2017-12-12 16:49:00

ቅዱስ አባታችን፡ ፖለቲካ ለሰው ልጅ አገልግሎት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ትዊተር በተሰየመው ማኅበራዊ መረብት ዘንድ ባለው @Pontifex በተሰኘው አድራሻቸው አማካኝነት እ.ኤ.አ. ታህሳስ 10 ቀን 2017 ዓ.ም. በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውሳኔ መሠረት ታስቦ የሚውለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብትና ክብር ቀን ምክንያት በማድረግ፥ ፖለቲካዊ ምግባር ለሰው ልጅ፡ ለጋራ ጥቅም እና ተፈጥሮን እና ፍጥረትን ለማክበር የገልግሎት መሣሪያ መሆን አለበት  የሚል መልእክት መልቀቃቸው ሲታወቅ። ይኽ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 10 ቀን 1948 ዓ.ም. ለሁለተኛው የዓለም ጦርነት እና በዚያኑ ወቅት ተከስቶ ለነበረው የሰው ልጅ አሰቃቂው እልቂት ግብረ መልስ በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ መሠረት በፓሪስ በተካሄደው ዓለም አቀፋዊ ዓውደ ጉባኤ የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር የውሳኔ ሰነድ ከጸደቀበት ዕለት ጋር በማያያዝ በየዓመቱ የሚዘከር የሰብአዊ መብትና ክብር ቀን ሲሆን፡ ይክ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብትና ክብር ሰነድ በአምስት መቶ ቋንቋዎች ተተርጉሞ ለንባብ የበቃ ሆኖ፡ በዓለማችን በብዙ ሚሊዮን ለሚገመተው ህዝብ ነጻነት እና ደኅንነት መረጋገጥ ያስቻለ ማሕበራዊ እና ግላዊ ነጻነት በሁሉም ስፍራ እንዲስፋፋና እንዲረጋገጥ የረዳ ውሳኔ መሆኑ ቀኑን ምክንያት በማድረግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉተረስ ባስተላለፉት መልእክት ገልጠው፡ እ.ኤ.አ. በ 2018 ዓ.ም. ይኽ በፓሪስ የጸደቀው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰው ልጅ የሰብአዊ መብትና ክብር  ሰነድ 70ኛ ዓመቱንም እንደሚያከብር ከወዲሁ ማስታወሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሚከለ ራቪያርት ገለጡ።

በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ የዓለማችን ክልሎች፡ በተጨባጩም በሶሪያ በደቡብ ሱዳን፡ በማእከላዊ ረፓብሊክ አፍሪቃ እና በዚያ እስላማዊ አሸባሪ ኃይሎች በስፋት በሚንቀሳቀሱባቸው አገሮች መሰረታዊው የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ሲጣስ እና ከዚህ ጋር ተያይዞም እርሃብ መስፋፋት፡ ሕፃናት ለውትድርናው ዓለም መዳረግ  ጨቅላው እድሚያቸውን ተነጥቀው ለሥራ ዓለም ተላልፈው የሚሰጡት ባጠቃላይ ለአዳዲስ የባርነት ቀንበር የሚዳረጉት ብዛት እጅግ ከፍ እያለ መምጣቱ በካሪታስ ለሚጠራው ለኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ቅርንጫፍ በኢጣሊያ ምክትል አስተዳዳሪ ፓውሎ በቸጋቶ ቀኑን ምክንያት በማድረግ ባሰራጩት መልእክት እንዳሰመሩበት ቫሪያርት ያመልክታሉ።

በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ የሰብአዊ መብትና ክብር ጥሰት ምክንያት በዓለማችን 250 ሚሊዮን ለስደት መዳረጋቸው እና 65 ሚሊዮን መፈናቀላቸው ገለው፡ የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር አብሮት አማራጭ ሳይሆን ሁሉም ሊያከብረው የሚገባው እና የሰዎችና የሁሉም ጥቅም ለማረጋገጥ የሚበጅ የሰላም መሣሪያ ነው እንዳሉ በቸጋቶ ያስተላልፉት መልእክት የጠቀሱት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ራቪያርት አስታወቁ።   








All the contents on this site are copyrighted ©.