2018-01-20 17:21:00

ር. ሊ. ጳ. ፍራንቸስኮ በፔሩ ቡሄርቶ ማልዶናልዶ በሚባል ሀገረ ስብከት የሚገኘውን የቴክኖሎጂ ተቋም ጎበኙ


 

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በፔሩ የሚያደርጉትን 22ኛው ሐዋሪያዊ ጉብኝት በመቀጠል ከአማዞን ደን አከባቢ ከሚኖሩ ሕዝቦች ጋር ከነበራቸው ቆይታ በኃላ በፔሩ ቡሄርቶ ማልዶናልዶ በሚባል ሀገረ ስብከት ውስጥ የሚገኘውን እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር 1980 ዓ.ም. የተቁቋመውን እና በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሥር የሚተዳደረውን የተክኖሎጂ፣ የህክምና፣ የእርሻ እና የሀገር አስጎብኝ ተማሪዎች የሚሰለጥኑንበት ተቋም ውስጥ በትላንትናው እለት ተገኝተው ንግግር ማድረጋቸውን ለመረዳት ተችሉዋል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያደርጉትን ንግግር እንደ ሚከተለው በአጭሩ አስናድተነዋል እንድትከታተሉን እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ

እዚህ የተሰበሰባችሁ ተማሪዎች በፔሩ ከሚገኘው የአማዞን መዳረሻዎች ብቻ የተውጣጣችሁ ሳትሆኑ ነገር ግን አንዳንዶቻችሁ በጎረቤት ሀገሮችም መጥታችሁ እዚህ እንደ ምትማሩ ሰምቻለሁ። ይህ ደግሞ ቤተክርስቲያን ድንበር የለሽ እንደ ሆነች የሚያሳይ መልካም የሆነ ገጽታ ነው። እንደዚህ ያሉት ገጠመኞች ለአንድ አፍታ አብርን እንድንሆን በማድረግ፣ ከየትም እንምጣ፣ የትውልድ ስፍራችን የትም ይሁ የት በጋርራ በመሆን የአብሮነት ባሕላችንን የበለጠ በማነሳሳት ተስፍችን እንደ ገና እንዲያንሰራራ ያደርጋል። እዚህ በተገኘውበት ወቅት የእንኳን ደህና መጣህ መልእክት በቅድሚያ ያስተላለፉት ብጹዕ ጳጳሳ ዴቪድ ከእዚያም በመቀጠል የሕይወት ተመክሮዎቻቸውን ያካፈሉን ሁለት ሰዎችን ማመስገን እወዳለሁ። እነርሱ በንንግራቸው ወቅት “እርሶ በአሁኑ ወቅት እየጎበኙ ያሉት አከባቢ ቀደም ሲል የተረሳ፣ የቆሰለ እና የተገለለ አከባቢ ነው. . . .ነገር ግን እኛ የምንኖርበት አከባቢ ሰው የሌለበት አከባቢ ተደርጎ ይቆጠራል” ብለው መናገራቸው ይታወሳል። “እኛ የምንኖርበት አከባቢ ሰው የሌለበት አከባቢ ተደርጎ ይቆጠራል” በማለታችሁ የተነሳ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። ይህንንም በይበልጥ መግልጽ ወይም ማሳየት ይኖርባችኃል። ነገር ግን ይህ መሬት ስም አለው፣ ገጽታም አለው ይህም ስም እና ገጽታ እናተ ናችሁ።

ይህ አከባቢ “የእግዚኣብሔር እናት” የሚል መጣም ደስ የሚል መጠሪያ አለው። ታዲያ እኔ ዛሬ ስለ ማሪያም መናገር እፈልጋለሁ፣ እርሷ ወጣት እና በጣም ገጠር የሚባል ቦታ የኖረች፣ እርሷ የኖረችበት መንደር የተገለለ የነበረ፣ እንዲያም በብዙዎቹ ዘንድ ሰው የማይኖርበት አከባቢ ተደርጎ የሚቆጠር አከባቢ ነበር። እርሷ ታላቁን ሰላምታ እና በሰው አእምሮ ሊታሰብ የማይቻለውን የእግዚአብሔር እናት የመሆን ጥሪ የተቀበለችው በእዚሁ በገጠራማ ቦታ ሆና ነበር። በማቴዎስ ወንጌል 1125 ላይበዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፤ ይህን ከጥበበኞችና ከዐዋቂዎች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁእንደ ሚለው ትናንሽ ሚባሉ ሰዎች የሚሰጣቸው ደስታ አለ።

ይህንንም በማሪያም ውስጥ የምትመለከቱት ተምሳሌት ብቻ ሳይሆን እናንተም እናት አላችሁ! እናት በሚኖረን ወቅት የተረሳን መስሎን የሚሰማን ስሜት ከእኛ በኖ ይጠፋል፣ ምክንያቱም እናት ካለች ቤተሰብ አለ፣ ቤተሰብ ካል ሕዝብ አለ፣ ሕዝብ ካለ መሬት አለ፣ እነዚህ ሁሉ ነገሮች  ካሉን ደግሞ እግዚኣብሔር አለ። ብለው ቅዱስነታቸው በቅቱ ተናግረዋል።

ቅዱስነታቸው ይህንን ያሉበት ምክንያት በእዚያ በአማዞን ጥቅጥቅ ደን አከባቢ የሚኖሩ የማሕባረሰብ ክፍሎች ለብዙ ዘመናት ከቀሪዎቹ ከፔሩ እዝቦች ተገለው፣ በድኽነት አረንቋ ስር የሚኖሩ፣ እንደ ሰው የማይቆጠሩ፣ መሬታቸው ውስጥ የምገኙ የተፍጥሮ ሀብት እና መአድን በሌሎች ኃያላን በሆኑ አካላት በሕገወጥ እና በሕጋዊ መንገድ ሳይቀር እይተበዘበዘ በመሆኑ የተነሳ ሲሆን እነዚህ የአማዞን ሕዝቦች ከመሬታቸው ፍትሃዊ ተጠቃሚ ሳይሆኑ በከፍተኛ ድኽነት ወስጥ እንዲኖሩ በመገደዳቸው የተነሳ ነው።

ቅዱስነታቸው በእዚያው ተገኝተው ያደርጉት ንግግር እነዚህን ሐሳቦች ከግምት ያስገባ እና ለእነዚህ በድኽነት ለተጎሳቆሉ እና ለተገለሉ ሕዝቦች አጋርነታቸው ለመግለጽ፣ ድምጻቸውን ለዓለም ከፍ አድርጎ ለማሰማት፣ የሚመለከተው አካል ለእዚህ ውስብስብ ችግር መፍትሄ እንዲፈልግ ለማስቻል በማሰብ ያደርጉት ንግግር ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.