2018-02-05 17:30:00

ር. ሊ. ጳ. ፍራንቸስኮ በዛሬው ቀን ከቱርክ በሬዚዳንት ራጃብ ጣይብ ሄርዶጋን ጋር በቫቲካን ተገናኙ


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዛሬ ረፋዱ ላይ የቱርክ ፐሬዚዳንት ከሆኑት ራጃብ ጣይብ ሄርዶጋን ጋር በቫቲካን ተገናኘተው መወያየታቸው የተገለጸ ሲሆን በእዚሁ ቆይታ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ውስጥ ስለሚታየው የሰብዓዊ መብት አያያዝ ዙሪያ መመካከራቸውም ተገልጹኃል።

በቱርክ የሚኖሩ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ጉዳይ በማንሳት ሰፊ ውይይ ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን  በመካከለኛው ምስርቅ በሚገኙ ሀገራት ውስጥ ሰብዓዊ መብቶች ይጠበቁ ዘንድ እና በተለይም በቀጠናው የሚታየው ብጥብጥ ተወግዶ ሰላም የስፈን ዘንድ ቱርክ የበኩሉዋን አስተዋጾ እንድታደርግ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

በቱርክ የሚገኙ የካቶሊክ ምዕመናን አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግላቸው፣ የቱርክ ሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታን እና ከተለያዩ ሀገራት በተለዩ ምክንያቶች ተሰደው በቱርክ የሚገኙ ስደተኞች አያያዝ ዙሪያ ሰፋ ያለው ውይይት ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በተለይም ደግሞ በአሁኑ ወቅት በቱርክ የሚገኙ ስደተኞች እየገጠማቸው በሚገኙ ተግዳሮቶች ዙሪያም ውይይት ማድረጋቸውም ተገልጹዋል።

በአሁኑ ወቅት የዓለማችን የመወያያ አርእስት በመሆን በርካቶችን በማወዛገብ ላይ የሚገኘውን የኢየስሩሳሌም ከተማ ጉዳይ በማንሳት ውይይት ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን ኢየሩሳሌምን በተመለከት የሚደርጉ ማንኛቸውም ውሳኔዎች በውይይት፣ በድርድር እና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ብቻ ሲካሄድ ነው በቀጣነው ሰላምን ማምጣት የሚቻለው የሚለውን አንስተው በጋራ መወያየታቸውም የተገለጸ ሲሆን በእዚህ ረገድ በቀጠናው ሰላም እንዲመጣ ቱርክ የራሱዋን አስተዋጾ ማድረግ እንደ ሚገባት ቅዱስነታቸው ጨምረው መግለጻቸውም ተዘግቡዋል።

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.