2018-02-08 08:36:00

በእግዚአብሔርና በሕዝቦቹ መካከል የተደረገው ውይይት፣ በቅዳሴ ወቅት በሚነበቡት ምንባባት አማካይነት ይበልጡኑ ይዳብራል


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች  በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። የእዚሁ መርሃ ግብር አንዱ አካል በሆነው በዛሬው እለት ማለትም በጥር 30/2010 ዓ.ም. ያደርጉት አተምህሮ ከእዚህ በፊት በመስዋዕተ ቅዳሴ ዙሪያ በተከታታይ አድርገው የነበረ አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን፣ ከእዚህ ቀደም በመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ዙሪያ ላይ ትኩረታቸውን በማድረግ በእዚሁ የመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ከፍተኛ መንፈሳዊ ትርጉም ያቸውን ክፍሎች በማንሳት አስተምህሮ ማድረጋቸውን ከቅድም ሲል መዘገባችን ይታወሳል።

የእዚህን አስተምህሮ ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

 በእዚህም መሰረት ቀደም ባሉት ጊዜያት በመስዋዕተ ቅዳሴ የመግቢያ ስነ-ስረዓት ላይ ስላለው የኑዛዜ ጸሎት፣ በመቀጠልም አሁንም በመስዋዕተ ቅዳሴ የመግቢያ ስነ-ስረዓት ላይ ስላለው የመግቢያ ጸሎት አንስተው ሰፊ የሆነ ትንታኔ መስጠታቸው የሚታወቅ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ባደርጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ደግሞ ከእዚሁ የመግቢያ ጸሎት በመቀጠል የሚገኘውን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባትን በተመለከተ ሰፊ አስተምህሮ አድርገዋል።

በእዚህም መሰረት የእግዚኣብሔር ቃል በሕይወታችን የሚያደርገው ጉዞ በተመለከተ የትናገሩት ቅዱስነታቸው የእግዚኣብሔር ቃል ከጆሮዋችን ወደ ልባችን ከልባችን ወደ እጃችን በመጓዝ መልካም ተግባራትን እንድናከናውን ይረዳናል ማለታቸውምን መዘገባችን ይታወሳል። በዛሬው እለት ማለት በጥር 30/2010 ዓ.ም. ባደርጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ከባለፈው ሳምንት አስተምህሮ የቀጠለ እና አሁንም በመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ወቅት ሰለምነበቡት የእግዚኣብሔር ቃላት እና በመቀጠልም በእዚህ በእግዚኣብሔር ቃል ላይ መስረቱን ስላደርገው ስብከት በማንሳት ጥልቅ የሆነ አስተምህሮ ማድረጋቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ለተገኙ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች ያደርጉትን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደ ምን አረፈዳችሁ!                           

በእግዚአብሔርና በሕዝቦቹ መካከል የተደረገው ውይይት፣ በቅዳሴ ወቅት በሚነበቡት ምንባባት አማካይነት ይበልጡኑ በመዳበር  በቅዱስ ወንጌል እወጃ ወቅት  ምልአቱን ያገኛል። ከእዚያም በመቀጠል ሃሌሉያ የምለው አጭር መዝሙር ከተዘመረ በኃላ ወይም ደግሞ በስብከተ ገና ወቅትምዕመኑ በቅዱስ ወንጌል ልናገራቸው የምመጣውን ጌታ ለማዳመጥ ይዘጋጃሉ። የክርስቶስ ምሥጢር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በምልአት በመገለጥ ሲያበራ፣ በእዚህም መልኩ በቅዳሴ ስነ-ስረዓት ወቅት በቅድሚያ ከቡሉይ ኪዳን ይሁን ከአዲስ ኪዳን ተወስደው የምነበቡት ቃላት ትርጉማቸውን በሚገባ እንድንረዳ ቅዱስ ወንጌል ብራሃን በመሆን ይረዳናል። በእርግጥ "በስርዓት ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ወቅት በሚነበቡት የእግዚኣብሔር ቃላት ውስጥ ይሁን በአጠቃላይ በቅዳሴ ስነ-ስረዓተ አምልኮ ወቅት ክርስቶስ በመአከሉ ይገኛል።

በእዚህም ምክንያት ነው እንግዲህ ቅዱስ ወንጌል ከሌሎች ምንባባት ለየት ባለ ሁኔታ በአክብሮት እና በአምልኮ መንፈስ የሚከበረው፣ የሚነበበውም በዚህ ምክንያት ነው። በእዚህ ምክንያት ነው እንግዲህ በመስዋዕተ ቅዳሴ ሰነ-ስረዓት ወቅት ቅዱስ ወንጌልን የሚያነበው ሰው ካህን የሆነ ወይም ለየት ያለ መነፍሳዊ ስልጣን የተሰጠው ሰው መሆን አለበት የሚባለው በእዚሁ ምክንያት ነው፣ ቅዱስ ወንጌል ከተነበበ በኃላ አንባቢው ቅዱስ ወንጌልን የሚስመው በእዚሁ ምክንያት ነው፣ ቅዱስ ወንጌል በሚነበብበት ወቅት ቆመን የምናዳምጠውም በእዚሁ ምክንያት ነው፣ ቅዱስ ወንጌል ከመነበቡ በፊት በግንባራችን፣ በንፈራችን እና በደረታችን ላይ በመስቀል ምልክት የምናማትበውም በእዚሁ ምክንያት ነው። በመስዋዕተ ቅዳሴ ሰነ-ስረዓት ወቅት ቅዱስ ወንጌል ሲነበብ የሻማ ብርሃና እንዲበራ፣ እጣን እንዲጨስ የሚደረግበት ምክንያት በሚነበበው የወንጌል ቃል አማካይነት በብቃት የሚናገረው ክርስቶስ በመሆኑ ለእዚያ ቃል ክብር ለመስጠት ነው። በእነዚህ ምልክቶች የተነሳ እያንዳንዱን ማኅበረ-ምዕመንመነፈሳዊ ለውጥ ማምጣት የሚያስችለን እና ሕይወታችንን መቀየር አቅም ያለውክርስቶስ በእዚያ ሆኑ መልካም ዜናውን እንደ ሚያቀርብልን ይገነዘባል። ይህ የወንጌል ቃል ቀጥተኛ የክርስቶስ ንግግር በመሆኑ የተነሳ ቅዱስ ወንጌል ተነቦ ካለቀ በኃላክርስቶስ ሆይ ምስጋና ለአንተ ይሁንበሚል የምስጋና ቃል የሚጠናቀቀውም በእዚሁ ምክንያት ነው።

ስለዚህ በመስዋዕተ ቅዳሴ ሰነ-ስረዓት ወቅት የሚነበበው የቅዱስ ወንጌል ቃል  ነገሮች ከእዚህ ቀደም እንዴት እንደነበሩ ለማወቅ ወይም ለመመልከት ሳይሆን፣ ነገር ግን ኢየሱስ በአንድ ወቅት ያደረጋቸውን እና የተናገራቸውን ቃላት ለመገንዘብ፣ አሁንም ቢሆን እንደዚያ ማድረጉን እንደ ሚቀጥል እና በእኛ ላይ እንደ ሚፈጽመው ለእኛ ይናገራል። ቅዱስ አጎስጢኖስ "ወንጌል የክርስቶስ ልሳን ነው፣ እርሱ በሰማይ ነግሦ የሚኖር ቢሆንም፣ ነገር ግን በምድር ላይ መናገሩን አላቁረጠምበማለት ጽፉዋል። እንግዲህ በስርዓተ አምልኮ ወቅት የሚናገረን ክርስቶስ ከሆነ መስዋዕተ ቅዳሴን በምንሳተፍበት ወቅት ለእርሱ ምላሽ ልንሰጠው ይገባል።

በቅዳሴ ወቅት በተነበበው ቅዱሱ ወንጌል አማካይነት የተናግረው ክርስቶስ  በጥልቀት መረዳት እንችል ዘንድ ቅዱስ ወንጌል ተነቦ ካለቀ በኃላ ካህኑ የሚያደርገው ስብከት አስፈላጊ ነው። የሁለተኛው የቫቲካን ጉባሄ በመስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት የሚደርገውን ስብከት በተመለከተስብከት ዝም ብሎ የገጠሙንን ነገሮች የምናወራበት ተራ የሆነ ንግግር ማለት አይደለም፣ ወይም አንድ ጉባሄ አይደለም ወይም ደግሞ አንድ አስተምህሮ አይደለም፣ ነገር ግን ቃሉ በሕይወታችን ውስጥ በምልአት ይሰርጽ ዘንድበክርስቶስ እና በሕዝቡ መካከል ቀደም ሲል ተደርጎ የነበረውን ውይይት እንደ ገና ማስቀጠል ማለት ነው የቅዱስ ወንጌል ትንታኔ የሚገለጸ በሕይወታችን ውስጥ ነው። የጌታ ቃል ጉዞውን የሚያቆመው በእኛ ሥጋ ውስጥ በመግባት ነው፣ በማርያም እና በቅዱሳን እንደተገለፀው ሥራውን ወደ ፍጻሜው ያመጣል።

በመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ወቅት የሚደርገውን ስብከት በተመለከተ Evangelii gaudium (በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም የወንጌል ደስታ በተሰኘው ቃለ ምዕዳኔ ውስጥ) ስብከትን በተመለከተበስብከት ወቅት ማኅበረ ምዕመኑ እና ሰባኪው በስብከት አማካይነት ከክርስቶስ ጋር ኅብረት እንዲኖራቸው በማድረግ በቅዱስ ቁርባን አማካይነት ሕየወትን ይቀይራልበማለት ገልጨ ነበር።

በቅዳሴ ስነ-ስረዓት ወቅት ስብከት የሚይደርግ ሰው እምነቱን በሚገባ በመከተል የእርሱን አገልግሎት በጥሩ ሁኔታ የሚፈጽ ሰው ሊሆን ይገባል፣ በመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ለሚሳተፉ ሰዎች ሁሉ እውነተኛ አገልግሎት መስጠት ይኖርበታል፣ ይህንን ስብከት የሚሰሙ ሰዎች ሁሉ ታዲያ የሰሙትን ነገር በተግባር በመለወጥ የራሳቸውን ድርሻ መወጣት አለባቸው።

በመጀመሪያ ደረጃ በንቃት በመሳተፍ፣ ተገቢውን ውስጣዊ ዝግጅት በማድረግ፣ ትክክለኛውን ውስጣዊ አሠራር በማየት፣ በሰባኪው ላይ ምንም ዓይነ ቅድመ ሁኔታ ባለማስቀመጥ ማዳመጥ ይኖርባቸዋል ምክንያቱም እያንዳንዱ ሰባኪ መልካም ስራዎች እና ገደቦች ወይም ውስን መሆናቸውን ማወቅ ያስፈልጋል።

አንዳንድ ጊዜ ለረዥም ስብከት በሚሆንበት ወቅት ወይም በእለቱ ምንባባት ላይ የማያተኩር ቢሆን፣ ወይም ለመረዳት የምያስችግር ነው፣ ወይም ደግሞ አንድ አንድ ጊዜ እንቅፋት የሚፈጥር ስብከት ነው፣ በአጠቃላይ ይህ ስብከት ጥሩ ነው ወይም አይደለም በማለት ለመወሰን ያስችለን ዘንድ በቅድሚያ ማዳመጥ ያስፈልገናል።

በስርዓተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ወቅት ስብከት የሚያደርጉ ሰዎች ኃላፊነታቸውን በተገቢው መልኩ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚወጡ ሊሆኑ ይገባል፣ በመስብኪያ ቦታ ላይ ሆነ የሚስበክ ሰው እድሉን ሊጠቀም ይገባዋል፣ በተመሳሳይ መልኩ ይህንን ስብከት የሚያዳምጡ ሰዎች እድሉን መጠቀም ይኖርባቸዋል። ይህንን ስል መወቃቀስ የገባል ለማለት  ፈልጌ ሳይሆን እገዛ ማድረግ ይገባል ለማለት ነው። ለካህኑ ቅርብ ከሆኑ ምዕመናን በተሻለ ሁኔታ ካህኑን ሊረዳ የሚችል ማነው?

በመጨረሻም የመጽሐፍ ቅዱስ በቂ እውቀት ያለው ሰው የስብከት ሥነ-ስርዓት በሚገባ ሊሳተፍ ይችላል፣ ስብከቱን እንዲረዳ በእጅጉ ይደግፋል ብዬ ለመናገር እወዳለሁ።  በተደጋጋሚ ወንጌልን የማያነቡ ግለሰቦች ወንጌልን ለማዳመጥ እጅግ ይቸግራቸዋል በመስዋዕተ ቃዳሴ ስነ-ስረዓት ወቅት የሚደረገውን ስብከት ለመረዳት ይቸግራቸዋል። በመጨረሻም በመስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት በሚነበቡት የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት፣ በቅዱስ ወንጌል እና ከእዚያም ቀጥሎ በሚገኝ ስብከት አማካይነት እግዚኣብሔር ከእዝቡ ጋር ይወያያል፣ እርሱን በጽሞና እና በታላቅ ክብር የሚያዳምጡ ሁሉ በተመሳሳይ ጊዜ እግዚኣብሔር ቅርብ መሆኑን ይረዳሉ፣ እግዚኣብሔር ሁል ጊዜ ሥራውን እንደ ሚሰራም ይገነዘባሉ ማለት እንችላለን። እንግዲያው "የምስራቹን ቃል" የምንሰማ ብንሆን እና በእርሱም አማካይነት መንፈሳዊ ለውጥ የምናመጣ እና ሕይወታችን የሚቀየር ከሆነ በእዚህም ምክንያት  እራሳችንን እና ዓለምን መለወጥ እንችላለን።

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.