2018-01-15 15:19:00

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ከብራዚል (ከአንደኛው) እስከ ኩባ እና አሜሪካ (ዐስረኛው) ያደርጉት


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ከብራዚል (ከአንደኛው)  እስከ ኩባ እና አሜሪካ (ዐስረኛው) ያደርጉት ሐዋሪያዊ ጉዞ በአጭሩ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ከሚቀጥለው ሰኞ ማለትም ከጥር 7- 14/2010 ዓ.ም. ደረስ ለሰባት ቀናት ያህል ማለት ነው 22ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን ለማደረግ የላቲን አሜርካ ሀገራት ወደ ሆኑት ወደ ቺሊ እና ፐሩ እንደ ሚጓዙ ያታወቃል።

ይህንን የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ 22ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝት አስመልክተን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ከእዚህ ቀደም ያደርጓቸውን ሐዋሪያዊ ግቡኝቶች አጠር ባለ መልኩ እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እናጋብዛለን።

የእዚህን ዝግጅት ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

በትውልድ አርጄንቲናዊ የሆኑት ካርዲናል ጆርጅ ማሪዮ በርጎሊ በመጋቢት 13/2013 ዓ.ም. 266ኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው በተመረጡበት ወቅት በ13ኛው ክፍለ ዘመን የኖረው እና የድኾች አባት በመባል የሚታወቀው፣ እንዲሁም የፍራንችስካዊያን ማሕበር መስራች የነበረው ቅዱስ ፍራንቸስኮ፣ በሕይወቱ ዘመን ልድኾች ባሳየው ትህትና፣ክብር፣ ፍቅር እና ልገሳ እርሳቸው በጣም ከሚያደንቁዋቸው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቅዱሳን መካከል አንዱ በመሆኑ የተነሳ፣ እርሳቸውም ይህንን የቅዱስ ፍራንቸስኮን አብነት በመከተል በጵጵስናቸው ዘመን ለድኾች፣ ለስደተኞች፣ እንዲሁም በዝቅተኛ ደረጃ ለሚኖሩ የማሕበረሰብ ክፍሎች፣ በአጠቃላይ በዓለም ዙሪያ እኩልነት እና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ይሰፍን ዘንድ  በማሰብ የቅዱስ ፍራንቸስኮን ስም የጵጵስናቸው ዘመን መጠሪያ እንዲሆን በማድረግ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የሚለው መጠሪያቸው እንዲሆን መምረጣቸው ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከተመረጡ በኃላ በአራት አመት ውስጥ ብቻ ከጣሊያን ውጭ 21 ሐዋሪያው ጎብኝቶችን ማድረጋቸው የሚታወቅ ሲሆን በእነዚህ ሐዋሪያዊ ጎብኝታቸው ደግሞ በርካታ የካቶሊክ ምዕመናን ከሚገኙባችን የዓለማችን ክፍሎች አንስቶ እስከ 900 ያህል የካቶሊክ ምዕመናን ብቻ የሚገኙባትን አዘረበጃን ድረስ በመሄድ የሰላም እና የእርቅ መልእክታቸውን ማስተላለፋቸው ያታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከተመረጡ በኃላ ከጣሊያን ውጪ የመጀመሪያውን ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ብራዚል ነበር ያቀኑት።

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከሐምሌ 22-29/2013 ዓ.ም. ድረስ በብራዚል ዋና ከተማ ሬዮ ዲ ጄኔሪዮ  28ኛው የዓለም የካቶሊክ ወጣቶች ቀን በተከበረበት ወቅት የመጀመሪያውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን ለማድረግ ወደ ብራዚል ማቅናታቸው ይታወሳል። በጉብኝታቸውም ወቅት በወቅቱ የብራዚል ርዕሰ ብሔር በነበሩት በዲልማ ሩውሴፍ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን በወቅቱም በብራዚል ኮፓካባና በተባለው ሥፍራ በሚገኘው ወብ በሆነ የባሕር ዳርቻ አመሻሹ ላይ ለተሰበሰቡት 3.5 ሚልዮን ወጣቶች ባደርጉት የመጀመሪያው ንግግር ወጣቶች part-time Christains "ሲመቻቸው ብቻ ክርስቲያን የሚሆኑ/ ሳይመቻቸው ደግሞ ከቤተክርስቲያን የሚጠፉ” ወይም ደግሞ ገሚሱን ሕይወታቸውን ለዓለም ገሚሱን ደግሞ ለቤተክርስቲያን የሚሰጡ ክርስቲያኖች ዓይነት መሆን እንደ ሌለባቸው አሳስበው፣ ነገር ግን ወጣቶች ሙሉ ትርጉም ያለው ሕይወት እንዲመሩ አዳራ ማለታቸው ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ሁለተኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከግንቦት 24-26/2014 ዓ.ም. ድረስ ለማድረግ ወደ እስራኤል፣ ዮርዳኖስ እና ፍልስጤም ማቅናታቸው ይታወሳል። በእዚህም የሦስት ቀን ጉብኝታቸው ወቅት በቅድሚያ ከዮርዳኖስ  ከንጉሥ አብዱላህ ሁለተኛ ጋር ከተገናኙ በኃላ በአማን በሚገኘው ዓለም አቀፍ ስታዲዬም ለተሰበሰቡ ምዕመናን መስዋዕተ ቅዳሴን አሳርገዋል። ወደ እስራኤል በማቅናት ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስተር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋር ከተገናኙ በኃላ በምእራብ ጋዛ የሚገኘውን በተለያዩ የአሸባሪዎች ጥቃት ነብሳቸውን ያጡ ሰዎች የተቀበሩበትን የመታሰቢያ ሐውልት ጎብኚተዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸኮ ይህንን በእስራኤል፣ በዮርዳኖስ እና በፍልስጤም ያደርጉትን 2ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝት ያጠናቀቁት ከፓትሪያርክ ቤርቶሎሜዎስ ቀዳማዊ ጋር ከተገናኙ ቡኃላ ሲሆን በግንኙነታቸውም ወቅት በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ማለትም በኦሮዶክስ እና በካቶሊክ አብያተ ክርስቲያንት መካከል ያለውን ግንኙነት በውይይት ለማጠናካር ከተስማሙ በኃላ እንደ ነበረ ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ሦስተኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከሐምሌ 14-18/2014 ዓ.ም. ለማድረግ ወደ ድቡብ ኮሪያ ማቅናታቸው ይታወሳል።  ቅዱስነታቸው በደቡብ ኮሪያ እንደ ደረሱ በወቅቱ የሀገሪቷ ርዕሰ ብሔር በነበሩት ፓርክ ጌሁን-ሄይ ደማቅ የሆነ አቀባበል ተደርጎላቸው የነበረ ሲሆን በወቅቱ በሴዎል በሚገኘው ብሔራዊ ቤተመንግሥት ለተሰበሰቡ የሀገሪቷ ባለስልጣናት ባደረጉት ንግግር “እኔ ወደ ደቡብ ኮሪያ የመጣሁት በኮሪያን ባሕረ-ሰላጤ ሰላም እና ዕርቅ ይወርድ ዘንድ እንድታስቡ የበኩላችሁንም ጥረት እንድታደርጉ ነው” ብለው እንደ ነበረ የሚታወስ ሲሆን በእዚሁ የአምስት ቀናት ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸው በወቅቱ በሴዎል ይከበር በነበረው 6ኛው የኤሺያ አህጉር የካቶሊክ ወጣቶች ቀን ላይ መሳተፋቸው ይታወቃል። ከ50,000 በላይ የሚገመቱ ወጣቶች በተገኙበት ቅዱስነታቸው ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ወጣቶች “ድህነትን የሚያስከትሉ እና ሥራ አጥነትን የሚያባብሱ አዳዲስ ኢሰብዓዊ የሆኑ የኢኮኖሚ ጽንሰ-ሐሳቦችን መቃወም እንደ ሚገባቸው” አበክረው ማሳሰባቸው ያታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ አራተኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በመስከረም 21/2014 ዓ.ም ለማድረግ የአልባኒያ ዋና ከተማ ወደ ሆነችው ቲራና የአንድ ቀን ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ እዚያው ባቀኑበት ወቅት በአልባኒያው ርዕሰ ብሔር ቡጃር ኒሻኒ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸው እንደ ነበረ ይታወሳል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባደርጉት ንግግር "በዚህ አጠር ያለ ጉብኝት የአልባንያ ቤተክርስቲያንን በእምነት ለማጠናከር እና ሕዝቡ ባለፈው ስርዐቶች ወቅት ለነበረው ርዕዮተ ዓለማዊ አስተሳሰብ አልበግርም ማለቱን ለማድነቅ እና ለእዚሁም ምስክርነቴን ለመስጠት ነው እዚህ የተገኘሁት” ማለታቸው ያታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ አምስተኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በኅዳር 25/2014 ለማድረግ ወደ ፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ ማቅናታቸው ያታወሳል። በእዚያው በነበራቸው የአራት ሰዓት ቆያታ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ከእዚያም በኅዳር 25/2014 ዓ.ም. በወቅት በፈረንሳይ ስትራስቡርግ ተብሎ በሚጠራው ከተማ ይካሄድ የነበረውን የአውሮፓ ፓርላማ ስብሰባ ተካፍለው የነበረ ሲሆን በወቅቱም በእዚያው በአሮፓ ፓርላማ ጉባኤ ላይ ባደርጉትን ንግግር በስደተኞች ላይ የሚደርገው ኢሰባዊ ድርጊት እንዲቆም መስራት እንደ ሚገባቸው አበክረው ገልጸው ለሰራተኞች የተሻለ የሥራ ሁኔታ እንዲፈጥሩ እንዲሁም ሥራ አጥነትን ለመቀረፍ እንዲሰሩ ጥሪ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ስድስተኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን ለማድረግ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በኅዳር 28-30/2014 ዓ.ም ለማድረግ ወደ ቱርክ ዋና ከተማ እስታንቡል መሄዳቸው የሚታወቅ ሲሆን በእዚያም በቱርኩ ርዕሰ ብሔር ሴጵ ጣይፕ ሄርዶጋን በብሔራዊ ቤተመንግሥት ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ያታወሳል። በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ባደርጉት ንግግር ቱርክ የአክራሪነት ጽንሰ-ሐሳቦችን ለመቃወም በተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት መካከል ውይይት ይደረግ ዘንድ መንገዱን መክፈት እንደ ሚገባት መናገራቸው የታወቅ ሲሆን በተጨማሪም በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም የፈጠር ዘንድ ቱርክ የበኩሉዋን ሚና እንድትጫወት አደራ ማለታቸው ያታወሳል። ከእዚያም የቁስጢንጢንያው ፓትሪያርክ በርቴሌሞስ ቀዳማዊ በተገኙበት መስዋዕተ ቅዳሴን ካሳረጉ ቡኃላ ወደ ቫቲካን መመለሳቸው ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ስባተኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን ለማድረግ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከጥር 13-19 /2015 ዓ.ም. ሲሪላንካን እና ፊሊፒንስን በቅደም ተከተል ለመጎብኘት ወደ እዚያው ማቅናታቸው ይታወሳል። ከጥር 13-15/2015 ዓ.ም. በስሪላንካ ቆይታ ማደርጋቸው የሚታወስ ሲሆን በእዚያ የሚገኙትን በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያ ስም የተሰየሙትን ሁለት ታላላቅ የተቀደሱ የንግደት ሥፍራዎች መጎብኘታቸውም ያታወቃል። ቅዱስነታቸው በመቀጠል ወደ ፍሊፒንስ አቅንተው ነበር።ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ1970 በወቅቱ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ብጹዕ ጳውሎስ 6ኛ፣ በመቀጠልም ደግሞ አሁንም እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር 1981 ዓ.ም. እና 1995 ዓ.ም. በወቅቱ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ዩሐንስ ጳውሎስን ተከትለው በፍሊፒንስ ሐዋሪያዊ ጉብኝት ያደረጉ ሦስተኛው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው። ይህ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በፍሊፒንስ አድርገውት የነበረው ስድስተኛ ሐዋሪያዊ ጉብኝት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት በዓለም ዙሪያ እስካሁን ድረስ ከተደረጉት ሐዋሪያዊ ጉብኝቶች ሁሉ፣ ይህ እርሳቸው በፍሊፒንስ ያደርጉት ሐዋሪያዊ ጉብኝት በታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ስፍራን የሚሰጠው ሲሆን ይህም የሆነበት ምክንያት በወቅቱ እርሳቸው በማኒላ ያደርጉትን ንግግር እና ያሳረጉትን መስዋዕተ ቅዳሴ ለመከታተል ከ6-7 ሚልዮን የሚጠጋ ሕዝብ በስፍራው በመታደሙ የተነሳ ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ስምነትኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን ለማድረግ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በሰኔ 6/2015 ዓ.ም. ወደ  ቦሲኒያ ሄርዘጎቪና ማቅናታቸው ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘጠነኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከነሐሴ 5-13 /2015 ዓ.ም. ለማድረግ ወደ ቦሊቪያ፣ ኤኳዶር እና ፓራጉዋይ በቅደም ተከተል አቅንተው ነበር። በቅድሚያ በቦሊቪያ ባደርጉት ጉብኚት በርዕሰ ብሔሩ ሄቮ ሞራሌስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸው የነበረ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው ባደርጉት ንግግር መንግሥት ሙስናን እንዲዋጋ፣ ሁሉንም ዜጎች ተጠቃሚ ማድረግ የሚችል ኢኮኖሚያዊ ስርዓት እዲገነባ ጥረት እንዲያደርግ፣ ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠር እንዳለበት ቅዱስነታቸው ማሳሰባቸው ያታወሳል።

ቅዱስነታቸው በመቀጠልም በኤኳዶር ባደርጉት ጉብኝት በሀገሪቷ ርዕሰ ብሔር ራፋሔል ኮሬአ አቀባበል ተደርጎላቸው ነበር። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባደርጉት ንግግር “ኤኳዶር እያስመዘገበች ያላችውን ከፍተኛ  ኢኮኖሚያዊ እድገት እንደ ሚያደንቁ ገልጸው ሕገመንግሥታችሁ፣ የሁሉንም ዜጋ መብት የሚያስከብር፣ የተፍጥሮ ሐብት እንዲጠበቅ የሚያስገድድ የተለያዩ የሲቪል ማህበራት በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ እንዲሳተፉ የሚያበረታታ መሆኑን በማውሳት አድናቆታቸውን መግለጻቸው ያታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዐስረኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን እንደ ጎጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከመስከረም 19-27 /2015 ዓ.ም. ለማድረግ ወደ ኩባ እና ከእዚያም በመቀጠል ወደ አሜሪካ መጓዛቸው ይታወቃል። በኩባ ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር በሀቫና ቆይታ አድርገው የነበረ ሲሆን፣ በሀገሪቷ ከሚገኙ የካቶሊክ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመናን ጋር ተገናኝተው በጋራ ጸሎት ማድረጋቸው ይታወቃል።

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በመስከረም 23/2015 ዓ.ም. ወደ ዋሽንግተን ዲሲ በማቅናት በእዚያ በወቅቱ የአማሪካ ርዕሰ ብሔር ከነበሩት ባራክ ኦባማ ጋር በዋይት ሀውስ ተገናኝተዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዋይት ሀውስ ያደርጉት ጉብኝት ከእዚህ ቀደም እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር 1979 ዓ.ም. በወቅቱ የአሜርካ ርዕሰ ብሔር በነበሩት ጂሚ ካርተር እና በወቅቱ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት በነበሩት ዩሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ፣ ቀጥሎም ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር 2008 ዓ.ም. በወቅቱ የአሜርካ ርዕሰ ብሔር በነበሩት በጆርጅ ደብሊዩ ቡሽ እና በወቅቱ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት በነበሩት በነዲክት 16ኛ ጋር ከተደርገው ጉንኙነት በመቀጠል በሦስተኛነት ዋይት ሀውስ የጎበኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት መሆናቸውን ከታሪክ ለመረዳት ይቻላል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በወቅቱ በአሜሪካ ኮንግረስ ፊት በመቅረብ ንግግር ማድረጋቸው ያታወሳል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባደርጉት ንግግር እንደ ገለጹት የእናንተ ተግባር ልክ ሙሴ ለእስራኤላዊያን ሕዝብ ያደርገውን ዓይነት ተግባር እንዲሆን ይገባል ማለታቸው ይታወሳል። በመጀመሪያ ሙሴ የእስራኤልን ሕዝብ በበረሃ አንድነታቸውን ተጠብቆ፣ የሚበሉት እና የሚጠቱት እንዳያጡ ተንከባክቦ ወደ ተስፍይቱ ምድር እንደ መራቸው ሁሉ እናንተም በተመሳሳይ መንገድ ሕዝባችሁን በሙሉ በአንድነት እና በሰላም መምራት ይኖርባችኃል ብለው ነበር። በሁለተኛ ደረጃ ሙሴ የእስራኤልን ሕዝብ አንድነታቸው ተጠብቆ፣ የሚበሉት እና የሚጠቱት እንዳያጡ በመከባከብ ብቻ ሳይሆን ወደ ተስፋይቱ ምድር የመራቸው ነገር ግን በተመሳሳይ መልኩ ሕዝቡ ከእግዚኣብሔር ጋር የነበረው ግንኙነት እየጠነከረ እንዲሔድ ከፍተኛ ጥረት እንዳደረገ ሁሉ እናንተም ልክ እንደ ሙሴ ሕዝባችሁ ከእግዚኣቤሔር ጋር ያለው ግንኙነት እየጠነከረ ይሄድ ዘንድ ሁኔታዎችን ታመቻችሁ ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለሁ ማለታቸው ይታወሳል።

ቅዱስነታቸው በማግስቱ ማለትም በመስከረም 25/2015 ዓ.ም. በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጽሕፈት ቤት በመገኘት ንግግር ማድረጋቸው ይታወሳል። በወቅት ቅዱስነታቸው ባደርጉት ንግግር እንደ ገለጹት በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ላይ ያለው የኢኮኖሚ መዋቅር በጣም ብዙ የሚባሉ የዓለማችን ሀገራርትን ያገለለ እና ተጠቃሚ ያላደረገ መሆኑ እንደ ሚያሳስባቸው ገልጸው፣ በእዚህም ምክንያት ሕዝቦች ለሕገወጥ ዝውውር፣ የሰው ልጆች ክቡር የሆነ የአካል ክፍላቸው በሕገወጥ ሰዎች እንደ ሸቀጣሸቀጥ መሸጥ መጀመሩ፣ በሕጻናት ልጆች ላይ የሚደርገው ወሲባዊ ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ፣ ሰዎች ለአስገዳጅ እና ነጻ የጉልበት ሥራ መዳረጋቸው፣ ብዙ ሴቶች እህቶቻችን ለወሲብ ንግድ መዳረጋቸው፣ የአደንዛዥ ዕጽ ተጠቃሚ ወጣቶች መባራከታቸው፣ የጦር መሳሪያ ንግድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተፋፋመ መምጣቱ፣ አሸባሪዎች በዓለማችን ላይ የደቀኑት አደጋ እየበረከተ መሄዱ፣ የተቀናጀ ዓለማቀፍ ያዘት ያላቸው ወንጀሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መምጣታቸው እነዚህን እና እነዚህን የመሳሰሉ በርካታ ስጋቶች በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ላይ መደቀናቸውን አስታውሰው እዚህ የተሰበሰባችሁ የዓለም ሕዝብ ተወካዮች ለእነዚህ አንገብጋቢ ጉዳዮች አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ይኖርባችኃል በማለት መናገራቸው ያትወሳል።

 

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዐስራ አንደንደኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን እንደ ጎጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከኅዳር 25-30/2016 ዓ.ም. ለማድረግ ወደ ኬንያ፣ ኡጋንዳ እና የማካከለኛው የአፍሪካ ሪፖብልክ በቅደም ተከተል ለማድረግ ወደ እዚያው ማቅናታቸው ይታወሳል። ቅዱስነታቸው ይህንን ዕስራአንደኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኚት ለመጀመር በቅድሚያ ወደ ኬንያ ዋና ከተም ናይሮብ አቅንተው የነበረ ሲሆን የጆሞ ሌኒያታ ዓለማቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ እንድ እንደ ተገኙም በሀገሪቷ ርዕሰ ብሔር ኡሩ ኬኒያታ፣ በሀገሪቷ የሚገኙ ብጹዕን ጳጳሳት እና ምዕመናን ደማቅ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ቅዱስነታቸው በኬንያ ብሔራዊ ቤተመንግሥት ተገኝተው በእዚያው ለተሰበሰቡ የመንግሥት ባለሥልጣናት ባደረጉት የ11 ደቂቃ ንግግር መንግሥት ድህነት እንዲቀርፍ፣  እኩልነት እንዲያረጋግጥ፣ እርቅ፣ ሰላምና መረጋጋት ላይ ትኩረት በማድረግ በተለይም ለወጣቶች እና ለአከባቢ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እንዲሠራ እና አስፈላጊውን ጥረት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

በማግሥቱም በኅዳር 26/2016 ዓ.ም. ከተለያዩ የሐይማኖት ተወካዮች ጋር ተገናኝተው በተወያዩበት ወቅት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት በተለያዩ የሐያማኖት ተቋማት መካከል ውይይት ማድረግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን አስምረው ከገለጹ ቡኃላ ይህም አክራሪነትን ለመወጋት ከፍተኛ የሆነ ፍይዳ እንዳለውም ገልጸዋል። በመቀጠልም ቅዱስነታቸው 1.4 ሚልዮን የሚገመቱ ምዕመናን በተገኙበት መስዋዕተ ቅዳሴን ማሳረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በወቅቱም ባሳረጉት መሳዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት ኬኒያዊይን ቤተሰቦችን መደገፍ እንደ ሚገባ እና ሁሉንም ያካተተ የማኅበረሰብ ክፍል መመሥረት አስፈላጊ እንደ ሆነ ገለጸው በተለይም ደግሞ "በሰዎች ላይ የእብሪት ተግብራትን የሚያራምዱ፣ ሴቶችን የሚጎዳ ወይም ክብር የሚነሱ እንዲሁም የንጹህን ህፃናት ህይወትን አደጋ ላይ የሚጥሉ ድርጊቶችን መወጋት እንደ ሚገባቸው አበክረው ገለጸዋል።

በኅዳር 28/2016 ዓ.ም. ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በኬኒያ ያደርጉትን ቆይታ አጠናቀው ወደ ሁጋንዳ ማቅናታቸው የሚታወቅ ሲሆን እዚያም እንደ ደረሱ በሀገሪቷ ርዕሰ ብሔር በዮዌሪ ሙሴቪዬን፣ በሀገሪቱ በሚገኙ ብጹዕን ጳጳሳስት እና ምዕመናን ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸው ነበር። ቅዱስነታቸው በእዚያ በነበራቸው ቆይታ በቅድሚያ የጎበኙት በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የክርስትናን እምነት በመቀበላቸው የተነሳ ከእነ ሕይወታቸው የጠቃጠሉ 45 ሰማዕታት አጽም የሚገኝበትን የሙንዮንዮን  ሰምዕታት መተሳሰብያ ቅዱስ ስፍራ መጎብኘታቸው ያትወሳል። እነዚህን ሰማዕታት ለመዘከረ በማሰብ 1.5 ሚልዮን ምዕመናን በተገኙበት የመስዋዕተ ቅዳሴ ስነስርዐት የተካሄደ ሲሆን በእዚህ መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ የኡጋንዳው ርዕሰ ብሔር ዩሄሪ ሙሴቪዬኒ ተገኝተው ነበር። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት ኡጋንዳዊያን የእነዚህን 45 ሰምዕታት ለእመነታቸው የነበረቸውን ቅንዓት በመከተል "በዕድሜ የገፉ አዛውንቶችን፣ ድሆችን መበለቶችን እንዲሁም ጡዋሪ የሌላቸውን ሰዎች መንከባከባቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ቅዱስነታቸው በመጨረሻም ወደ መካከለኛው የአፍሪካ ሪፖብሊክ ዋና ከተማ ወደ ሆነችው ባንጉዊ ማቅናታቸው ያትወሳል። በወቅቱ የመካከለኛው የአፍሪካ ሪፖብሊክ በክርስቲያኖች እና በሙስሊም እመንት ተከታዮች መካከል ደም አፍሳሽ የሆነ ግጭት ተፈጥሮ ብዙዎችን ለስደት እና ለሞት የዳረግ ግጭት እንደ ነበረ የሚታወቅ ሲሆን ቅዱስነታቸውም የክርስቲያን እና የሙስሊም እምነት መሪዎችን በጋራ በአንድ ላይ አገናኝተው በማወያየት እርቅ ይፈጠር ዘንድ የበኩላቸውን አስተዋጾ ማድረጋቸው ያትወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በኅዳር 29/2008 ዓ.ም. ተጀመሮ በኅዳር 11/2009 ዓ.ም ላይ ከ349 ቀናት ቡኃላ የተጠናቀቀው ልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመት ያወጁትም ከእዚያው ከመካከለኛው የአፍሪካ ሪፖብሊክ ዋና ከተማ ባንጉዊ እንደ ሆነ የሚታወስ ሲሆን በእዚህም ለ349 ቀናት ያህል በቆየው ልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመት በመላው ዓለም በምትገኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ልዩ ልዩ መንፈሳዊና አካለዊ የምሕረት ተግባራትን በመፈጸም አክብረውት እንዳለፉ ያትወቃል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዐስራ ሁለተኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን እንደ ጎጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከየካቲት 12-18/2016 ዓ.ም. አቅንተዋል። ቅዱስነታቸው በእዚሁ ለስድስት ቀናት ያህል በሚቆየው ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸው ወቅት እገረ መንገዳቸውን በኩባ ዋና ከተማ ሀቫና ለአንድ ቀን ያህል ጎራ በማለት ከሞስኮና የመላው ሩስያ ፓትርያርክ ከሆኑት ፓትርያርክ ቄርሎስ ጋር በግል በመገናኘትና ከዝያም ወደ ሜክሲኮ ለማቅናት ጉዞ መጀመራቸው ይታውቋል። ይህንን ጉብኝት ታሪካዊ ነው ተብሉዋል። ይህንን ጉብኚታቸው ታሪካዊ ያሰኘው ደግሞ በሜክሲኮ የምያደርጉት የመጀመሪያው ጉብኝታቸው ሳይሆን ከሞስኩና የመላው ሩስያ ፓትርያርክ ቄርሎስ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ከዝህ በፊት በታሪክ ተከስቶ በማይታውቅ ሁኔታ ፊት ለፊት ተገናኝተው ለመንጋገር መወሰናቸውና ይህንንም እውን ለማድረግ ቀን ቆርጠው ለመገናኘትና ስለ ወደፊቱ በሁለቱ ታላላቅ አብያተ ክርስቲያንት መካከል ልኖር ስለ ምገባው መልካም ግንኙነት ለመነጋገርና አንድ የጋራ የአቋም ወይም መግለጫ ለማውጣት  መወሰናቸው ነው እንግዲህ ታሪካዊ የምያደረው።

እንደ ጉርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በየካቲት 14.2016 ቅዱስነታቸው በድኽነትና ከአደንዛዥ እፅ ዝውውር ጋር በተያያዘ ብጥብጥ እና ህውከት ወደ አልተለያት በሜክስኮ የምትገኘውን ኤካትፔክ ከተማ መጎብኘታቸው እና በእዚያም የአደንዛዢ እፅ አዛዋዋሪዎች በከፈቱት ጥቃት የተገደሉትን ዘጎች ለማስታወስ መገኘታቸው ያትወቃል። የቅዱስነታቸው በእዚህች በብጥበጥና በስርዓት አልበኝነት የተጎሳቆለችውን ከተማ ተገኝተው መጎብኘታቸው በእዚያ የምገኙትን በአብዛኛው በድኸነት ለተጎሳቆሉ የምህበረሰብ ከፍሎች ትልቅ ተስፋን የጫረባቸው እንደ ነበረ በወቅቱ ተገልጹዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዐስራ ሦስተኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን እንደ ጎጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በሚያዚያ 16/2016 ዓ.ም. ለማድረግ ወደ ግርክ ማቅናታቸው ያትወሳል። በእዚህም ጉብኝታቸው በግሪክ የወደብ ከተማ በሆነችው በሌስቦስ ተገኝተው በእዚያ የሚገኙትን በተለያዩ ምክንያቶች ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የተውጣጡ ስድተኞች ታጭቀው የሚገኙባትን የወደብ ከተማ መጎብኘታቸው የሚታወቅ ሲሆን፣ በጉብኚታቸውም ወቅት የዓለም መንግሥታት ለስደተኞች ቀውስ አስፈላጊውን ምላሽ በአስቸኩዋይ ይሰጥ ዘንድ ጥሪ ማቅረባቸው ያትወቃል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዐስራ አራተኛውን  ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን እንደ ጎጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከሰኔ 24-26/2016 ዓ.ም. ለማድረግ ወደ አርሜኒያ ማቅናታቸው ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዐስራ አምስተኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን እንደ ጎጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከነሐሴ 27-31/2016 ዓ.ም. ለማድረግ ወደ ፖላንድ ማቅናታቸው ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዐስራ ስድተኛ ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን እንደ ጎጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 2/2016 ዓ.ም. ለማድረግ ወደ ጆርጂያ እና አዘረበጃን በቅደም ተከተል ለማድረግ ማቅናታቸው ይታወሳል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ በጆርጂያ ዋና ከተማ በተብሊሲ ከምንግሥት ባለስልጣናት እና የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደ ገለጹት በእዚህች በተባረከች ምድር፣ በተለያዩ ባህሎች እና ስልጣኔውች የግንኙነት ቦታ በሆነችው እንዲሁም ከአራተኝው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በቅዱስ ኒኖ ተሰብካ ክርስትናን የተቀበልች እና የክርስትና እመነት ሥር መሰረት ያላት እና ጠንካራ የእመንት መሰረት ባላት ሀገር በመገኘተ እግዚኣብሔርን አመሰግናለሁ።

ቅዱስ ጳውሎስ ሁለተኛ ሀገራችሁን ከጎበኙ ቡኋላ “የጆርጂያን ባሕል እንደ አበባ እንዲፈካ ያደረገው ዘረ ክርስትና መሆኑን” ታዝበው ነበር ይህም ዘረ ፍሬያማ መሆኑን ቀጥሉዋል። ባለፈው ዓመት ክቡር ፕሬዝዳንት በቫቲካን ያደረጉትን ግንኙነት ወቅት ከጆርጂያ ጋር የቅድስት መንበር ያላትን መልካም ግንኙነት የሚያጠናክር በመሆኑ እና ይህም ግንኙነት ቀጣይ እንዲሆን በማሰብ በጆርጂያ ሕዝብ እና ባለስልጣናት ስም ክቡር ፕሬዚደንቱ  እዚህ እንድመጣ ስለጋበዙኝ ከልብ ላመሰግኖት እወዳለሁ ማለታቸው ያትወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዐስራ ሰባተኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን እንደ ጎጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከጥቅምት 31- እስከ ኅዳር 1/2016 ዓ.ም. ለማድረግ ወደ ሲዊድን ማቅናታቸው ይታወሳል።

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.