2018-01-03 16:16:00

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ያደረጉትን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች በተላያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። የዚሁ መርሃ ግብር አንዱ አካል በሆነው በዛሬው እለት ማለትም በጥር 25/2010 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ አዳራሽ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች ያደረጉት የጠቅላላ አስተምህሮ ቀደም ሲል ባለፉት ሳምንታት በመስዋዕተ ቅዳሴ ዙሪያ አድርገውት የነበረ አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን በዛሬው እለት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮዋቸው  ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች በጻፈው 1ቆሮ. 10፡15-17 ላይ በተጠቀሰው “ይህን የምናገረው አስተዋይ ለሆኑ ሰዎች ነው፤ ስለምናገረው ነገር እናንተው ፍረዱ። የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቈርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? እንጀራው አንድ እንደሆነ፣ እኛም ብዙዎች ሆነን ሳለ አንድ አካል ነን፤ ሁላችን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና” በሚለው ጥቅስ ላይ መሰረቱን ያደርገ እንደ ነበረ ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅታችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ያደረጉትን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ከእዚህ ቀደም በመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ዙሪያ ጀምሬው የነበረውን የትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመቀጠል በዛሬው እለት ደግሞ  የመስዋዕተ ቅዳሴ በመግቢያ ሥነ-ስርዓት ውስጥ የሚገኘውን  የኑዛዜ ጸሎት  በተመለከት መናገር እፈልጋለሁ። ይህ የኑዛዜ ጸሎት በራሱ ቅዱስ በመሆኑ የተነሳ እኛም ይህንን ቅዱስ የሆነ ምስጢር ተገቢ በሆነ መልኩ ለመካፈል እንችል ዘንድ በእግዚአብሔርና በወንድሞቻችን ላይ የፈጸምነውን ኃጢአቶች በሚገባ ማስተዋል እንችል ዘንድ ይረዳናል። በእርግጥ ካህኑ በዚያው በመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ላይ ለተሳተፉ በጸሎት መንፈስ ውስጥ ለሚገኙ  ምዕመናኖች ሁሉ የሚያቀረበው ግብዣ ሲሆን፣ ይህም የሚሆንበት ምክንያት ሁላችንም ኃጢያተኞች በመሆናችን የተነሳ ነው። ልባቸው በራስ ወዳድነት መንፈስ እና የራሳቸውን እርካት በመፈለግ ለተሞላ ሰዎች ጌታ ምን ዓይነት ስጦታ መስጠት ይችል ይሆን? ምንም ዓይነት ስጦታ ሊሰጥ አይችልም! ምክንያቱም ልባቸውን የሞላው ትዕቢት ይቅርታን ማግኘት የማያስችል በመሆኑ የተነሳ። እስቲ ስለ ፈሪሳዊው እና ስለ ቀራጩ  ሰው ምሳሌ ለአፍታ ያህል እናስብ፣ ቀራጭ የነበረው ሰው ይቅርታን አግኝቶ እና ኃጢአቱ ይቅር ተብሎለት በደስታ ወደ ቤቱ ሲመለስ እናያለን (ሉቃስ 189-14) የራሳቸውን አሳር በሚገባ ጠንቅቀው የሚያውቁ እና ዓይኖቻቸውን በትሕትና ዝቅ የሚያደርጉ ሰዎች ሁሉ መሐሪ የሆነው የእግዚኣብሔር እይታ በእነርሱ ላይ እንደ ሆነ ይሰማቸዋል። ከልምዳችን እንደ ምንረዳው ስህተቱን በሚገባ ለይቶ ያወቀ እና ለእዚነዚህም ስህተቶች ይቅርታን የጠየቀ ሰው ብቻ የቅርታን ያገኛል ሌሎችንም ይቅር ይላል።

በዝምታ የሕሊናችንን ድምጽ በምናዳምጥበት ወቅት ሐሳባችን ከመለኮታዊ ሃሳቦች በጣም የራቀ መሆኑን  እንድገነዘብ፣ ቃላቶቻችን እና ድርጊቶቻችን በአብዛኛው ተለምዷዊ ማለትም ከቅዱስ ወንጌል ተቃራኒ በሆኑ አማራጮች የሚመራ መሆኑን እንድንገነዘብ ያስችለናል። ስለዚህ በመስዋዕተ ቅዳሴ መግቢያ ወይም መጀመሪያ ላይ ሁላችንም  ወጥ በሆነ መልኩ  የኑዛዜ ጸሎት በአንድነት፣ ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው በግሉ ይህንን ጸሎት መድገም ይጀምራል። እያንዳንዱ ሰውበማሰብ፣ በማድረግ፣ በመናገር ተግባሬን ባለመፈጸም ብዙ ኃጢአት መሠራቴን እናዘዛለሁ!” በማለት በእግዚኣብሔር እና በወንድሞቹ ላይ ስለፈጸመው በደል ይቅርታን ይጠይቃል። አዎ! መልካም ነገር መሥራት እየቻልን ቸል ማለታችን በራሱ ኃጢአት ነው። ብዙውን ጊዜማንም ሰው አልጎዳሁምየሚል ጥሩ ስሜት እየተሰማን ራሳችንን በራሳችን ጥሩ ሰዎች አድርገን እንቆጥራለን። በተጨባጭ በባልንጀሮቻችን ላይ ከፉ ነገር አለመሥራት በራሱ በቂ አይደለም፣ ነገር ግን የአንዱ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙር  መሆናችንን ለመመሥከር መልካም እድሎችን በመውሰድ መልካም ለማድረግ መጣር ይኖርብናል። ለእግዚአብሔር እና ለወንድሞቻችን ኃጢያተኞች መሆናችንን መናዘዝን በራሱ መልካም ነው፡ ይህ ኃጢአት እኛን ከእግዚአብሔር እና ከወንድሞቻችንም ዘንድ ሳይቀር እንደ ሚለያየን፣ በተቃራኒውም እግዚኣብሔር እና ወንድሞቻችን ከእኛ እንዲለዩ እንደ ሚያደርግ እንድንገነዘብ ይረዳናል።

በአፋችን ከምንናገራቸው ቃላት ጋር መሳ ለመሳ ደረታችንን በእጃችን እየመታንበእኔ ክፋት፣ በእኔ ብዙ ክፋት እያልን በምንጸልይበት ወቅት የሠራነው ኃጢአት በሌሎች ጥፋት ሳይሆን በራሳችን ጥፋት መሆኑን እናረጋግጣለን። ብዙውን ጊዜ በፍርሃትና በሀፍረት ስሜቶች የተነሳ ሌሎችን ለመወንጀል ጣታችንን ወደ ሌሎች የምንቀስርበት አጋጣሚዎች ይፈጠራሉ። የጥፋተኛነት ስሜት እንዳለን ተረድተን በቅንነት መናዘዝ ያስፈልጋል።

ኃጢአቶቻችንን  ከተናዘዝን ቡኃላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያምን፣ መልአክትን እና የቅዱሳንን ሱታፌ በመማጸን ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ እንዲያማልዱን እንለምናለን ወይም እንማጸናለን። በዚህም ውብ የሆነውን የቅዱሳን አንድነት እንገልጻለን፣ የእነዚህ ወዳጆቻችን የሆኑ እና መልካም የሕይወት አብነት ያሳዩንን ቅዱሳን አማላጅነት እንማጸናለን፣ ይህም ሕይወታችንን ባዶ ያደረገውን ኃጢአት ወደ ጎን በመተው ወደ እግዚኣብሔር የምናደርገውን ጉዞ በብርታት እንድናከናውን ያግዘናል።

ይህ የኑዛዜ ጸሎት የሚደመደመው ካህኑ በሚሰጠው ፍትሀት ሲሆን ይህምሁሉን የሚችል እጊኣብሔር በምሕረቱ ኃጢአታችንን ይቅር ብሎ ወደ ዘላለማዊ ሕይወት ያግባንበማለት ካህኑ ይጸልያል።   የእዚህ ዓይነቱ የፍትኃት ጸሎትምስጢረ ንስሐ ያለውን ዓይነት ዋጋ በተመሳሳይ መልኩ የለውም” (General Instruction of the Roman Missal, 51) በእግርጥ በጣም ከባድ የሚባሉ ኃጢአቶች አሉ፣ በጣም ከባድ የሆኑና በውስጣችን የሚገኘውን መለኮታዊ ሕይወት እንዲሞት የሚያደርጉ ኃጢአቶችም አሉ፣ እነዚህን እና እነዚህን ከመሳሰሉ ኃጢአቶች ለመፈወስ የግድ ምስጢረ ንስኃ ማድረግ እና የእዚህን ምስጢር ፍትሃት መቀበል ይኖርብናል።

መጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ኃጢአትን ከፈጸሙ በኋላ ወደ እግዚኣብሔር የተመለሱ፣ ራሳቸውን በመክፈት የእርሱን ፀጋ ወደ ውስጣቸው ለማስገባት ድፍረቱን ያገኙ እና "ልባቸው እንዲታደስ" ያደረጉ ሰዎች ተምሳሌት በብዛት ያቀርብልናል። በመዝሙረ ዳዊት ውስጥ የተጠቀሰውንእግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ቸርነትህ መጠን፣ ምሕረት አድርግልኝ፤ እንደ ርኅራኄህም ብዛት፣ መተላለፌን ደምስስ” (መዝሙር 511.2) የሚለውን የንጉሥ ዳዊትን ቃላትን ልብ እንበል ጠፍቶ የተገኘው ልጅ ምሳሌን እንመልከት፣ ወይም ደግሞ  በሉቃስ ወንጌል 1813 ላይ የተጠቀሰውንቀረጥ ሰብሳቢው ግን በርቀት ቆሞ፣ ወደ ሰማይ ቀና ብሎ ማየት እንኳ አልፈለገም፤ ነገር ግን ደረቱን እየደቃ፣እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔን ኀጢአተኛውን ማረኝይል ነበርየሚለውን እንመልከት። የቅዱስ ጴጥሮስን፣ የዘኪዎስን፣ የሳምራዊቷን ሴት ታሪክ እንመልከት። የእነዚህ ሰዎች ታሪክ ተሰባሪ እና  የእጁ ሥራዎች መሆናችንን በመገንዘብ እኛ እንድንጠነክር የሚያደርገን ተመክሮ ነው። ድክመቶቻችንን እያሰላን የሚቀይረንን እና መንፈሳዊ ለውጥ የሚያስገኘውን የእግዚኣብሔር መለኮታዊ ምሕረት ለጠየቅ እንድንችል  ልባችንን ይከፍትልናል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.