2018-03-06 15:00:00

"ሃይማኖት እና እምነት እንደ አንድ "ትዕይንት" ዝም ተብሎ የሚታዩ ነገሮች አይደሉም"።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በየካቲት 26/2010 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት ቤተክርስቲያን የክርስቶስን አስተምህሮ በመከተል በእዚህ የዐብይ ጾም ወቅት መንፈሳዊ ለውጥ እንድናመጣ ትጠይቀናለች በለዋል።

የእዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ቅዱስነታቸው በእለቱ በቀዳሚነት ከመጀመሪያው መጽሐፈ ነገሥት 5:1-5 ተወስዶ በተነበበው በወቅቱ የሶሪያ ንጉሥ ጦር አዛዥ የነበረው ንዕማን ከለመጽ በሽታ መፈወሱን በሚገልጸው እና ከሉቃስ ወንጌል 4፡24-30 የተጠቀሰው “ኢየሱስ ነቢይ በገዛ ሀገሩ አይከበርም” በማለት በተናግረው የወንጌል ክፍል ላይ መስረቱን ባደረገ ስብከት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት ሃይማኖት እና እምነት ልክ እንደ አንድ "ትዕይንት" ዝም ተብሎ የሚታዩ ነገሮች እንዳልሆኑ ገለጸዋል።

በእዚህ አሁን ባለንበት የዐብይ ጾም ወቅት ቤተክርስቲያን የሐሳብ ለውጥ እንድናደርግ ትጠይቀናለች በማለት ስብከትቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ከሐሳብ ለውጥ ባሸገር በመሄድ በእዚህ ባለንበት የዐብይ ጾም ወቅት የተግባር እና የስሜት ለውጥ ማምጣት ይኖርብናል ብለዋል።

“ቤተክርስቲያን በእዚህ በዐብይ ጾም ወቅት መልካም ተግባራትን እንድናከናውን ያግዘን ዘንድ ጾም መጾም፣   መጽዋት መመጽወት እና ንስሐ መግባት አስፈላጊ እንደ ሆነ ትመክረናለች፣ እነዚህም ሦስት ተግባራት ደግሞ በጎ የሆኑ ምግባራትን እንድናከናውን ያነሳሱናል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በጎ የሚባሉ ተግባራትን በተመለከተ በማቴዎስ ወንጌል 25 የተጠቀሱትን የአንድ ክርስቲያን መገለጫ ባህሪይ የሆኑትን በጎ ምግብራት ማከናወን ይኖርብናል ብለዋል።

ቤተክርስቲያን በተጨማሪም በእዚህ የዐብይ ጾም ወቅት የስሜት ለውጥ እንድናደርግ ጥሪ እንደ ምታቀርብልን በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእዚህ በያዝነው የዐብይ ጾም ወቅት ስሜቶችንን ወደ መልካም ስሜት ልንቀየር ይገባል፣ የደጉ ሳምራዊ ምሳሌን በመከተል በርኅራኄ የተሞላ ስሜት ሊኖረን ይገባል፣ ስሜቶቻችን በሙሉ የክርስቲያን ስሜት መገለጫ ሊሆኑም ይገባል ብለዋል።

በእዚህ የዐብይ ጾም ወቅት መልካም ያልሆኑ ተግባሮቻችንን እና ክርስቲያናዊ ያልሆኑ ስሜቶቻችን መቀየር ብቻ ሳይሆን የሚጠበቅብን፣ ነገር ግን አሁን ባለንበት ዓለማችን የሐሳብ ለውጥ ማምጣት ያስፈልጋል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ምን ማስብ እንዳለብን ብቻ ሳይሆን እንዴት እንደምናስብ፣ ያስተሳሰብ ዘይቤያችንን ሳይቀር መቀየር አስፈላጊ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

የእኔ የአስተሳሰብ ሁኔታ እንደ አንድ ክርስቲያን ነው ወይስ እንደ አንድ አረማዊ ነው? ከእነዚህ ከሁለቱ በየተኛው ወገን ላይ የተመሰረተ አስተሳሰብ ነው ያለኝ? ብለን በእዚህ በዐብይ ጾም ራሳችንን እንድንጠይቅ ቤተክርስቲያን ጥሪ ታደርጋለች በለዋል።

በእለቱ ከመጀምሪያው የመጽሐፈ ነገሥት ላይ  ተወስዶ በተነበበው እና የሶሪያ ንጉሥ የጦር አዛዥ የነበረው ነዕማን ከያዘው የለምጽ በሽታ ለመፈወስ ፈልጎ የእግዚአብሔር ሰው ወደ ሆነው ወደ ኤልሳዕ በሄደበት ወቅት ኤልስሳዕ “ሂድና በዮርዳኖስ ወንዝ ሰባት ጊዜ ታጠብ፤ ሥጋህ ይፈወሳል፤ አንተም ትነጻለህ” ብሎ እንደ ነገረው  በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ንዕማን ግን ተቆጥቶ የደማስቆ ወንዞች ከየትኞቹም የእስራኤል ወንዞች አይሻሉምን? በማለት ወደ ሀገሩ ወደ ሶሪያ ሊመለስ ፈልጎ እንደ ነበረ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው በእዚህ ረገድ ንዕማን ትልቅ የሆነ ትዕይንት ጠብቆ እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው አስታውሰው እግዚኣብሔር የሚጠቀምበት የማዳን ዜዴ ወይም ሁኔታ ከእኛ የሐስተሳስብ ዜዴ እጅጉን የተለየ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

በተመሳሳይ መልኩም ልክ በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ እንደ ተጠቀሰው “ኢየሱስ ወደ ገሊላ ተመለሰ፤ ዝናውም በአካባቢው ባለው አገር ሁሉ ወጣ። እርሱም በምኵራባቸው ያስተምር ነበር፤ ሰውም ሁሉ ያመሰግነው ነበር፣ ነገር ግን ወደ ገዛ ሀገሩ ወደ ናዝሬት በተመለሰበት ወቅት የራሱ ወግኖች የሆኑ ወገኖቹ ግን “ይህ የአንጺው የዮሴፍ ልጅ አይደለምን? ታዲያ እርሱ ምን ልያትሰምረን ይችላል? በማለት እርስ በእርስ በማጉረምረም፣ ባሕሪያቸውም በመቀየር፣ በምኵራብ የነበሩ ሰዎች ሁሉ በቍጣ ገንፍለው፤  ሊገሉትም እንደ ፈለጉ” ያስታወሱት ቅዱስነታቸው በእዚህ ረገድ  እነዚህም የናዝሬት ሰዎች አንድ ትልቅ የሆነ ትይንት ማከናወን ፈልገው እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው አስታወሰዋል።

ነገር ግን ኢየሱስ ““እውነት እላችኋለሁ፤ ነቢይ በገዛ አገሩ አይከበርም” ብሎ መልሶላቸው እንደ ነበረ በስብከታቸው ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ምክንያቱም እኛ ብዙን ጊዜ በመካከላችን የሚኖር አንድ ሰው እኛን ለማበረታታት በሚነሳበት ወይም አንድ መልካም ነገር በሚናገርበት ወቅት ትልቅ ትይናትዊ ተግባራትን የማይፈጽም ከሆነ ልንሰማው አንፈልግም፣ ይህም ተግባር መልካም የሚባል ተግባር አይደለም ካሉ በኃላ እመንት እንደ አንድ ትይንት በፍጹም ቆጠር አይኖርበትም ምክንያቱም እምነት በትይንት የሚፈጸም ተግባር አይደለም እና በአንጻሩ እምነት በእግዚኣብሔር ቃል አማክይነት በመነፈስ ቅዱስ አነሳሽነት በልባችን ውስጥ የሚነቅሳቀስ ነገር ነው እንጅ ትይንት አይደለም ብለዋል።

በእዚህ ምክንያት ቤተክርስቲያን የአስተሳሰብ ዜይቤያችንን እንድንቀይር ጥሪ የምታድርግልን በእዚሁ ምክንያት ነው ያሉት ቅዱስነታቸው የቱንም ያህል የቤተክርስቲያንን አስተምህሮ የምንደግም ቢሆን እንኳን ነገር ግን ይህንን በክርስቲያንዊ መንፈስ ታግዘን ያማናደርግ ከሆነ ሁሉም ነገር ከንቱ ይሆናል ማለት ነው ብለዋል።

በእዚህ ባለንበት የዐብይ ጾም ወቅት የአስተሰሰብ ዘይቤያችንን በመቀየር፣ የእኔ አስተሰሰብ ምንጩ ምንድነው? በማለት ራሳችንን በመጠየቅ የአስተሳሰባችን ምንጭ ምን እንደ ሆነ ለይተን በማወቅ በእግዚኣብሔር መንፈስ እና በክርስቲያንዊ እሴቶች ላይ የተመሰረተ አስተሳስብ ይኑረን ወይም አይኑረን መርምረን በማወቅ መንፈሳዊ ለውጥ እንድናመጣ ይረዳን ዘንድ የእግዚኣብሔርን ጸጋ በመማጸን የአስተሰብ ለውጥ ለማምጣት ጸጋን የምንማጸንበት ወቅት ሊሆን ይገባል ካሉ በኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 
All the contents on this site are copyrighted ©.