2018-01-20 17:29:00

ቅዱስነታቸው በፔሩ "ትንሹ ልዑል" በመባል የሚታወቀውን የሕጻናት ማሳደጊያ መጎብኘታቸው ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በፔሩ የሚያደርጉትን 22ኛው ሐዋሪያዊ ጉብኝት በመቀጠል በፔሩ ቡሄርቶ ማልዶናልዶ በሚባል ሀገረ ስብከት ውስጥ የሚገኘውን እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር 1980 ዓ.ም. የተቁቋመውን እና በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሥር የሚተዳደረውን የተክኖሎጂ፣ የህክምና፣ የእርሻ እና የሀገር አስጎብኝ ተማሪዎች የሚሰለጥኑበት ተቋም ውስጥ ተገኝተው ንግግር ካደርጉ በኃላ በእዚያው አከባቢ ወደ ሚገኘው ሆጋር ወደ ሚባለው የወላጅ አልባ ሕጻናት ማሳደጊያ ጣቢያ አቅንተው ነበር።

ሆጋር የወላጅ አልባ ሕጻናት ማሳደጊያ ጣቢያ ትንሹ ልዑል” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሲሆን 40 የሚሆኑ ወላጅ አልባ ሕጻናት የሚኖሩበት ማዕከል ሲሆን እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር 1996 ዓ.ም. አባ ዛቬር አርበት በተባሉ አንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካህን የተቋቋም የሕጻናት ማሳደጊያ መዕከል ነው።

ቅዱስነታቸው በእዚያ በተገኙበት ወቅት ለተደረገላቸው አቀባበል ከፍተኛ ምስጋና አቅርበው እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን በተለይም ደግሞ በእዚያ የሚገኙ ታዳጊ ሕጻናት ላቀረቡላቸው ዝማሬ ከፍተኛ የሆነ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

“እናንተ ሕጻናት የማሕበረሰቡ ክቡር የሆናችሁ ሐብት ናችሁ” ካሉ በኃላ ከእናንተ በእድሜ የሚብልጡ ጎልማሶች ለእናንተ እንክብካቤ ማድረግ ሲገባቸው ባለማድረጋቸው ይቅርታን እጠይቃችኃለሁ ብለዋል። “እናንተ የማኅበረሰቡ ትልቅ ሐብት በመሆናችሁ የተነሳ እንክብካቤ ሊደርግላችሁ ይግባል” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅድስነታቸው “አንድ አንድ ጊዜ የእናንተ ወላጅ አባት እና እናት የሆኑት እዚህ ከእናንተ ጋር ባለመኖራቸው የተነሳ የሐዘን እና የትካዜ ስሜት ሊሰማችሁ ይችል ይሆናል” ያሉት ቅዱስነታቸው “ይህም ስሜት አንድ አንድ ጊዜ በጣም ሊጎዳችሁ ይችላል” ብለዋል።

“ነገር ግን የእናንተ የእያንዳንዳችህ ሕጻናት ሕይወት፣ የምትናገሩት ንግግር ሳይቀር ለእኛ የተስፋ ብርሃን ነው” ያሉት ቅዱስነታቸው “እናንተ ለእኛ የተስፋ ብርሃን በመሆናችሁ የተነሳ ላመስግናችሁ እወዳለሁ” ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በንግግራቸው ማብቂያ ላይ እንደ ገለጹት “ጌታ ሁላችሁንም ይባርካችሁ፣ ይጠብቃችሁም፣ ፊቱን በእናንተ ላይ ያብራ፣ ምሕረቱን ያሳያችሁ፣ ፊቱንም ወደ እናንተ ይመልስ፣ ስለሙን ይስጣችሁ፣ በአብ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም አንዱ አምላክ አሜን” ካሉ በኃላ በእዚያ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.