2018-03-01 18:04:00

ክቡር አባ ኪዩንጉ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ፍትሕም፣ ነጻነትም አለመኖሩን ገለጹ።


ክቡር አባ ኪዩንጉ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ፍትሕም፣ ነጻነትም አለመኖሩን ገለጹ።

የዚህን ዝግጅት ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ።

አሁን በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ፣ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የሚደርስ ጥቃት መቀጠሉን፣ ክቡር አባ ኢጎበርት ኪዩንጉ አስታወቁ። የኢየሱሳዊያን ማሕበር አባል የሆኑት አባ ኪዩንጉ ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፣ መንግሥት ሠራዊቱን ወደ ሥፍራው በመላክ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የሃይል እርምጃን በመውሰድ የንጹሐን ዜጎችን ሕይወት በከንቱ እያጠፋ ይገኛል ብለዋል። በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ መንግሥት አመጽን በመቀስቀስ በንጹሐን ዜጎች ላይ የሚወስደውን የጥቃት እርምጃን መውሰድ አላቋረጠም፣ ፍትሕና ነጻነትም ጨርሶ የለም ብለዋል።

ከትናንት በስቲያ በየቁምስናዎች የሚገኙ የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪዎች በርካታ ምዕመናን የተሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱ ሲነገር በዚህም ወቅት አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት እንዲወርድና በምትኩ አዲስ መንግሥት እንዲመሠረት ጥያቄን ማቅረባቸው ታውቋል። ይህን ጥያቄ ባቀረቡት ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ በተወሰደው የሃይን እርምጃ ብዙ ሰአዎች መቁሰላቸው ታውቋል። ሦስት ሰዎች ብቻ እንደተጎዱ ቢነገርም የተጎዱት ሰዎች ቁጥር ከዚያ በላይ እንደሚሆን  አባ ኪዩንጉ ተናግረዋል። የሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪዎች እንደገልጹት በሃገሪቱ ነጻነትና ፍትሕ እስከሚረጋገጥ ድረስ ሰላማዊ ጥያቄዎችን ከማቅረብና ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ድምዛችንን ከማሰማት ወደ ኋላ አንልም ብለዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.