2017-12-09 11:36:00

የጽንሰተ ማሪያም አመታዊ በዓል በደመቀ ሁኔታ በቫቲካን መከበሩ ተገለጸ


የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ አብያተክርስቲያናት  ዘንድ በትላንትናው እለት ማለትም በኅዳር 28/2010 ዓ.ም. የጽንሰተ ማሪያም ዓመታዊ ክብረበዓል በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ውሉዋል።

በካቶሊክ ቤተክርስቲያ ስርዓተ አምልኮ ውስጥ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ከፍተኛ የሆነ ቦታ እንዳለት ይታወቃል። በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዶግማ (አንቀጸ እምነት) ወይም የማይሻር የማይለወጥ አስተምህሮ ውስጥ ማሪያምን የሚመለከቱ 4 (አንቀጸ እምነቶች) ዶግማዎች ይገኛሉ። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስ እናት ብቻ ሳትሆን እርሱ አምላክ በመሆኑ የተነሳ የእግዚኣብሔር እናት ናት የሚለው የመጀመሪያው ነው (Mary Mother of God) ። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ እነሆ ዛሬ የምህራባዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ዛሬ እየተከበረ የሚገኘው የጽንሰተ ማሪያም በዓል ሲሆን ይህም ማሪያም ያለአዳም ኃጢአያት የተጸነሰች ናት፣ ምክንያቱም እግዚኣብሔር የልጁ እናት እንድትሆን አስቀድሞ የመረጣት በመሆኑ የተነሳ እኛ ሰዎች ሁላችን ይዘነው የምንወለደው እና ምስጢረ ጥምቀት በምንቀበልበት ወቅት የሚደመሰሰው (የሚሰረየው) ኃጢአት  ነጻ ሆና እንድትወለድ እግዚኣብሔር አድርጓታል የሚለው በሁለተኛ ደረጃ የምናገኘው ዶግማ (አንቀጸ እምነት) (Imaculate conception) ነው። በሦስተኛ ደረጃ ደግሞ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ጌታችን በቅድሚያ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የጸነሰቺው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አማካይነት ነው፣ እርሱንም የወለደቺው በድንግልና ነው፣ ከወለደችሁም ቡዋላ እናኳን ለዘልዓለም ድንግል ሆና ትኖራለች የሚለው 3ኛው ዶግማ (አንቀጸ እምነት)  ነው (The Perpetual Virginity of Mary) ። በአራተኛው ደረጃ የምናገኘው ደግሞ ፍልሰታ ማሪያም የሚያመለክት ዶግማ ነው። ይህም በሀገራችን የቀን አቆጣጠር በእየአመቱ በነሐሴ 16 የሚከበረው በዓል ሲሆን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ምድራዊ ሕይወቷ ባበቃ ጊዜ  በነብስ እና በስጋ ወደ ሰማይ ተወስዳለች የሚለው የማሪያምን በነብስ እና በሥጋ ወደ ሰማይ መፍለሷን የሚያመልክት ዶግማ (አንቀጸ እምነት) ነው (Thw Assumption of Mary into heaven)።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች እንግዲህ  ስለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም (አንቀጸ እምነት) ይህንን ያህል ካልንችሁ ቡዋላ በቀጣት ወደ ዛሬው ዝግጅቶችንን እንመልሳችኃለን።

ቀደም ሲል በመግቢያችን ላይ ለመገልጸ እንደ ሞከርነው በትላንትናው እለት ማለትም በኅዳር 28/2010 ዓ.ም.  የምሕራባውያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ አብያተክርስቲያን የጽንሰተ ማሪያምን ዓመታዊ በዓል በደመቀ ሁኔታ አክብረው ውለዋል። በተመሳሳይ መልኩም ይህ በዓል በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ መከበሩ የተገለጸ ሲሆን ይህንን በዓል ለመታደም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ያደረጉትን ስብከት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን ኣንድትከታተሉን እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ፣ መልካም በዓል ይሁንላችሁ!

ዛሬ የጽንሰተ ማሪያምን ውበት እናሰላስላለን። ዛሬ በተነበበልን ቅዱስ ወንጌል (ሉቃስ 126-38) ውስጥ የተጠቀሰው የማሪያም ብስራት ታሪክ ዛሬ እያከበርነው የሚንገኘው በዓል ምን እንደሆነ ለመገንዘብ እንድንችል ይረዳናል፣ በተለይም ደግሞ የመልአኩ ገብረኤል ሰላምታ ይህንን በዓል በላቀ ሁኔታ እንድንገነዘብ ያደርገናል። እርሱም በሰውኛ ቋንቋ ለመተርጎም የምያዳግቱ ቃላትን በመጠቀምጸጋን የተሞላሽበማለት ይጀመራል። ማሪያም ብሎ በስሟ ከመጥራቱ በፊት ጸጋን የተሞላሽ በማለት በመጀመር በዚህም በእግዚኣብሔር የተሰጣትን አዲስ ስም ይፋ አደረገ፣ ይህም ወላጆቿ ከሰጧት ስም የበለጠ ዋጋ እንዳለው አሳየ።  እኛምጸጋ የሞላሽ ማሪያም ሆይእያልን ነው የምንጠራት።

ታዲያጸጋ የሞላሽማለት ምን ማለት ነው? ይም ማለት ማሪያም በእግዚኣብሔር ሕልውና የተሞላች ናት ማለት ነው። እግዚኣብሔር በምልአት በውስጧ ስላደረ ለኃጢያት ምንም ቦታ በውስጧ የለም ማለት ነው። ዓለማችን በተለያዩ ክፉ በሆኑ ነገሮች ተበክሎ በአለበት ወቅት ይህ በጣም ትልቅ የሆነ ነገር ነው። እያንዳንዳችን ውስጣችን ብንመለከት የጨለሙ ጎኖቻችንን መመልከት እንችላለን። ከማሪያም በስተቀር ሁሉም ታላላቅ ቅዱሳን የሚባሉ ሳይቀሩ ኃጢያተኞች ነበሩ። ሁል ጊዜ የሰው ልጆች የልምላሜ መገለጫ የሆነች፣ በኃጢኣት ያልተበከለች፣ ያለአዳም ኃጢኣት የተጸነሰች፣ ሙሉ በሙሉእንዳልከኝ ይሁንልኝበማለት ወደ ዓለም በመምጣት እና ለዓለም አዲስ ታሪክ የፈጠረውን እግዚኣብሔርን በውስጧ በማኖር የታዘዘች እርሷ ብቻ ናት።

ሁል ጊዜጸጋ የሞላሽ ማሪያም ሆይ!” በምንልበት ውቅቶች ሁሉ ለእርሷ ብቻ ሳይሆን ይህንን ታላቅ ነገር በሕይወቷ ያከናወነውን እግዚኣብሔርንም እናመሰግናለን።ጸጋን የተሞላሽ ማሪያም ሆይበምንልበት ወቅት ይህንንም የምንለው ለየት ባለ እና ክብር በተሞላው መልኩ ነው። እርሷ ሁል ጊዜ ወጣት እንደ ሆነች አድርገን ነው የምንቆጥረው ምክንያቱ ኃጢኣት አላስረጃትም እና ነው። እኛን ልያስረጀን የሚችል አንድ ነገር ብቻ ነው፣ ይህም የውስጥ እርጅና ነው፣ በእድሜ ማርጀት ሳይሆን ከኃጢኣት የሚመጣ እርጅና። እኛን የሚያስረጀን ኃጢኣት ነው፣ ምክንያቱም ኃጢአት ልባችንን ስለሚበክል ነው። ልባችንን ይዘጋል፣ ልባችንን ያፈርሳል፣ ልባችን እንዲሰቃይ ያደርጋል። ነገር ግን በጸጋ መሞላት ከኃጢአት ነጻ ያደርጋል። ማሪያም ሁሌም ወጣት ናት የምላችሁ በዚሁ ምክንያት ነው።

ቤተክርስቲያን ዛሬ ይህንን የማሪያም ውብት እና ንጽሕና በማሰላሰል ላይ ተገኛለች። የእርሷ ወጣትነት በእድሜዋ እንደ ማይለካ ሁሉ እንደዚህም የእርሷ ውበት በውጫዊ ገጽታዋ አይለካም። የዛሬ ቅዱስ ወንጌል እንደ ሚለን ይህንኑ ነው፣ በጣም ትሁት ከሆነ ቤተሰብ የተገኘች፣ በትህትና በናዝሬት ትኖር የነበረች፣ በሰዎች ዘንድ ብዙ የምትታወቅ ሴት እንዳልነበረችም ያስረዳናል። መልአኩ ገብርኤል ወደ እርሷ መምጣቱን እንኳን ማንም ሰው አያውቅም ነበረ፣ ምናልባትም በዚያን ወቅት ዘጋቢ ጋዜጠኞች ስላልነበሩ ይሆናል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያ የተደላደለ ኑሮ አልነበራት ነበር በአንጻሩ ግን ጭንቀትና በፍርሃት ተሞልታ ነበረ፣ በሉቃስ ወንጌል 129 “ማሪያም በመልአኩ ንግግር በጣም ደንግጣእንደ ነበረ ይናገራል፣ በልአኩ ገብርኤል ከእርሷ ተለይቶ በሄደበት ወቅት ችግሮቹዋም ተባብሰው ነበር።

ነገር ግን ይቺህጸጋ የተሞላችሴት ውብ የሆነ ሕያወት ኖራላች። ታዲያ የእዚህ ምስጢር ምን ይሆን? ይህንንም ለመረዳት አሁን ለአንድ አፍታ መልአኩ ገብርኤል ያበሰራትን ብስራት መመልከት ያስፈጋል። ብዙ ሰዓሊያን የመልአኩ ገብርኤልን እና የማሪያምን ግንኙነት በስዕል ስያስፍሩ ማሪያም ከመልአኩ ፊት ለፊት ቁጭ ብላ ትንሽዬ መጽሐፍ በእጃ እንደ ያዘች የሚያሳይ ስዕል ስለዋል። ይህ መጽሐፍ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። በዚህም ማሪያም እግዚኣብሔርን ማዳመጥ ተለማምዳ ነበር፣ ከእርሱም ጋር ትተዋወቅ ነበር። ታዲያ የማሪያም ሕይወት ምስጢር ይህ የእግዚኣብሔር ቃል ነው፣ ለእርሱ ልብ ቅርብ ነበረች፣ የእርሱን ሥጋ በማህጸኑዋ አሳደረች። ከእግዚኣብሔር ጋር አብሮ በመኖር፣ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ከእርሱ ጋር ትወያይ ነበረ፣ ይህ ድርጊቷ የማሪያም ሕይወት ያማረ እንዲሆን አድርጎታል። የምያልፈው ውጫዊ ውበት ሳይሆን ወደ እግዚኣብሔር የሚጠቁም ልብ ሁልጊዜ ሕይወትን ውብ ያደርጋል። ዛሬ በደስታ ይችህንጸጋ የተሞላችእንመልከት። ሁልጊዜ ወጣት ሁነን መኖር እንድንችል ትረዳን ዘንድኃጢአትን እብየው!” በማለት በአንጻሩም ለእግዚኣብሔር አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት ውብ የሆነ ሕያወት እንድንኖር እርሷ በአማላጅነቷ ሁላችንንም ትርዳን አሜን።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.