2018-03-05 15:38:00

“የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት”


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር እሁድ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በእለቱ በሚነበበው ቅድስ ወንጌል ላይ ተመስርተው አስተንትኖ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። በእዚህ መሰረት በየካቲት 25/2010 ዓ.ም. በላቲን የስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት በሦስተኛ የዐብይ ጾም ሳምንት ሰንበት ላይ ከዩሐንስ ወንጌል 2፡13-25 ላይ ተወስዶ በተነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ በተጠቀሰው ኢየሱስ የገመድ ጅራፍ አበጅቶ በቤተመቅደስ ውስጥ ሲነግዱ የነበሩ ሰዎችን  ሁሉ ከቤተ መቅደሱ ግቢ እንዳባረረ በሚገለጽው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን ኢየሱስ “የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት” ብሎ በቤተመቅደስ ውስጥ ሲነግዱ የነበሩ ሰዎችን በሙሉ እንዳባረራቸው ቅዱስነታቸው በወቅቱ አስታውሰዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራቸስኮ በትላንትናው እለት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ አድርገው የነበረውን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል፣ አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የእዚን አስተንቶኖ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደ ምን አረፈዳችሁ!

ዛሬ በወንጌላዊው ዩሐንስ አማካይነት በቀረበልን የወንጌል ክፍል ውስጥ ኢየሱስ በቤተልሔም በቤተመቀድስ ውስጥ ሲነግዱ የነበሩ ሰዎችን አባር ስያስወጣቸው እንመለከታለን (ዩሐንስ 213-25) ይህንንም ያደረገውየገመድ ጅራፍ አበጅቶ በጎችንና ከብቶችን ሁሉ ከቤተ መቅደሱ ግቢ አባረረ፤ የመንዛሪዎችን ገንዘብ በተነ፤ ጠረጴዞቻቸውንም በመገለባበጥየአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት!” በማለት እንዳባረራቸው ይገልጽልናል። በፋሲካ በዓል አካባቢ የተፈጸመው ይህ ወሳኝ ድርጊት በሕዝቡ መካከል ከፍተኛ አድናቆት የተቸረው እና በሃይማኖት አለቆች ዘንድ ደግሞ የኢኮኖሚ፣ የገቢ ፍላጎቶቻቸውን አደጋ ላይ የሚጥል እና ሥጋት የሚፈጥርባቸው ሁኔታ ነበር። ታዲያ ይህንን ሁኔታ እንዴት ነው መተርጎም ያለብን? በእርግጠኛነት ኢየሱስ የተጠቀመው የኃይል እርምጃ አልነበረም ወይም ደግሞ እንደ አንድ ስርዓት አስከባሪ በሕዝባዊ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ የሚገባ እንደ የፓሊስ ኃይል ዓይነትም አልነበረም። አይ እንዲህም አልነበረም! አንድ ነቢይ እይተፈጸሙ የሚገኙትን መጥፎ ነገሮች በእግዚኣብሔር ሥም እንደ ሚያወግዝ ሁሉ ኢየሱስም ያደረገው ይህንኑ ተግባር ነበር። ዋናው ጥያቄ የነበረው የስልጣን ጥያቄ ነበር። አይሁድም፣ይህን ሁሉ ለማድረግ  ሥልጣን እንዳለህ የሚያረጋግጥ ምን ታምራዊ ምልክት ታሳየናለህ?” ብለው መጠየቃቸው የሚያሳየው ይሄንኑ ነው። ይህም ማለት ይህንን ተግባር ለመፈጸም የሚያስችልህ ሥልጣን ማን ነው የሰጠህ? የሚለው ነበር ጥይቄያቸው። እርሱ በእውነት የእግዚኣብሔር ልጅ መሆኑን ለማረጋረጥ የፈለጉም ይመስላል። ኢየሱስ በእግዚኣብሔር ቤት ውስጥ ሆነው ይነግዱ የነበሩትን አዎች አባሮ ማስወጣቱ የእርሱ ደቀ መዛሙርት፣ የተረዱት በመዝሙረ ዳዊት 69 “ለቤትህ ያለኝ ቅናት ያቃጥለኛልተብሎ በተጻፈው መሰረት ነው።

ይህ የመዝሙር ክፍል አንድ ሰው በጠላቶቹ ምክንያት ከፍተኛ የሆነ አደጋ ውስጥ በሚገባበት ወቅት እርዳታን የሚጠይቅበት የመዝሙር ክፍል ሲሆን፣ይህም ከቅርብ ጊዜያት በኃላ ኢየሱስ በመከራ ውስጥ በሚገባበት ወቅት የሚገጥመው ሁኔታ ዓይነት ነው። ለአባቱ እና ለአባቱ ቤት ያለው ቅንኣት ኢየሱስን እስከ መስቀል ላይ ሞት ያደረሰዋል፣ እርሱ የነበረው ቅንኣት እራሱን ለፍቅር ሲል አስላፎ እስከ መስጠት የሚያደርሰው ዓይነት ቅንኣት ነው እንጂ ልክ አንዳንዶቹ በእግዚኣብሔር ስም ሆነው እንደ ሚያነሱት ዓይነት ብጥብጥ ወይም ሁከት ዓይነት አይደለም። እንዲያውም ኢየሱስ የእርሱን ሥልጣን ለማሳየት በትክክል የሚሰጠው "ምልክት" የእርሱ ሞትና ትንሳኤ ይሆናል ኢየሱስምይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፤ እኔም በሦስት ቀን መልሼ አነሣዋለሁ  መቅደስ ሲል ግን፣ ስለ ገዛ ሰውነቱ መናገሩ ነበር (21)  ኢየሱስ ከፋሲካ በዓል በኃላ አዲስ ቤተመቀደስ መሆን ይጀምራል።

በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ዝንባሌ እኛም ብንሆን የራሳችንን ጥቅም ብቻ ለመስከበር እና ፍላጎቶቻችንን ለሟሟላት ብቻ ሳይሆን መኖር የሚገባን ነገር ግን የእግዚኣብሔር ክብር መገለጫ የሆነውን የፍቅር ሕይወት መኖር ይገባናል። እኛምየአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉትየሚለውን የኢየሱስን ጠንካራ ቃላቶች ዘወትር እንድንጠበቅ ጥሪ ያቀርብልናል። ቤተክርስቲያን በእዚህ ዓይነቱ ዝንባሌ ውስጥ ስትገባ እና የእግዚኣብሔርን ቤት የንግድ ቤት ስታደርገው በጣም የሚያጸይፍ ተግባር ነው።

እነዚህ ቃላቶች እኛንም ብሆን የእግዚኣብሔር ማደሪያ የሆነውን ነብሳችንን የሚፈታተኑዋትን መጥፎ ነገሮች እንድናስወግዳቸው፣ ነብሳችንን የገበያ መዐከል እንዳንደርጋት፣ በተቃራኒው ግን ቀጣይነት ባለው መልኩ የእግዚኣብሔርን ተጨበጭ የሆነ ፍቅር በዘላቂነት እንድንፈልግ ይስተምረናል። ይህ ኢየሱስ ዛሬ በወንጌሉ ያስተማረን አስተምህሮ አሁንም በእኛ ዘመን የሚታይ ነባራዊ ሁኔታ ሲሆን ይህም አስተምህሮ ለቤተክርስቲያን ማኅበር ብቻ የተተወ አስተምህሮ ሳይሆን ለእያንዳንዱ ግለሰብ የተሰጠ በአጠቅላይ ለሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል የተሰጠ አስተምህሮ ነው። እንዲያውም ሰዎች አንዳንድ ጊዜ መልካም የሆኑ ተግባራትን ለማከናዋን ሲነሳሱ፣ መልካም የሆኑ የግል ባህሪያቸውን ይበልጡኑ ለማዳበር በሚነሳሱበት ወቅት መፈተናቸው የተለመደ ተግባር ነው። ነገር ግን በጣም አደገኛ የሚሆነው ነገር የእግዚኣብሔርን ስም በመሳሪያነት በመጠቀም ወይም ደግሞ የሰው ልጆችን ምድራዊ ፍላጎቶች ለሟሟላት ብቻ በማሰብ የእግዚኣብሔርን ስም መጠቀም በጣም አደገኛ ነው። በእዚህ ዓይነቱ በጥፎ ተግባር ውስጥ በምንገባበት ወቅት ኢየሱስ በኃይል ከእዚህ ሊያጠፈን ከሚችለው አደገኛ ዝንባሌ ልያላቀቀን ይመጣል።

በእዚህ ባለንበት የዐብይ ጾም ወቅት መልካም የሆኑ ተግባራትን ብቻ በማከናወን፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የሕይወታችን ጌታ አድርገን ሁልጊዜ እንድንቀበል፣ በልባችን ውስጥ የሚገኙትን ማንኛቸውንም ክፉ የሆኑ ነገሮች በማስወገድ ለእርሱ የተገባ ልብ ይኖረን ዘንድ እምቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በአማላጅነቷ ትርዳን።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.