2018-03-01 12:09:00

ለእግዚኣብሔር ያለን ጣማት


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የበለይ የመስተዳድር አካላት እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ የሥራ ተባባሪዎች ጋር በጋራ በመሆን በየወቅቱ እንደ አስፈላጊነቱ ሱባሄ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል።

በእዚህም መሰረት ቅዱስነታቸው የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የበለይ የመስተዳድር አካላት እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቀርብ የሥራ ተባባሪዎች ጋር በጋራ በመሆን ከባለፈው እሁድ ምሽት ማለትም ከየካቲት 11/2010 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ የካቲት 16/2010 ዓ.ም. ድረስ የሚቆይ ሱባሄ ለማድረግ በሮም ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው አራቺያ በሚባል ስፍራ በሚገኘው “ ዲቪኒ ማዬስትሮ” በሚባል የሱባሄ ምስጫ ማዕከል በመገኘት ስቡባሄ እያደርጉ እንደ ሆነ ቀድም ሲል መግለጻችን ያትወሳል።

የእዚህ ሱባሄ መሪ የሆኑት በፖርቹጋል ዋና ከተማ በሌዝቦን የሚገኘው የካቶሊክ ዩንቬርሲቲ ምክትል ድይሬክተር የሆኑ፣ በነገረ መልኮት አስተምህሮ ጠበት የሆኑ፣ ገጣሚ እና ደረሲ አባ ጆዜ ቶሌንቲኖ በሚባሉ ካህን እንደ ሆነ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን እርሳቸው በእዚህ ሱባሄ ላይ ለተሳተፉት ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ እና የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የበለይ የመስተዳድር አካላት እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቀርብ የሥራ ተባባሪዎች ያደርጉትን ሦስተኛውን  አስተንትኖ እንደ ሚከተለው እናቀርብላችኃለን።

 

ጥማችንን እንዴት ነው በትግባር መተርጎም የምንችለው?

ጥማችንን ማዳመጥ ማለት በውስጣችን ያለውን ፍላጎታችንን መተርጎም ነው። እናም በዚህ መልኩ የዚህን ቃል ትርጉም በጥልቀት መመልከት በጣም አስፈላጊ ነው። ፍላጎት እና ምኞት በሚሉት ቃላት ውስጥ ከፍተኝእ የሆነ ልዩነት አለ። አሁን የምንገኝበት የካፒታሊዝም ማኅበረሰብ የተሻሉ መሰረታዊ ፍላጎቶችን በማራገብ የሰው ልጆችን የፍጆታ ፍላጎት ከፍ በማድረግ በተፍጥሮአዊ መነግድ ሰው ጥማቱን ማርካት በማይችልበት መልኩ ላይ ያተኮረ ፍላጎቶች እንዲጨምሩ ያደርጋል። የካፒታሊስት የንግድ ሕግን እና ስነ-ምግባር ገደብ እናድይኖረው በማድረግ ይህንንም የካፕታሊዝም ብያኔ በመጠቀም መቋጫ የሌለው እርካትን በመፍጠር ላይ ይገኛል። ነገር ግን ደስታን እና ፍቅርን የሚቃረን የሸማችነት ስሜትን በመፍጠር፣ በንብረቶችም ጥማት ስንወሰድ የስሜት መቃወስ ይገጥመናል፣ ሕይወታችንንም እናጣለን። በእዚህ የተነሳ በጣም ታላላቅ የሚባሉ ነገሮች ለእኛ እንደ ትንሽ ሆነው ይታዩናል፣ ይህም በባሕላችን፣ በማኅበረሳባችን፣ በየቤተክርስቲያናችን የሚግጥመን ስሜት ነው። በእዚህ ሁኔታ ከፍተኛ ፍላጎት ከሌላቸው ርዕሰ-ጉዳዮች በላይ በሆነ መልኩ ምኞቶቻችንን ብቻ የምንመለከት ከሆንን፣ ይህ ስሜታችን ደግሞ ወደ ቤተ-ክርስቲያን  ሊመራን ይገባል። እኛ ምስጢረ ጥምቀትን የተጠመቅን ሁላችን የምንመኘው ነገር ምንድነው? ክርስቲያኖች ያላቸው ሕልም ምንድነው? ኢዩሔል በትንቢቱ እንደ ሚለው ወንድ እና ሴት ልጆቻችን ትንቢት ይናገራሉ፣ አያቶቻችን አዳዲስ ሕልሞችን ያልማሉ፣ ወጣቶቻችንም አዳዲስ ራዕይ ያያሉ ይለናል።

ቤተክርስቲያን የፍትህ ርሃብ እና ጥማት አላት ወይ? ክርስቲያኖች “እኛ ግን ጽድቅ የሚኖርበትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር በተስፋ ቃሉ መሠረት እንጠባበቃለን” (2ኛ ጴጥሮስ 3፡13) የሚለውን ቃል ኪዳን ይጠባበቃሉ። እናም እኛ "በሁሉም ዘንድ የእግዚኣብሔርን የምሕረት ተግባር ለሁሉም ማድረስ" የሚለውን ሕልም እንዴት ነው በተግባር ላይ ማዋል የምንችለው። በቅርቡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት “Evangelii gaudium” በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም “በወንጌል የሚገኝ ደስታ” በሚል አርእስት በተጻፈው ቃለ ምዕዳን ውስጥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ እንደ ተቀሱት “ሁሁሉንም ነገር በመልካም ለመለወጥ የሚቻል የሚስዮን አልማለሁ፣ ምክንያቱም የቤተክርስቲያን ባህል፣ ቋንቋ፣ የአሰራር ዘይቤ፣ የጊዜ አጠቃቀም እና እያንዳንዱ መዋቅራዊ አሰራሩዋ አሁን ያለውን ነበራዊ ዓለም ለመለወጥ እና ወንጌልን ለማሰራጨት ትክክለኛ መንገድ ሊሆን ይገባል” EG 27 ማለታቸው ይታወሳል። ስለእዚህም ቤተክርስቲያን የሰው ልጆችን ጥማት ለማርካት በብርቱ መትጋት ይኖርባታል ማለት ነው።

ለእግዚኣብሔር ያለን ጣማት

“ዋላ የምንጭ ውሃ እንደምትናፍቅ” (መዝሙር 42) በማለት መዝሙረ ዳዊት በመግለጽ እኛ ለእግዚኣብሔር ያለንን ጣማት ምጻራዊ በሆነ መልኩ በመግለጽ በእዚህ በውሃ ጥም የተነሳ ተንከራቶ ይህንን የውሃ ጥሙን ለመቁረጥ እንደ ሚፈልግ ይናገረናል። ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ሮም ሰዎች በጻፈው መልእክቱ እንደ ገለጸው “ፍጥረት ሁሉ የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ በናፍቆት ይጠባበቃል” ይለናል (ወደ ሮም ሰዎች 8:19)። ይህንን በሚገባ የምንረዳው ከሆነ በጣም እውነት የሆነ ነገር ነው። ይህንን በትክክል ለመገንዘብ ከሞከርን የሰው ልጅ ለእግዚኣብሔር ያለውን ጣማት መመልከት እንችላለን። ይህ በመዝሙረ ዳዊት ውስጥ የተጠቀሰው የዋላ ጣማት ሁሉም ፍጥረታታ ያልቸው ጣማት ነው፣ ይህንን ቃል በሚገባ በፍቅር በተሞላ ስሜት የምናሰላስል ከሆን ሁላችንም እግዚኣብሔርን እንደ ተጠማን ለመረዳት እንችላለን። ምንም እንኳን በመዝሙረ ዳዊት ውስጥ ምጻራዊ በሆነ መልኩ “ዋላ የምንጭ ውሃ እንደምትናፍቅ” በማለት ምጻራዊ በሆነ መልኩ “ዋላ” የሚለውን ቃል በመጠቀም የሰው ልጆች ሁሉ ለእግዚኣብሔር ያላቸውን ጣማት ይገልጻል። ቅዱስ አጎስጢኖስ በበኩሉ እንዲህ ይላል “ወደ ምንጩ ሩጡ፣ ምንጩንም አነፍንፉ፣ ነገር ግን በዘፈቀደ አትሩጡ፣ እንደ ማንኛውም ዓይነት እንሳሳም አትሩጡ፣ እንደ ውላ ሩጡ. . .በዝግታ አትሩጡ. . .እንደ ዋላ ሩጡ ምክንያቱም ዋላ በጣም ፈጣን የሆነ እንስሳ ነውና” በማለት ቅዱስ አጎስጢኖስ ጥማችንን ለማርካት ወደ እግዚኣብሔር በፍጥነት መጓዝ እንዳለብን ይመክረናል። በጥንት ጊዜ የእግዚኣብሔርን ፊት መመልከት በወቅቱ ለነበሩ መነፈሳዊ ለሆኑ ሰዎች ብቻ የተተወ ነገር ነበር። በእዚህ በመዝሙረ ዳዊት ውስጥ  “ዋላ የምንጭ ውሃ እንደምትናፍቅ” ተብሎ በተጠቀሰው ቃል ላ በመመስረት ምናልባ በእዚህ ታሪክ ውስጥ ተዋናይ የነበሩት አንድ ካህን ወይም አንድ የአይሁድ የሕግ መምህር ሊሆኑ ይችላላኡ እነርሱ ወደ ምንጭ ውሃ የሚያደርጉትን ጉዞ ያሳያል፣ ይህም የምንጭ ውሃ የሕይወት ውሃ ነው ይህም የሕይወት ውሃ የሚገኘው በተቀደሰ ስፋር ብቻ ነው። በእዚህም መሰረት ነው እንግዲ ““ዋላ የምንጭ ውሃ እንደምትናፍቅ፣ አምላክ ሆይ፤ ነፍሴም እንዲሁ አንተን ትናፍቃለች// ነፍሴ አምላክን፣ ሕያው አምላክን ተጠማች፤ መቼ ደርሼ ነው የአምላክን ፊት የማየው? በማለት ጥያቄ ያነሳል። የቦታ ርቀት የጥማችንን ፋላጎት ያሻሽላል። ለእዚህም ነው እንግዲህ ዳዊት በበዝሙር እንደ ገለጸው መቼ ደርሼ በማለት የጠቀሰውም የቦታ ርቀት የጥማችንን ለማርካት ያለንን ፍላጎት ያሸሻል። ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በግሪክ የተጻፈውን ስንመለክት በግሪኩ psyche በአማሪኛው ሲተረጎም ነብስ በኢብራይስጥ ቁናቋ ደግሞ በደንብ ጠለቅ ብሎ በመግባት ነፍሽ ይለዋል በአማሪኛው ጉሮሮ በማለት ይገልጸው እና በእዚህም ውሃ ወደ ሰውነታችን ክፍል ዘልቆ የሚንቆረቆርበትን የሰውናታችን ክፍል ያሳያል። በእዚህም ጣማችንን ለመቁረጥ ይሚያስችለን የሰውነት ክፍል እንደ ሆነም ያሳያል።

በእዚህ መሰረት ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በግርድፉ የኢብራይስጡን ቋንቋ ተጠቅመን ስንተረጉመው  “ዋላ የምንጭ ውሃ እንደምትናፍቅ፣ አምላክ ሆይ፤ የኔም ጉሮሮ  እንዲሁ አንተን ትናፍቃለች// ጉሮሮዬ አምላክን፣ ሕያው አምላክን ተጠማች፤ መቼ ደርሼ ነው የአምላክን ፊት የማየው?” የሚለውን ትርጉም ያሰማናል። በእዚህም ምክንያት ሕያው የሆነው እግዚኣብሔር በሕይወታችን ውስጥ የጎደለ ከሆነ፣ በውስጣችን ለእርሱ ያለን ጣማት በክፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል፣ ለእርሱ ያለን ናፍቆት እያደገ ይመጣል፣ በኣዚህም ምክንያት ይህንን የሕይወት ጣማታችንን ለማርካት ወደ እርሱ የሕይወት ውሃ መጓዝ እንጀምራለን። ይህ ለእግዚኣብሔር ያለን ጥማት በጸሎታችን ይገለጻል። በእዚህም መሰረት ከእግዚኣብሔር ቤተመቅደስ ርቀን ለእርሱ መስዋዕት ማቅረብ በፍጹም አንችልም።

ለእግዚኣብሔር ያለን ጥማችንን ማርካት የምንችለው ያ ያለንን ጥም ተጠብቆ እንዲሄድ ማድረግ ይኖርብናል። ከእግዚኣብሔር ጋር ያመን ግንኙነት ተጠብቆ ይሄድ ዘንድ ማንኛውንም ከእግዚኣብሔር ጋር የምናደርገውን እውነተኛ ግንኙነት አጠናክረን መቀጠል ይኖርብናል፣

በተለይም ደግሞ እኛ ክርስቲያኖች፣ በተለይም ደግሞ እኛ ካህናት፣ በውስጣችን ላለው ምንፈሳዊ ጥማት ዋግ ኣልንሰጠው ይገባል፣ ምኞታችንን ለይተን ማወቅ ይገባናል፣ ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ የሆነ፣ ዋስትንናየሚሰጠው ነገር አለመሆኑን በሚገባ መረዳት ይገባል። የፍላጎት ወይም የምኞት ተሞክሮ ንብረን ለማግኘት ወይም የንብረት ባለቤት ለመሆን የምናደርገው ዓይነት ተመክሮ ሊሆንም በፍጹም አይገባውም። በእርግጠኛነት የምንፈልገውን በውስጣችን ያለውን መነፈሳዊ ጥማት ለማርካት እና ለመለመን የምናድርገው ተመክሮ ሊሆን ይገባዋል። አንድ ምዕመን ምሕረትን የሚለምን ተመጽዋች ነው። በእዚህ አግባብ እንዲህ ዓይነት ስሜት የሚሰማን ከሆንን በፍጾም መጨነቅ አይገባንም፣ በትክክለኝእው መንገድ ላይ እንገኛለን እና። የእዚህ ዓይነቱ ምኞት ደግሞ ልማዳዊ ከሆኑ ናህሪያችንን ነጻ ያደርገናል፣ ሕይወታችንን ከሚበክሉዋት፣ ሕይወታችንን ከሚያሰቃዩዋት፣ በሕብሪት እንድናብጥ ከሚያደርጉን ነገሮች ሁሉ ነጻ መሆን እንችላለን። ራሳችንን በራሳችን ቆልፈን እንዳንኖር ያደርገናል። እኔ እኔ እነ ብቻ ከሚል ስሜታችን እንድንላቀቅ ያደርገናል። ታዲያ ይህንን እንዴት ነው እውን ማድረግ የምንችለው፣ የእርሱን በር የማንኳኳት ምኞት ሊኖረን ይገባል፣ አንድ ገጣሚ እንዲህ በማለት ጽፎ ነበር “እርቃኔን ወደ እግዚኣብሔር መጓዝ በፍጹም አልችልም፣ ሆኑም ግን ልብሴን ማውለቅ አለብኝ” በማለት ምጻራዊ ቃል በመጠቀም ስናገር እንሰማለን። እርቅናችንን መሄድ አይገባንም // ወይም ልብስ መልበስ አይገባንም የሚሉት ቃላት እርስ በእርስ የሚጋጮ ቢመስሉም፣ ነገር ግን አዲስ ሕይወት መኖር የምንፈልግ ከሆንን ግን የድሮውን ልብስ ማውለቅ ይኖርብናል ማለት ነው።  ዋንው ቁመነገር ከእዚህ በፊት የነበረው ሕይወት አይደለም፣ ወይም አሁን እኔ ያለኝ ሕይወት ውናው ነገር ሊሆን አይገባውም፣ ነገር ግን እግዚኣብሔር በኣኔ ውስጥ ሊቀሰቅሰው የሚችለው ምኞት፣ እግዚኣብሔር በእነ ውስጥ ሊቀሰቅሰው የሚችለው ጥማት በሕይወቴ ውስጥ ይኑር አይኑር የሚለውን ለይቶ ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው።

ሰልእዚህም በውስጣችን ያለውን የተጠቂነት ዝንባሌ ጥንቆቆ ማወቅ ለእግዚኣብሔር ያለንን ጣማት ወይም ምኞት ይበልጡኑ እንዲቀሰቀስ ያደርገዋል፣ በእዚህም ተግባራችን ኢየሱስ ለምጻሙን ሰው አቅፎ እንደ ያዘው እኛንም አቅፎ እንዲይዘን ማድረግ እንችላለን (ማቴዎስ 8፡3)፣ ልክ እንደ በትኩሳት በሽታ ተይዛ እንደ ነበረችሁ እንደ ስምዖን አማት ኢየሱስ እጃችንን ይዞ እንዲያነሳን ማድረግ እንችላለን (ማቴ 9`20)፣ አስራ ሁለት አመት ደም ሲፈሳት የነበረችው ሴት የኢየሱስን ልብስ ጫፍ ነክታ እንደ ተፈወሰች ሁሉ እኛም መፈስ እንችላለን (መቴዎስ 17፡6)፣ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢያሪኮ በሚሄዱበት ወቅት በዚያም የነበሩ ሁለት ዐይነ ስውሮች በመንገድ ዳር ተቀምጠው ኢየሱስም በዚያ ማለፉን ሲሰሙ፣ “ጌታ ሆይ፤ የዳዊት ልጅ ማረን!” ዐይኖቻችን እንዲያዩ እንፈልጋለን” በማለት ጮኹበት ወቅት እርሱም እናዳናቸው ሁሉ እኛንም ያድነናል (ማቴዎስ 20:3)።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ይህ ቀደም ሲል ያቀረብንላችሁ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የበለይ የመስተዳድር አካላት እና የእርሳቸው የቀርብ የሥራ ተባባሪዎች በጋራ በመሆን ይህንን የያዝነውን የዐብይ ጾም ወቅት አስመልክተው በሮም ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው አራቺያ በሚባልበት ስፍራ በሚገኘው ዲቪኒ ማዬስትሮ በተባለው የሱባሄ መስጫ ማዕከል ተገኝተው እያደርጉት በሚገኘው ሱባሄ ላይ አባ ጆዜ ቶሌንቲኖ የተባሉ ካህን በዩሐንስ ወንጌል 4:4-23 ላይ በተጠቀሰው ኢየሱስ ከሳምራዊቷ ሴት ጋር በተገናኘበት ወቅት ውሃ አጠጭኝ ብሎ በጠየቀው ጣያቄ ዙሪያ ላይ ተመርኩዘው ያደርጉትን ስብከት ነበር።

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.