2018-02-09 09:09:00

የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት 16ኛ፣ በፍቅርና በቸርነት ታጅቤ ወደ ዘለዓለማዊው ቤት በመጓዝ ላይ እገኛለሁ ማለታቸው ተሰማ።


የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት 16ኛ፣ በፍቅርና በቸርነት ታጅቤ ወደ ዘለዓለማዊው ቤት በመጓዝ ላይ  ማለታቸው ተሰማ።

በኢጣሊያ የሚታተመውን “ኮሪየረ ደላ ሴራ” የተባለ ዕለታዊ ጋዜጣ አንባቢዎች፣ ስለ ቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት 16ኛ ጤንነት ሁኔታ ለማወቅ ፈልገው ላቀረቡላቸው ጥያቄ፣ ቅዱስነታቸው በሰጡት መልስ፣ በፍቅርና በቸርነት ታጅቤ ወደ ዘለዓለማዊው የዕርፍት ሥፍራ በመጓዝ ላይ ነኝ ብለዋል።

የዚህን ዝግጅት ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ።

ቅዱስነታቸው ለጋዜጠኛ ለዶክተር ማሲሞ ፍራንኮ በጻፉት መልዕክታቸው፣ በርካታ የጋዜጣው አንባቢዎች ስለ እኔ ጤንነት ለማወቅ ያላቸው ጉጉት ልቤን ነክቶኛል። ከሰውነት መድከም ባሻገር በውስጤ ወደ ዘለዓለማዊው የዕርፍት ሥፍራ በመጓዝ ላይ እንደሆንኩ ይሰማኛል ብለው ይህን የሚቀረኝን ዕድሜ በፍቅርና በቸርነት በመጓዝ ላይ ስሆን ይህ ጉዞም ካሰብኩት ልባዊ ፍቅር እና ቸርነት በላይ ነው ብለዋል። በዚህ መሠረት ከጋዜጣው አንባቢዎች የቀረበውን ጥያቄ እና ስለ እኔ ጤንነት ለማወቅ መፈለጋቸውን፣ ዘወትር ከእኔ ጋር እንደሆኑ በማሰብ ምስጋናዬን እያቀረብኩ በጸሎቴም እንደማስታውሳቸው ላረጋግጥላቸው እወዳለሁ ብለዋል።

ከሰውነት መድከም ባሻገር ያሉትንና ለአንባቢዎቹ ምስጋና ማቅረባቸው ላይ “ኮሪየረ ደላ ሴራ” ጋዜጣ ዘጋቢ የሆኑት ዶክተር ማሲሞ ፍራንኮ ትንተና ሲሰጡ፣  ቅዱስነታቸው ስለ ጤናቸው ሁኔታ ለጠያቂዎቻቸው የሰጡት ምላሽ አጭር ቢሆንም ጥልቀት ያለው መሆኑን አስረድተው ላለፉት አምስት ዓመታት ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር የነበራቸው ግንኙነት፣ በሁለቱ መካከል መልካም መቀራረብ የታየበት እንደነበር ገልጸው፣ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት ለጥያቂዎቻቸው የሰጡት ምስጋና መንፈሳዊናትና ትህትና የተሞላበት እንድሆነ የ“ኮሪየረ ደላ ሴራ” ጋዜጣ ዘጋቢ የሆኑት የሆኑት ዶክተር ማሲሞ ፍራንኮ አስረድተዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት 1፮ኛ በ2005 ዓ. ም. የርዕሠ ሊቃነ ጵጵስነት ሐዋርያዊ መንበር ስልጣናቸውን ተተኪያቸው ለሆኑት ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮ ማስረከባቸው የሚታወስ ነው። ከ600 ዓመታ ወዲህ ይህ ሲሆን የመጀመሪያው የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት መሆናቸው ታውቋል። የርዕሠ ሊቃነ ጵጵስና ሐዋርያዊ መንበር ስልጣናቸውን ባስረከቡበት ጊዜ ቀሪውን ሕይወታቸውን በሙሉ መላዋ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንን በጸሎት ለማገልገል ቃል መግባታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ከ2005 ዓ ም ጀምሮ በቫቲካን ከተማ ውስጥ በሚገኘው “ማተር ኤክለሲያ” በሚባል ገዳም ውስጥ እንደሚኖሩ ይታወቃል።                   

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.