶሪያ እና  ከኢራቅ የተውጣጡ ክርስቲያኖች ይገኙባቸዋል።

በወቅቱ የቀረበው በወጣቶቹ የተዘጋጀው አስተንትኖ የተደርገው አራቱ ወንጌላዊያን ስለክርስቶስ መከራ እና ስቃይ እንዲሁም ተስቅሎ መሞቱን የሚተርከው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ከተነበበ በኃል ሲሆን ወጣቶቹ ካደርጉት አስተንትኖ በመቀጠል መስቀሉን ይዘው በዝማሬና በጸሎት በታላቅ መንፈሳዊነት ውደት እንዳደርጉም ተገልጹዋል።

በእዚህ የመሰቀል መንገድ ጸሎት ማብቂያ ስነ-ስረዓት ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ያደርጉትን የመደምደሚያ ጸሎት እንደ ሚከተለው እናቀርብላችኃለን።

ጌታ ኢየሱስ ሆይ አፍረት በተሞለበት መልኩ፣ በጸጸት እና በተስፋ ተሞልተን እይታችንን በአንተ መስቀል ላይ እናደርጋለን። ለእኛ ካሳየህን ከፍተኛ ፍቅር አንጻር ስንመለከት ለእኛ ኃጢኣት ብለህ ስትሰቃይ ዝም ብለን ማየታችን ያሳፍረናል፣ በሺዎች በሚቆጠሩ አጋጣሚዎች ውስጥ በተፈጠሩ ፈተናዎች ውስጥሌሎቹ አንተን ብቻህን ትተውህ ቢሄዱ እንኳን እኔ ግን በፍጹም ብቻህን አልተውህምየሚለውን ቃል በድፍረት ማለት ባለመቻላችን አፍረት ይሰማናል።

አንተን ሳይሆን በርባንን እንዲፈታ በመፈለጋችን፣ ስላንጣንን እንጂ አንተን ባለመፈለጋችን፣ ውጫዊ ገጽታችንን እንጂ አንተን ስላልመረጥን፣ገንዘብን እንደ እንጂ አንተን አምላክ አድርገን ባልመቁጠራችን፣ ዓለማዊነትን እንጂ የዘላዓለም ሕይወት ለመምረጥ ባለመቻላችን ከፍተኛ ሀፍረት ይሰማናል።

አንተን በአፋችን እናጂ በልባችን ውስጥ ባለማስገባታችን፣ ብዙን ጊዜ ፈተናዎች በሚያጋጥሙን ወቅቶች ሁሉእስቲ አንተ ነብይ ከሆን እራስህ አድን፣ ይህንን ካደረክ ብቻ ነው በአንተ የማምነውበማለታችን እፍረት ይሰማናል።

ዓለማችን አሁን ላለው የወጣቱ ትውልድ የተከፋፈለ እና በጦርነት የተጎሳቆለ፣ ወጣቶችን፣ ታናናሾችን ሕሙማንን፣ አረጋዊያንን ባገለለ መልኩ የራስ ወዳድነት መነፈስ የተሞላ ዓለም በመፍጠራችን ሀፍረት የሰማናል።

የማፈርን መንፈስ በማጣታችን የተነሳ እናፍራለን

ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቅዱስ የሆነ ሃፍረት ይሰማን ዘንድ ጸጋህን ስጠን!

የእኛ ዓይኖች አንተ በስቃይ ውስጥ በታላቅ ዝምታ የቆየህበትን ወቅት በጸጸት በመመልከት የአንተን መለኮታዊ ምሕረት ይማጸናል።

ይህም ጸጸት የመነጨው እኛን ከክፉ ነገሮች ሁሉ ልታድነን የሚችለው አነተ ብቻ እንደ ሆንክ እርግጠኛ በመሆናችን የተነሳ፣ ከጥላቻ፣ ከራስ ወዳድነት፣ ከትዕቢት፣ ከቅናት፣ ከክህደት፣ ከስግብግብነት፣ ከአመንዝራነት መልስህ እንደ ልጅ በማቀፍ አተነው የነበረውን የልጅነት መብት በድጋሚ በማጎናጸፍ እና ወደ አባታችን እና ወደ መልካም ሕይወት የምትመልሰን አነተ ብቻ እንደ ሆንክ እርግጠኞች በመሆናችን የተንሳ ነው።

እኛ ትንሽ መሆናችንን በመረዳታችን፣ ባዶ መሆናችን፣ የእኛ ሕይወት በአንተ በርኅራኄ በተሞለው ጥሪ ምክንያት ወደ ንስሐ የሚጠራን በመሆኑ ከእህዚ መንፈስ የመነጨ ጸጸት ትንሽ መሆናችንን እንድንረዳ አድርጎታል።

ምስቅልቅሉ ከወጣ ሕይውቱ ውስጥ በአንተ አማካይነት ጥንካሬን እና ብራታትን ካገኘው ዳዊት የነበረ ዓይነት ጸጸት ይሰማናል።

ከፍራሃት የመነጨ ጸጸት ይሰማናል፣ ልባችን በአነት እስኪያርፍ ድረስ እረፍት እንደሌለው እና የምልኣት እና የእርፍት  ሁሉ ምንጭ  እንተ እንደሆንክ ከሚሰማን እርግጠኛነት የመነጨ ጸጸት።

የአንተን ፊት በተመለከተ ጊዜ በስዎች ሁሉ ፊት አንተን በመካዱ የተነሳ ምርር ብሎ ካለቀሰው ሐዋሪያው ጴጥሮስ ታሪክ የመነጨ ጸጸት።

ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቅዱስ የሆነ ጸጸት ማድረግ እንችል ዘንድ ጸጋህን ስጠን!

ክቡራን እንናክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ይህ ቀደም ሲል ያስደመጥናችሁ ርዕስ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በመጋቢት 21/2010 ዓ.ም. ምሽት የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበርሰቦች ዘንድ በታላቅ መነፍሳዊነት በተከበረው የስቀለት ዐርብ ምሽት በተደረገው የመስቀል መነገድ ጸሎት ማብቂያ ላይ ያደርጉትን የማጠቃለያ ጸሎት ነበር።

 
All the contents on this site are copyrighted ©.