2018-02-22 10:35:00

ኢየሱስ ሳምራዊት የሆነች ሴት ባየ ጊዜ “ውሃ አጠጭኝ” ብሎ መጠየቁ እኛን በጣም የምያስገርም ጉዳይ ነው


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የበለይ የመስተዳድር አካላት እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቀርብ የሥራ ተባባሪዎች ጋር በጋራ በመሆን በየወቅቱ እንደ አስፈላጊነቱ ሱባሄ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል።

በእዚህም መሰረት ቅዱስነታቸው የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የበለይ የመስተዳድር አካላት እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቀርብ የሥራ ተባባሪዎች ጋር በጋራ በመሆን ከባለፈው እሁድ ምሽት ማለትም ከየካቲት 11/2010 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ የካቲት 16/2010 ዓ.ም. ድረስ የሚቆይ ሱባሄ ለማድረግ በሮም ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው አራቺያ በሚባል ስፍራ በሚገኘው “ ዲቪኒ ማዬስትሮ” በሚባል የሱባሄ ምስጫ ማዕከል በመገኘት ስቡባሄ እያደርጉ እንደ ሆነ ቀድም ሲል መግለጻችን ያትወሳል።

የእዚህ ሱባሄ መሪ የሆኑት በፖርቹጋል ዋና ከተማ በሌዝቦን የሚገኘው የካቶሊክ ዩንቬርሲቲ ምክትል ድይሬክተር የሆኑ፣ በነገረ መልኮት አስተምህሮ ጠበት የሆኑ፣ ገጣሚ እና ደረሲ አባ ጆዜ ቶሌንቲኖ በሚባሉ ካህን እንደ ሆነ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን እርሳቸው በእዚህ ሱባሄ ላይ ለተሳተፉት ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ እና የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የበለይ የመስተዳድር አካላት እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቀርብ የሥራ ተባባሪዎች ያደርጉትን የመጀመሪያ አስተንትኖ እንደ ሚከተለው እናቀርብላችኃለን።

“በሰማርያም በኩል ማለፍ ነበረበት። ስለዚህ በሰማርያ፣ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ቦታ አጠገብ ወደ ነበረች፣ ሲካር ወደምትባል ከተማ መጣ። በዚያም የያዕቆብ የውሃ ጒድጓድ ነበረ፤ ኢየሱስም ከጒዞው የተነሣ ደክሞት ስለ ነበር በውሃው ጒድጓድ አጠገብ ተቀመጠ፤ ጊዜውም ከቀኑ ስድስት ሰዓት አካባቢ ነበር።አንዲት ሳምራዊት ሴት ውሃ ለመቅዳት ስትመጣ ኢየሱስ፣ “እባክሽ የምጠጣው ስጪኝ” አላት (ዩሐንስ 4፡4-7)

ኢየሱስ በያዕቆብ የውሃ ጉድጓድ አጠገብ ተቀምጦ አንዲት ሳምራዊት የሆነች ሴት ባየ ጊዜ “ውሃ አጠጭኝ” ብሎ መጠየቁ እኛን በጣም የምያስገርም ጉዳይ ሲሆን በከፍተኛ ግርምታችን የተነሳ የድንጋጤ ስሜት ውስጥ ይከተናል።

አንድ አይሁዳዊ ከአንዲት ሳምራዊት ሴት ጋር መነጋገር ይጀምራል፣ አንድ አይሁዳዊ ከአንዲት ሳምራዊ ጋር የመነጋገሩ ሁኔታ ደግሞ በአይሁዳዊያን ዘንድ ተቀባይነት የሌለው ነገር ነው። ኢየሱስ ወደ እኛ በመምጣት "ያለህን ነገር ስጠኝ፣ ልብህን ክፈት፣ ማንነትህን ስጠኝ” በማለት ይጠይቀናል።

ይህ ሁኔታ “በአግራሞት እንድንወሰድ” በማድረግ “በጥማት ውስጥ የሚገኘውን ደስታ” በእዚሁ በኢየሱስ እና በእዚህቺ ሳምራዊት ሴት መካከል ተደርጎ በነበረው ግንኙነት ውስጥ መመልከት ይቻላል።

ኢየሱስ ሳምራዊቱዋን ሴት “ውሃ አጠጭኝ” ብሎ መጠየቁ ለእኛ ግራ የመጋባት እና እርግጠኛ ያለመሆን ስሜት ውስጥ ይከተናል፣ ምክንያቱም ከውሃ ጉድጓድ ውስጥ ውሃ አውጥተን ለመጠጣት ወደ እዚያው የሄድነው እኛ ነን እንጂ እርሱ አለነበረም፣ ጥማት አድካሚ የሆነ ነገር ነው፣ ይህንን ጥማችንን መቁረጥ እንደ ሚገባን ጠንቅቀን እናውቃለን። ኢየሱስም ቢሆን ብዙ መንገድ በእግሩ በመጓዙ የተነሳ ደክሞት ነበር፣ በእዚህም ምክንያት በውሃው ጉድጓድ አጠገብ ተቀምጦ ነበር። በወንጌል ውስጥ በብዙ ቦታ እንደ ተጠቀሰው ቁጭ ብለው የምለምኑ ሰዎች ሁሉ እንደ የኔ ቢጤ ይቆጠሩ ነበር። ኢየሱስም ሲለምን እናየዋለን እርሱ የነበረው “አካል ማንኛችንም በቀን ውስጥ በምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች የተነሳ እንደ ምንደክም ሁሉ የእርሱም አካል ደክሞ ነበር፣ በፍቅር የተሞላ እንክብካቤ ከሌሎች ሰዎች ይፈልግ ነበር”። የሰው ልጅ ብቻ አይደለም እግዚኣብሔርን መለመን የሚገባው። “እግዚኣብሔርም የሰው ልጆችን ለምኑዋል”።

ኢየሱስ በድካም ውስጥም ሆኖ ሳይቀር እኛን ልፈልገን እንደ መጣ ይናገራል። በጣም ውስጣዊ እና ዘለቄታዊነት በሌላቸው ነገሮች ወይም ሁኔታዎች ውስጥ እንደ ምንኖር ኢየሱስ ስለሚያውቅ ይህንን ለእርሱ ያለንን ጥማት በመረዳት እኛን ልፈልገን መጣ። ይህም የውሃ ጥማት ብቻ አይደለም፣ ከእዚህም ላቅ ያለ ጣማት እንጂ “ጣማታችንን ለማርካት በማሰብ የምንጠማው ጥማት፣ ከቁስሎቻችን ጋር ለመገናኘት የምናደገውን ጥማት”። እርሱም “የሚጠጣ ውሃ ስጠኝ ይለናል”።

ታዲያ ለኢየሱስ ምን ብለን ነው መመለስ የሚገባን? አንዳችን ለአንዳችን እንሰጣጣለን ወይ? እኛ እንደ ተጠራን ልብ እንበል፣ ምክንያቱም እኛን ለመገናኘት ተነሳሽነቱን ሁል ጊዜም ቢሆን የሚወስደው ኢየሱስ ራሱ ነው። “የእኛ ምኞት ምኑንም ያህል የላቀ ቢሆንም፣ የእግዚኣብሔር ፍላጎት ደግሞ ከእኛ ፍላጎት እጅጉን የላቀ ነው። በእዚሁ በዩሐንስ ወንጌል 4፡4-23 ላይ እንደ ተጠቀሰው ኢየሱስ ለዛች ሳምራዊት ሴት  የሕይወቷን እውነታ እንቅጩን በነገራ ጊዜ “እርሷን አላሳፈራትም ወይም አላሸማቀቃትም ነበር። ነገር ግን በተቃራኒው በእግዚኣብሔር ጸጋ እንደተጎበኘች እና የጌታ እውነት ነጻ እንዳወጣት ተሰምቱዋት ነበር።

እኛ (ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የበለይ የመስተዳድር አካላት እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቀርብ የሥራ ተባባሪዎች) እዚህ መሆናችንን እግዚኣብሔር በሚገባ ሰለምያውቅ በእግዚኣብሔር እቅፍ ውስጥ እናዳለን ይሰማን። እናም በእነዚህ የሱባሄ ቀናት "ሕይወታችንን እና ውስጣችን ሊያሳርፍ የሚችል ፀጋን ለመማር እንሞክር”። በውስጣችንም “ጌታ ሆይ አንተን በመጠባበቅ ላይ እገኛለሁ” በማለት እንጠይቀው። ይህም ማለት ጌታ ሆይ የምታስፈልገኝ አንተ ብቻ ነህ፣ የምያስፈልገኝ አንተ የምትሰጠኝ ነገር ብቻ ነው” እንበለው።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ይህ ቀደም ሲል ያቀረብንላችሁ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የበለይ የመስተዳድር አካላት እና የእርሳቸው የቀርብ የሥራ ተባባሪዎች በጋራ በመሆን ይህንን የያዝነውን የዐብይ ጾም ወቅት አስመልክተው በሮም ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው አራቺያ በሚባልበት ስፍራ በሚገኘው ዲቪኒ ማዬስትሮ በተባለው የሱባሄ መስጫ ማዕከል ተገኝተው እያደርጉት በሚገኘው ሱባሄ ላይ አባ ጆዜ ቶሌንቲኖ የተባሉ ካህን በዩሐንስ ወንጌል 4:4-23 ላይ በተጠቀሰው ኢየሱስ ከሳምራዊቷ ሴት ጋር በተገናኘበት ወቅት ውሃ አጠጭኝ ብሎ በጠየቀው ጣያቄ ዙሪያ ላይ ተመርኩዘው ያደርጉትን ስብከት ነበር።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.