2018-01-15 16:01:00

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ከ11ኛው እስከ 21ኛው ያደረጉት ሐዋሪያዊ ጉዞ በአጭሩ


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ከ11ኛው እስከ 21ኛው ያደረጉት ሐዋሪያዊ ጉዞ በአጭሩ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ 11ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከኅዳር 25-30/2016 ዓ.ም. ወደ ኬንያ፣ ኡጋንዳ እና የማካከለኛው የአፍሪካ ሪፖብልክ በቅደም ተከተል ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ እዚያው ማቅናታቸው ይታወሳል። ቅዱስነታቸው ይህንን 11ኛውን  ሐዋሪያዊ ጉብኚት ለመጀመር በቅድሚያ ወደ ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮብ አቅንተው የነበረ ሲሆን የጆሞ ኬኒያታ ዓለማቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ እንደ ደረሱም በሀገሪቷ ርዕሰ ብሔር ኡሩ ኬኒያታ፣ በሀገሪቷ የሚገኙ ብጹዕን ጳጳሳት እና ምዕመናን ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ቅዱስነታቸው በኬንያ ብሔራዊ ቤተመንግሥት ተገኝተው በእዚያው ለተሰበሰቡ የመንግሥት ባለሥልጣናት ባደረጉት የ11 ደቂቃ ንግግር መንግሥት ድኽነት እንዲቀርፍ፣  እኩልነት እንዲረጋገጥ፣ እርቅ፣ ሰላምና መረጋጋት ላይ ትኩረት በማድረግ በተለይም ለወጣቶች እና ለአከባቢ ጥበቃ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እንዲሠራ እና አስፈላጊውን ጥረት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበው ነበር።

የእዚህን ዝግጅት ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

በማግሥቱም በኅዳር 26/2016 ዓ.ም. ከተለያዩ የሐይማኖት ተወካዮች ጋር ተገናኝተው በተወያዩበት ወቅት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት በተለያዩ የሐያማኖት ተቋማት መካከል ውይይት ማድረግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን አስምረው ከገለጹ በኃላ ይህም አክራሪነትን ለመወጋት ከፍተኛ የሆነ ፍይዳ እንዳለውም ገልጸዋል። በመቀጠልም ቅዱስነታቸው 1.4 ሚልዮን የሚገመቱ ምዕመናን በተገኙበት መስዋዕተ ቅዳሴን ማሳረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በወቅቱም ባሳረጉት መሳዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት “ኬኒያዊይን ቤተሰስ የመደገፍ ልማዳቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ እና ሁሉንም ያካተተ የማኅበረሰብ ክፍል መገንባት አስፈላጊ እንደ ሆነ” ገለጸው በተለይም ደግሞ "በሰዎች ላይ የእብሪት ተግባራትን የሚያራምዱ፣ ሴቶችን የሚጎዳ ወይም ክብር የሚነሱ እንዲሁም የንጹሃን ህፃናት ህይወት አደጋ ላይ የሚጥሉ ድርጊቶችን መወጋት እንደ ሚገባቸው” አበክረው መገልጻቸው ያትወሳል።

በኅዳር 28/2016 ዓ.ም. ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በኬኒያ ያደርጉትን ቆይታ አጠናቀው ወደ ሁጋንዳ ማቅናታቸው የሚታወቅ ሲሆን እዚያም እንደ ደረሱ በሀገሪቷ ርዕሰ ብሔር በዮዌሪ ሙሴቪዬኒ፣ በሀገሪቱ በሚገኙ ብጹዕን ጳጳሳት እና ምዕመናን ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸው ነበር። ቅዱስነታቸው በእዚያ በነበራቸው ቆይታ በቅድሚያ የጎበኙት በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የክርስትናን እምነት በመቀበላቸው የተነሳ ከእነሕይወታቸው የጠቃጠሉ 45 ሰማዕታት አጽም የሚገኝበትን የሙንዮንዮን  ሰምዕታት መታሰብያ ቅዱስ ስፍራ መጎብኘታቸው ይታወሳል። እነዚህን ሰማዕታት ለመዘከረ በማሰብ 1.5 ሚልዮን ምዕመናን በተገኙበት የመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስርዐት የተካሄደ ሲሆን በእዚህ መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ የኡጋንዳው ርዕሰ ብሔር ዩሄሪ ሙሴቪዬኒ ተገኝተው ነበር። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት ኡጋንዳዊያን የእነዚህን 45 ሰምዕታት ለእመነታቸው የነበረቸውን ቅንዓት በመከተል "በዕድሜ የገፉ አዛውንቶችን፣ ድሆችን፣ መበለቶችን እንዲሁም ጡዋሪ የሌላቸውን ሰዎች መንከባከባቸውን እንዲቀጥሉ” ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ቅዱስነታቸው በመጨረሻም ወደ መካከለኛው የአፍሪካ ሪፖብሊክ ዋና ከተማ ወደ ሆነችው ባንጉዊ ማቅናታቸው ይታወሳል። በወቅቱ የመካከለኛው የአፍሪካ ሪፖብሊክ በክርስቲያኖች እና በሙስሊም እመንት ተከታዮች መካከል ደም አፍሳሽ የሆነ ግጭት ተፈጥሮ ብዙዎችን ለስደት እና ለሞት የዳረግ ግጭት እንደ ነበረ የሚታወቅ ሲሆን ቅዱስነታቸውም የክርስቲያን እና የሙስሊም እምነት መሪዎችን በጋራ በአንድ ላይ አገናኝተው በማወያየት እርቅ ይፈጠር ዘንድ የበኩላቸውን አስተዋጾ ማድረጋቸው ያትወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በኅዳር 29/2008 ዓ.ም. ተጀመሮ በኅዳር 11/2009 ዓ.ም ላይ ከ349 ቀናት በኃላ የተጠናቀቀውን ልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመት ያወጁትም ከእዚያው ከመካከለኛው የአፍሪካ ሪፖብሊክ ዋና ከተማ ባንጉዊ እንደ ሆነ የሚታወስ ሲሆን በእዚህም ለ349 ቀናት ያህል በቆየው ልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመት በመላው ዓለም በምትገኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ልዩ ልዩ መንፈሳዊና አካለዊ የምሕረት ተግባራትን በመፈጸም አክብረውት እንዳለፉ ይታወቃል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዐስራ ሁለተኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን እንደ ጎጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከየካቲት 12-18/2016 ዓ.ም. ለማድረግ ወደ ሜክሲኮ ማቅናታቸው ያትወሳል። ቅዱስነታቸው በእዚሁ ለስድስት ቀናት ያህል በሚቆየው ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸው ወቅት እገረ መንገዳቸውን በኩባ ዋና ከተማ ሀቫና ለአንድ ቀን ያህል ጎራ በማለት ከሞስኮና የመላው ሩስያ ፓትርያርክ ከሆኑት ፓትርያርክ ቄርሎስ ጋር በግል በመገናኘትና ከዝያም ወደ ሜክሲኮ ለማቅናት ጉዞ መጀመራቸው ይታወሳል። ይህ ጉብኝት ታሪካዊ ነው ተብሎ ነበር። ይህንን ጉብኝታቸው ታሪካዊ ያሰኘው ደግሞ በሜክሲኮ የምያደርጉት የመጀመሪያው ጉብኝት ሳይሆን ከሞስኩና የመላው ሩስያ ፓትርያርክ ቄርሎስ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ከእዚህ በፊት በታሪክ ተከስቶ በማይታውቅ ሁኔታ (አንድ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና አንድ የሞስኮ እና የመላው ራሻ ፓትሪያርክ በታሪክ አጋጣሚ በቀጥታ ተገናኝተው አያውቁም) ፊት ለፊት ተገናኝተው ለመንጋገር መወሰናቸውና፣ ይህንንም እውን ለማድረግ ቀን ቆርጠው ለመገናኘትና ስለ የወደ ፊቱ በሁለቱ ታላላቅ አብያተ ክርስቲያንት መካከል ልኖር ስለ ምገባው መልካም ግንኙነት ለመነጋገርና አንድ የጋራ የአቋም ወይም መግለጫ ለማውጣት  መወሰናቸው ነው እንግዲህ ይህንን ግንኙነት ታሪካዊ የምያደረው።

እንደ ጉርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በየካቲት 14.2016 ቅዱስነታቸው በድኽነትና ከአደንዛዥ እፅ ዝውውር ጋር በተያያዘ ብጥብጥ እና ሁከት ወደ አልተለያት በሜክስኮ የምትገኘውን ኤካትፔክ ከተማ መጎብኘታቸው እና በእዚያም የአደንዛዢ እፅ አዛዋዋሪዎች በከፈቱት ጥቃት የተገደሉትን ዘጎች ለማስታወስ መገኘታቸው ያትወቃል። የቅዱስነታቸው በእዚህች በብጥብጥና በስርዓት አልበኝነት በተጎሳቆለችው ከተማ ተገኝተው መጎብኘታቸው በእዚያ የምገኙትን በአብዛኛው በድኸነት ለተጎሳቆሉ የማኅበረሰብ ከፍሎች ትልቅ ተስፋን የጫረባቸው እንደ ነበረ በወቅቱ ተገልጹዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ 13ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በሚያዚያ 16/2016 ዓ.ም. ለማድረግ ወደ ግሪክ ማቅናታቸው ይታወሳል። በእዚህም ጉብኝታቸው በግሪክ የወደብ ከተማ በሆነችው በሌስቦስ ተገኝተው በእዚያ የሚገኙትን በተለያዩ ምክንያቶች ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የተውጣጡ ስድተኞች ታጭቀው የሚገኙባትን የወደብ ከተማ መጎብኘታቸው የሚታወቅ ሲሆን፣ በጉብኝታቸውም ወቅት የዓለም መንግሥታት ለስደተኞች ቀውስ አስፈላጊውን ምላሽ በአስቸኩዋይ ይሰጡ ዘንድ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወቃል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ 14ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን እንደ ጎጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከሰኔ 24-26/2016 ዓ.ም. ለማድረግ ወደ አርሜኒያ ማቅናታቸው ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ 15ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከነሐሴ 27-31/2016 ዓ.ም. ለማድረግ ወደ ፖላንድ ማቅናታቸው ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ 16ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 2/2016 ዓ.ም. ለማድረግ ወደ ጆርጂያ እና አዘረበጃን በቅደም ተከተል  ማቅናታቸው ይታወሳል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ በጆርጂያ ዋና ከተማ በተብሊሲ ከምንግሥት ባለስልጣናት እና የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደ ገለጹት “በእዚህች በተባረከች ምድር፣ በተለያዩ ባህሎች እና ስልጣኔዎች የግንኙነት ቦታ በሆነችው እንዲሁም ከአራተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በቅዱስ ኒኖ ተሰብካ ክርስትናን የተቀበለች እና የክርስትና እመነት ሥር መሰረት ያላት እና ጠንካራ የእመንት መሰረት ባላት ሀገር በመገኘተ እግዚኣብሔርን አመሰግናለሁ” ብለው እንደ ነበረ ይታወሳል።

“ቅዱስ ጳውሎስ ሁለተኛ ሀገራችሁን ከጎበኙ በኋላ “የጆርጂያን ባሕል እንደ አበባ እንዲፈካ ያደረገው ዘር ክርስትና መሆኑን” ታዝበው ነበር ይህም ዘር ፍሬያማ መሆኑን ቀጥሉዋል። ባለፈው ዓመት ክቡር ፕሬዝዳንት በቫቲካን ያደረጉትን ግንኙነት ወቅት ከጆርጂያ ጋር የቅድስት መንበር ያላትን መልካም ግንኙነት የሚያጠናክር በመሆኑ እና ይህም ግንኙነት ቀጣይ እንዲሆን በማሰብ በጆርጂያ ሕዝብ እና ባለስልጣናት ስም ክቡር ፕሬዚደንቱ  እዚህ እንድመጣ ስለጋበዙኝ ከልብ ላመሰግኖት እወዳለሁ” ማለታቸው ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ 17ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከጥቅምት 31- እስከ ኅዳር 1/2016 ዓ.ም. ለማድረግ ወደ ሲዊድን ማቅናታቸው ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ 18ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለማደርግ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በሚያዝያ 28 ወደ ግብፅ ማቅናታቸው ይታወሳል። የዚህ የቅዱነታቸው 18ኛው ሐዋሪያዊ ጉብኝት ዋንኛው ዓላማ በታላቁ በአል ዐዛር የእስልምና ማዕከል ዳይሬክተር ኢማም ሼህ አምድ አል ጣይብ፣ የግብፅ ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት የሆኑት አብደል ፋታህ ሳሂድ ሁሴን ካሊል አል ሲሲ እንዲሁም የአጠቃላዩን የግብጽ ሕዝብ 30% የሚወክሉት የግብፅ የኮፕት የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ሊቃነ ጳጳሳት የሆኑት ፓትሪያርክ ቴውድሮስ ዳግማዊ ባቀረቡላቸው ግብዣ ምክንያት እንደ ሆነ የታወቀ ሲሆን በተጨማሪም በዚህ ጉብኝታቸው እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በ969 ዓ.ም. መቆርቆሩ የሚነገርለት የአል ዐዛር የእስልምና ማዕከል ባዘጋጀው ዓለማቀፍ የሰላም ጉባሄ ላይ ተገኝተው ንግግር ማድረጋቸውን መዘገባችን ያትወሳል።

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በግንቦት 12/2017 ዓ.ም. ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮ 19ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለማድረግ በፖርቹጋል ሀገር ፋጢማ በሚባል ልዩ ስፍራ የሚገኘውን እና የዛሬው 100 አመት ገደማ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በወቅት እረኛ ለነበሩ 3 ሕጻናት የተገለጸችበት ሥፍራ የሚገኘውን የፋጢማ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማሪያም ቤተ መቅደስ ለመሳለም ወደ እዚያው መሄዳቸው ይታወቃል። ቅዱስነታቸው በዚህ መንፈሳዊ ጉዞዋቸው ለማሪያም ያላቸውን ፍቅር እና እምነት በመግለጽ ለእመቤታችን ቅድስት ማሪያም የግል ጸሎታቸውን ያቀረቡበት ወቅት እንደ ነበረም መዘገባችን ያትወሳል።

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከመስከረም 06-11/2017 ዓ.ም.  ደረስ በኮሎንቢያ 20ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን ለምድረግ ወደ ኮሎንቢያ ማቅናታቸው ይታወሳል።

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከሕዳር 26-ታኅሳስ 2/2017 ዓ.ም. ድረስ በማያንማር (የቀደሞ ስሟ በርማ)እና በባንላዲሽ  ሐዋሪያዊ ጉብኝት አድርገዋል። ማያንማር 54.4 ሚልዮን ሕዝብ ብዛት ያላት ሀገር ስትሆን በጣም በቁጥር አነስተኛ የሆኑ የካቶሊክ ምዕመናን የሚገኙባት ሀገር ናት።  

በማያን ማር ያደርጉት ሐዋሪያዊ ጉብኝት “የሰላም ልዑክ” በሚል መሪ ቃል ያነገበ እንደ ነበረ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በመቀጠልም ቅዱስነታቸው በባንግላዲሽ አድርገውት ለነበረው 21ኛ ሐዋሪያዊ ጉብኝት ደግሞ የመረጡት መሪ ቃል “ሰላም እና ሕብረት” የሚል መሪ ቃል ያነገበ ነበር። ባንግላዲሽ 166 ሚሎዮን የሕዝብ ብዛት ያላት ሀገር ናት። ከጠቃላይ የሕዝብ ብዛቷ ውስጥ 350,000 የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ሲሆኑ ይህም በመቶኛ ሲሰላ 0.24 % የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ናቸው። አብዛኛው የባንግላዲሽ ሕዝብ የሙስሊም እምነት ተከታትይ ሲሆን፣ የቡዳ እና የሌሎች ባሕላዊ እመንት ተከታዮችን መኖሪያ ናት ባንግልዲሽ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከጥር 15-22 ዓ.ም 22ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን ለማድረግ የደቡባዊ አሜሪካ ሀገራት ቺሊ እና ፐሩ አቅንተዋል።

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.