2018-01-19 11:12:00

ር. ሊ. ጳ. ፍራንቸስኮ በቺሊ ዋና ከተማ ሳንቲያጎ በሚገኘዋ ጳጳሳዊ ዩኒቬርሲቲ ከወጣቶች ጋር ተገናኝተው ተወያዩ


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በጥር 09/2010 ዓ.ም. በቺል ዋና ከተማ በሚገኘው የዛሬ 130 አመት  ገደማ በተቆረቆረው የካቶሊክ ዩኒቬርሲቲ ተገኝተው በእዚያ ከተሰበሰቡ ወጣት ተማሪዎች ጋር ቆይታ አድርገዋል። በእለቱ ቅዱስነታቸው ባደረጉት ንግግር እንደ ገለጹት ወጣቶች ከክርስቶስ ጋር ያቸውን ግንኙነት አጠናክረው በመቀጠል ለሀገራቸው እድገት እና ለውጥ የሚደረገውን ጥረት በቀዳሚነት መምራት እንደ ሚኖርባቸው ቅዱስነታቸው አሳስበዋል። 

ቅዱስነታቸው የሞባይል ስልክን በንጽጽር በመጠቀመ ባሰሙት ንግግር እንደ ገለጹት እኛ የሞባይል ስልኮቻችንን ሁል ጊዜ ከኔት ወርክ ጋር እንዲ ገናኙ እንደ ምንፈልግ ሁሉ እናንተ ወጣቶች በተመሳሳይ መልኩ የልባችውን ባትሪ መቀየር ከሚችለው ከክርስቶስ ጋር ሁል ጊዜ ተገናኝታችው መኖር ይገባችኃል በማለት ተናግረዋል።

በተለይም ደግሞ ወጣቶች በሀገራቸው ሁለንተናዊ ማሕበራዊ እድገት እንዲመጣ የበኩላቸውን ጥረት ማደርግ እንደ ሚጠበቅባቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው ወጣቶች ይህንን ለውጥ ልያስመዘግቡ የሚችሉት በቤተክርስቲያን አማካይነት ከክርስቶስ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በማጠናከር ሊሆን እንደ ሚገባም ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው ንግግራቸው ምጻራዊ በሆነ መልኩ የሞባይል ስልክ ጽንሰ ሐሳብ በተደጋጋሚ በንንጽር መጠቀማቸው የተገለጸ ሲሆን የሞባይል ስልካችን ባቲሪ ካለቀ የኢንተርኔት ግንኙነታችን እንደ ሚቋረጥ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ ክርስቶስ የሚያስተላልፍልንን መልእክቶች በአግባቡ መቀበል እንችል ዘንድ የሞተውን እምነታችንን መልሶ እንዲያንሰራራ ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል።

ከኢየሱስ ጋር ያለን ግንኙነት ከተቋረጠ ውስብስብ በሆኑ ሀሳቦች እና አመለካከቶች ውስጥ በመዘፈቅ ተስፋ ወደ መቁረጥ እና የመናደድ ስሜት በውስጣችን እንደ ሚያድር የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህም ስሜት ልባችውን በማሸበር አላስፈላጊ ወደ ሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ የወጣቶችን ሕይወት ሊከት ስለሚችል ወጣቶች ከክርስቶስ ጋር ያላቸውን ግንኙነት አጠናክረው መቀጠል እንደ ሚኖርባቸው ለወጣቶቹ ምክር አዘል መልእክት ካስተላለፉ በኃላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.