2018-01-01 16:41:00

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በተገባደደው 2017 ዓ.ም ያደርጉት አበይት ክንውኖች በአጭሩ


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ እንደ ጎግርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በተገባደደው 2017 ዓ.ም ያደርጉት አበይት ክንውን እና ሐዋሪያው ጎዞ በአጭሩ

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የዓለማችን የማኅበረሰብ ክፍሎች ዘንድ 2018 ዓ.ም አዲስ አመት በይፍ ተጀምሯል። በዚሁ አጋጣሚ የጎርጎራሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉት ሀገራት ውስጥ የሚኖሩ አድማጮቻችን እንኳን ለ2018 ዓ.ም አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን።

የዚህን ዝግጅት ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

በማስከተል ይህንኑ የጎጎሮሳዊያኑን 2017 ዓ.ም. ማለቅያን እና 2018 ዓ.ም. አዲስ አመት መጀመሩን ምክንያት በማድረግ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ እየተገባደደው 2017 ዓ.ም. ያከናወኑዋቸውን አብይት ተግባራት እና በሮም እና በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ያደረጉትን ሐዋሪያዊ ጉዞ ከዚህ በመቀጠል አጠር ባለ መልኩ እናቀርብላችኃለን አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን እንጋብዛለን።

የጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር 2017 ዓ.ም. ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሮም እና በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ያከናወኑበት፣ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ሐዋሪያዊ ጉብኝት ያደርጉበት፣ በተለይም በመካከለኛው የጣሊያን ግዛት ተከስቶ በነበረው ርዕደ መሬት ምክንያት የተጎዱ አከባቢዎችን የጎበኙበት፣ የኒውክለር የጦር መሳሪያ ለዓለማችን በአጣም አደገኛ በመሆኑ የተነሳ ይህንን የኒውክለር የጦር መሳሪያ የታጠቁ ሀገራት ይህንን አደገኛ መሳሪያ እንዲያስወግዱ ጥሪ ያደርጉበት፣ ያወገዙበት፣ በአውሮጳ ውስጥ ከሚገኙ መሪዎች ጋር ተገኛኝተው በተለያዩ የዓለማችን ጉዳዮች ላይ የተወያዩበት፣ ከአሜርካው ርዕሰ ብሔር ዶናልድ ትራፕም ጋር በቫትካን የተገናኙበት፣ እንዲሁም የፍልስጤም ርዕሰ ብሔር ከሆኑት ሙሃሙድ አባስ ጋር በቫቲካን ተገናኝተው ስለ ሰላም የተወያዩበት፣ አመት በመሆን ተጠንቋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በጥር 5/2017 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከ7ሺ በላይ ሰዎች በተገኙበት ንግግር አድርገው ነበር። ለእነዚህ ላዚዮ፣ ኡብሪያ እና ማርኬ ከተባሉ የጣሊያን ክፍለ ሀገራት የተውጣጡ ሰዎች እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በጥቅምት ወር በጣሊያን ተከስቶ በነበረው ርዕደ መሬት ወዳጅ ዘመዶቻችውን እና ንብረቶቻቸውንም ሳይቀር በዚሁ የተፈጥሮ አደጋ ያጡ ሰዎች ነብሩ። በእለቱ ቅዱስነታቸው “ርዕደ መሬት የተፈጥሮ ክስተት እንደ ሆነ ጠቅሰው ምድራችንም ወጣ ገባ ሆና፣ የምያምሩ ተራሮች እና ሸንትረሮችን ምድራችን እንዲኖራት ያደርገው ይህ የተፈጥሮ ክስተት ወይም ርዕደ መሬት እንደ ሆነ” ገልጸው፣ “ነገር ግን በዚሁ የተፍጥሮ ሂደት ምክንያት በሰው ልጆች እና በንብረት ላይ አደጋ ሲደርስ ግን እንደ ሚያሳዝን” ቅዱስነታቸው በወቅቱ ገልጸው ነበር። በዚሁ የተፈጥሮ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ሰዎች እግዚኣብሔር ምሕረቱን እንዲሰጣቸው፣ ለዘመድ አዝማዶቻቸው ድግሞ መጽናናትን እንዲሰጣቸው ተመኝተው በዚሁ ክስተት የተነሳ ተስፋ የመቁርጥ ስሜት ሊኖር እንደ ማይገባ አስስበው፣ በተጫማሪም በዚሁ አደጋ መኖሪያ ቤቶቻቸውን እና ንብርቶቻችውን ላጡ ሰዎች ድጋፍ እንዲደርግ ጥሪ አቅርበው እንደ ነበረ ይታወሳል።

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በጥር 14/2017 ዓ.ም. የፍልስጤም ርዕሰ ብሔር ከሆኑት ሙሃሙድ አባስ ጋር በቫቲካን ተገናኝተው በመካከለኛው ምስርቅ ስላለው የሰላም ሁኔታ ተወያይተዋል፣ በመቀጠልም የፍልስጤም መንግሥት ከቅድስት መንበር ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ትስስር ከቫቲካን ጋር ለማጠናከር በማሰብ የፍልስጤም ምንግሥት ለዚሁ ከቫቲካን ጋር ለሚደረጉ ግንኙነቶች ማስፈጸሚያ  የሚሆን ኤምባሲ በሮም ከተማ ከፍቱዋል ቅዱስነታቸው በምረቀው ስነ-ስረዓት ላይ ተገኝተዋል።

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በየካቲት 17/2017 ዓ.ም. በሮም ከተማ የሚገኘውን ሮማ ትሬ በተባለው ዩኒቬርሲቲ ሐዋሪያዊ ጉብኝት አድርገዋል። በጉብኝታቸውም ወቅት በዚያው ከሚማሩ ተማሪዎች እና በተለያዩ የሥራ መደብ ከተሰማሩ ሰዎች ጋር ተግናኝተው ተወያይተው የነበረ ሲሆን ዩኒቬርሲቲ “በልዩነቶች ላይ ውይይት በማድረግ ውህደት እንዲፈጠር ውይይት የሚደርግበት ሥፍራ እንደ ሆነ ጠቁመው፣ የሰው ልጆች ፍልሰት አደጋን የሚፈጥር ክስተት አለመሆኑን በመረዳት በዚህ ምክንያት የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በውይይት መፍታት እንደ ሚገባ መጠቆማቸው ይታወሳል።

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በየካቲት 27/2017 ዓ.ም. በሮም ከተማ የሚገኘውን የአንግሊካን ቤተክርስቲያን ጎብኝተዋል፣ በሃይማኖት ተቋማት መካከል ውይይት ማድረግ አስፈላጊ እንደ ሆነም ቅዱስነታቸው በወቅቱ ገልጸው ነበር።

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በመጋቢት 24/2017 ዓ.ም. ለአሁኑ የአውሮፓ ሕብረት ምስረታ ከፍተኛ አስተዋጾ ያበረከተው እና ከ60 ዓመት በፊት የተካሄደው “የሮም ስምምነት” በመባል የሚታወቀው ሰንድ የጸደቀበትን 60ኛ አመት ለመዘከር ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የተውጣጡ ርዕሰ ብሔሮች በተገኙበት ቅዱስነታቸው ንግግር አድርገው ነበር። በወቅት ቅዱስነታቸው ባደርጉት ንግግር አውሮፓ መሰረታዊ የሆኑ የሰው ልጆች እሴቶች ተጠብቀው ይሄዱ ዘንድ መሪዎች የበኩላቸውን ጥረት ማድረግ እንደ ሚገባቸው ጠቅሰው፣ የአንድነት እና የመተጋገዝ መንፈስ እንዲመጣ በተለይም ለቤተሰብ ጉዳይ እና ለወጣቶች ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ ማድረጋቸው ይታወሳል።

እንደ ጎጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በሚያዚያ 14/2017 ዓ.ም. የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በሮም ከተማ በሚገኘው ኮሎሴኦ በመባል በሚታወቀው ስፍራ ላይ የመስቀል መንገድ ጸሎት ተካሂዶ ነበር። በዚህም የጸሎት ስነ-ስራዓት ላይ ቅዱስነታቸው በቅዱስ መስቀል ሥር በመሆን “ ጌታ ሆይ እኛ በታላቅ ሀፍረት ተሞልተን ነገር ግን ልባችንን በታላቅ ተስፋ ሞልተን ወደ አንተ እንመለሳለን” በማለት ጸልየው እንደ ነበረ የሚታወስ ሲሆን በመቀጠልም ከቀናቶች ቡኃላ በተከበረው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በርሳቸው መሪነት ባሳረጉት የመስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት “ኢየሱስ ተቀብሮበት የነበረበት የመቃብር ስፍራ ላይ የነበረው እና የተከፈተው የመቃብር ክዳን የእኛ የሕይወታችን መሰረት እና ሕልውና ሆነ” ማለታቸው ይታወሳል።

እንደ ጎጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በግንቦት 24/2017 ዓ.ም. ከአሜርካው ርዕሰ ብሔር ከዶናልድ ትራፕ ጋር በቫቲካን ተገናኝተው እንደ ነበረ ይታወሳል። በወቅቱ በአሜሪካ የምትገኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በዚያው ለሚገኙ ከተለያዩ ሀገራት ለተውጣጡ ስደተኞ እያደርገች ያለውን ድጋፍ እና ለወደፊቱም ምን ማድረግ እንደ ሚገባት ተወያይተዋል። በመካከለኛው ምስርቅ የሰላም ጉዳይ ላይ ተነጋግረዋል፣ በተለይም ደግሞ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ውስጥ በሚገኙ የክርስቲያን ማሕበረሰቦች ላይ በአክራሪዎች እና በሽብርተኞች እየተቃጣ ያለውን ከፍተኛ ጉዳት እና በደል በተመለከት ቅዱስነታቸው ከአሜሪካው ርዕሰ ብሔር ዶናልድ ትራፕ ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት በስፋት የተወያዩበት ጉዳይ እንደ ነበረ ይታወሳል።

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በሰኔ 3/2017 ዓ.ም. ላይ “በመንፈስ ቅዱስ ታድሶ” የተሰኘው ዓለማቀፍ የካቶሊክ ምዕመናን ማኅበር 50ኛውን አመት የምስረታ በዓል ለማክብር በሮም ከተማ ተገኝተው እንደ ነበረ መዘገባችን ይታወሳል። ይህንን 50ኛ አመት የምስረታ በዓል ለማክብር ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ 50 ሺ ምዕመናን መንፈስ ቅዱስ በሐዋሪያት ላይ በእሳት አምሳል በወረደበት የጴንጤቆስጤ በዓል ዋዜማ ምሽት ላይ በሮም  ከተማ በሚገኘው ቺርኮ ማሲሞ በተባለው ስፍራ ተሰብስበው መጸለያቸውን መግለጻችን የሚታወስ ሲሆን፣ በዚያው የጸሎት ስፍራ የተገኙት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ከሁሉም የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ሁሉ የላቀው ስጦታ “ይቅርታ ማድረግ ነው” ማለታቸው ይታወሳል።

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በሰኔ 10/2017 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ከጣሊያን ሪፐብሊክ ርዕሰ ብሔር ከሆኑት ሴርጆ ማቴሬላ ጋር በሮም በሚገኘው ያጣሊያን ብሔራዊ ቤተ ምንግሥት ውስጥ ተገናኝተው  ነበር። በወቅቱም ቅዱስነታቸው የጣሊያን ሪፖብሊክ ርዕሰ ብሔር ለሆኑት ሴርጆ ማቴሬላ እንደ ገለጹት “አዳዲስ የሥራ እድሎችን መክፈት የሚችሉ ሂደቶችን በተቀናጀ እና በጋር ማከናወን እንደ ሚገባ አበክረው መግልጻቸው ይታወሳል።

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በሰኔ 17/2017 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው በቫቲካን የጀርመን ቻንስለር ከሆኑት አንጌላ ምርከል ጋር ተገናኝተው ነበር። በግንኙነታቸውም ወቅት በርካታ ጉዳዮችን በማንሳት ተወያይተው እንደ ነበረ መግለጻችን የሚታወቅ ሲሆን በተለይም ደግሞ የዓለማቀፉ ማሕበርሰበ በአሁኑ ወቅት በዓለማችን በከፍተኛ ሁኔታ እያተየ የሚገኘውን ድኽነት እና ረዐብ መዋጋት እናዳለበት በአጽኖት ገልጸው ነበር። በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ላይ ከፍተኛ የሆነ አደጋ የደቀነው የአሸባሪዎች ጥቃት እንዲሁም የዓለማችን የአየር ንብረት ለውጥ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አስታውሰው ለእዚህች የጋራ መኖሪያችንን በሆነችው ምድራችን ላይ ከፍተኛ ስጋት የደቀነውን ይህንን አደጋ በጋራ መከላከል ያስፈልጋል ብለው ነበር።

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በሰኔ 8/2017 ዓ.ም. የቅዱሳን ጴጥሮስ እና ጳውሎስ ዓመታዊ በዓል በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በታላቅ ድምቀት በተከበረበት ወቅት 5 አዳዲስ ካርዲናሎችን መሾማቸውንም መዘገባችን ይታወሳል። እነዚህ አዲስ የካርዲናልነት ማዕረግ የተሰጣቸው ጳጳሳት ከላዎስ፣ ከማሊ፣ ከሲውዲን፣ ከኤል ሳልቫዶረ እና ከእስፔን እንደ ነበሩ ይታወሳል።

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በጥቅምት 11/2017 ዓ.ም. የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ በአዲስ መልክ ተዘጋጅቶ የቀረበበትን 25ኛው ዓመት በተከበርበት ወቅት ቅዱስነታቸው በዚያው ተገኝተው ነበር። የእግዚኣብሔር ቃል ሁል ጊዜ የምያሳድግ እና እውነትን የያዘ የሕይወት ምንጭ ነው ብለዋል።

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በሕዳር 10/2017 ዓ.ም. በዓለማቀፍ ደረጃ የኒውክለር የጦር መሳሪያዎችን ማስወገድ ላይ ትኩረቱን ያደረገ አውደ ርዕይ በሮም ከተማ በተካሄደበት ወቅት ቅዱስነታቸው በዚያው ተገኝተው ነበር። ይህንን አውደ ርዕይ ለታደሙ ሰዎች ቅዱስነታቸው ባሰሙት ንግግር ይህንን አደገኛ እና አጥፊ የሆነውን የኒውክለር መሳሪያ የመታጠቅ ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ገልጸው፣ ይህም ፍላጎት የመነጨው ከፍርሃት የተነሳ መሆኑን ገለጸዋል። ስለዚህም ይህ አደገኛ እና የሰው ልጆችን በጅማላ የመጨረስ አቅም ያለውን ጅምላ ጨረሽ የሆነውን የኒውክለር መሳሪያ ሁሉም ሀገራት ያስወግዱት ዘንድ ጥሪ አቅረበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር 2017 .. ያደረጉዋቸውን ሐዋሪያዊ ጉብኝቶችን በአጭሩ እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እናግብዛለን።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ 18ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለማደርግ እንደ ጎጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በሚያዝያ 28 ወደ ግብፅ ማቅናታቸው ይታወሳል። የዚህ የቅዱነታቸው 18ኛው ሐዋሪያዊ ጉብኝት ዋንኛው ዓላማ በታላቁ በአል ዐዛር የእስልምና ማዕከል ዳይሬክተር ኢማም ሼህ አምድ አል ጣይብ፣ የግብፅ ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት የሆኑት አብደል ፋታህ ሳሂድ ሁሴን ካሊል አል ሲሲ እንዲሁም የአጠቃላዩን የግብጽ ሕዝብ 30% የሚወክሉት የግብፅ የኮፕት የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ሊቃነ ጳጳሳት የሆኑት ፓትሪያርክ ቴውድሮስ ዳግማዊ ባቀረቡላቸው ግብዣ ምክንያት እንደ ሆነ የታወቀ ሲሆን በተጨማሪም በዚህ ጉብኝታቸው እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በ969 ዓ.ም. መቆርቆሩ የሚነገርለት የአል ዐዛር የእስልምና ማዕከል ባዘጋጀው ዓለማቀፍ የሰላም ጉባሄ ላይ ተገኝተው ንግግር ማድረጋቸውን መዘገባችን ያትወሳል።

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በግንቦት 12/2017 ዓ.ም. ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮ 19ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለማድረግ በፖርቹጋል ሀገር ፋጢማ በሚባል ልዩ ስፍራ የሚገኘውን እና የዛሬው 100 አመት ገደማ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በወቅት እረኛ ለነበሩ 3 ሕጻናት የተገለጸችበት ሥፍራ የሚገኘውን የፋጢማ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማሪያም ቤተ መቅደስ ለመሳለም ወደ እዚያው መሄዳቸው ይታወቃል። ቅዱስነታቸው በዚህ መንፈሳዊ ጉዞዋቸው ለማሪያም ያላቸውን ፍቅር እና እምነት በመግለጽ ለእመቤታችን ቅድስት ማሪያም የግል ጸሎታቸውን ያቀረቡበት ወቅት እንደ ነበረም መዘገባችን ያትወሳል።

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከመስከረም 06-11/2017 ዓ.ም.  ደረስ በኮሎንቢያ 20ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን ለምድረግ ወደ ኮሎንቢያ ማቅናታቸው ይታወሳል።

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከሕዳር 26-ታኅሳስ 2/2017 ዓ.ም. ድረስ በማያንማር (የቀደሞ ስሟ በርማ)እና በባንላዲሽ  ሐዋሪያዊ ጉብኝት አድርገዋል። ማያንማር 54.4 ሚልዮን ሕዝብ ብዛት ያላት ሀገር ስትሆን በጣም በቁጥር አነስተኛ የሆኑ የካቶሊክ ምዕመናን የሚገኙባት ሀገር ናት።  

በማያን ማር ያደርጉት ሐዋሪያዊ ጉብኝት “የሰላም ልዑክ” በሚል መሪ ቃል ያነገበ እንደ ነበረ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በመቀጠልም ቅዱስነታቸው በባንግላዲሽ አድርገውት ለነበረው 21ኛ ሐዋሪያዊ ጉብኝት ደግሞ የመረጡት መሪ ቃል “ሰላም እና ሕብረት” የሚል መሪ ቃል ያነገበ ነበር። ባንግላዲሽ 166 ሚሎዮን የሕዝብ ብዛት ያላት ሀገር ናት። ከጠቃላይ የሕዝብ ብዛቷ ውስጥ 350,000 የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ሲሆኑ ይህም በመቶኛ ሲሰላ 0.24 % የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ናቸው። አብዛኛው የባንግላዲሽ ሕዝብ የሙስሊም እምነት ተከታትይ ሲሆን፣ የቡዳ እና የሌሎች ባሕላዊ እመንት ተከታዮችን መኖሪያ ናት ባንግልዲሽ።

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.