2018-03-27 11:33:00

በራሻ በሳይቤሪያ በደረሰው የእስት አደጋ ሐዘን እንደተስማቸው ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ገለጹ


ባለፈው እሁድ በመጋቢት 16/2010 ዓ.ም. በራሻ በሳይቤሪያ ክፍለ ሀገር በምትገኘው ኬመሮቮ በሚባል ሥፍራ በአንድ የንግድ መዕከል ላይ በደረሰ ድንገተኛ የእስት አደጋ ሕጻናት የሚበዙበት የ64 ሰዎች ሕይወት መቅጠፉ የሚታወቅ ሲሆን ይህንን የእሳት አደጋ ተከትሎ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በመጋቢት 17/2010 ዓ.ም. በቴለግራም ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ ምልእክት እንደ ገለጹት በእዚህ አደጋ ሕጻናት የሚበዙበት 64 ሰዎች በመሞታቸው የተሰማቸውን ከፍተኛ ሐዘን መገልጻቸው የታወቀ ሲሆን ይህንን አጋጣሚ ተጠቅመው ለሟች ቤተሰቦች ቡራኬያቸውን እና በአደጋው ወዳጆቻቸውን ላጡ ቤተሰቦች ደግሞ መጽናናትን ተመኝተዋል።

በእዚህ ድንገተኛ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡትን ሰዎች ነብስ በተለይም ደግም የጨቅላ ሕጻናቱን ነብስ ሁሉን ቻይ በሆነው በእግዚኣብሔር ምሕረታዊ እጅ ውስጥ ይገቡ ዘንድ ጸሎታቸው እንደ ሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው በእዚህ አደጋ ወዳጆቻቸውን ላጡ እና በለቅሶ ላይ ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ እግዚኣብሔር መጽናናቱን ይሰጣቸው ዘንድ በጸሎታቸው ከእነርሱ ጋር እንደ ሚሆኑ ቅዱነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.