2018-02-01 16:31:00

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ በስብከታቸው “ሞት የማይቀር እዳ ነው፣ ሞት ውርሳችን ነው፣ ሞት መታሰቢያችን ነው” ማለታቸው ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ጥዋት በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት መስዋዕተ ቅዳሴ እንደ ሚያሳርጉ ይታወቃል። በዛሬው እለት ማለትም በጥር 24/20101 ዓ.ም. ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት “ስለ ሞት ማሰብ እኛ የጊዜያት ጌታ እንዳልሆንን ጥንቅቀን እንድነረዳ በማድረግ ከግራ መጋባት መንፈስ ነጻ ያወጣናል” በማለት ስብከታቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው “ሞት የማይቀር እዳ ነው፣ ሞት ውርሳችን ነው፣ ሞት መታሰቢያችን ነው” ማለታቸው ተገለጹዋል።

የእዚህ ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

 

"እኛ ዘለአለማዊ ወይም ዘላቂ የሆንን ፍጡራን አይደለንም፣ እኛ በጊዜ ውስጥ እየተጓዝን የምንገኝ  ሰዎች ነን፣ በጊዜ የምንጀምር እና በጊዜ ውስጥ የምንጠናቀቅ ሰዎች መሆናችንን በፍጹም መዘንጋት የለብንም” ያሉት ቅዱስነታቸው በእለቱ በላቲን ስረዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት 1 መጽሐፈ ነግሥት 2 ተወስዶ በተነበበው እና የንጉሥ ዳዊትን ሞት በሚያማላክተው ታሪክ ላይ ተመርኩዘው ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት “የጊዜያትን ጥቅም መረዳት የሚያስችለንን ጸጋ እግዚኣብሔር እንዲሰጠን መጸለይ እንደ ሚገብ ገልጸው ይህም ጸጋ ራሳችንን በራሳችን በመቆለፍ የራሳችን እስረኞች እንዳንሆን ይረዳናል ብለዋል።

“ሞት ሁለቻንንም የሚነካ ሐቅ ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ማት ይዘግይ ወይም ዛሬ ይሁን ነገ ለሁላችን የማይቀር ሐቅ መሆኑን ማስታወስ እንደ ሚገብ የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን ብለዋል. . .

የሕይወታችን ጌቶች ሆነን እንዲሰማን የሚያደርግ ፈተና ብዙን ጊዜ ያጋጥመናል፣ በእዚህም ምክንያት መጭው ጊዜ በደንብ ስለማይታያቸው ዝም ብለው በራስ ወዳደነት መነፈስ ውስጥ ሲመላለሱ ይኖራሉ። የእዚህ ዓይነቱ ኑሮ ደግሞ ሁላችንም እንደ ምናውቀው በሞት ይጠናቀቃል። ለእዚህም ነው ብዙን ጊዜ ቤተክርስትያን በሞት ዙሪያ የተለያዩ ዓይነት አስተምህሮችን የምትሰጠው፣ እኛ የሞት ጊዜያችንን በሚገባ በማሰብ በጥንቃቄ መኖር እንዳለብን ቤተክርስትያን የምታስተምረን በእዚሁ ምክንያት  ነው።

“እኛ የጊዜያት ጌቶች አይደለንም፣ ይህንንም ደጋግመን ማስታወስ በጣም ይረዳናል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም በአሁኑ ጊዜ እየገጠመን ካለው ውዥንብር ነጻ እንድንሆን ያደርገናል፣  ሞት የማይቀር ውርሳችን ነው ካሉ በኋላ ሁል ጊዜም ቢሆን የምንሞትበትን ቀን ማሰብ መልካም የሆነ ሕይወት እንድንኖር በማድረግ ጥሩ ስሜት እንዲኖረን ያደርገናል ካሉ በኃል ስብከታቸውን አጠናቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.