2017-12-06 15:27:00

በማያንማር እና በባንግላዲሽ አድርጌው በነበረው 21ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝት የተሳካ እንዲሆን ያደረጉ ሁሉ አመሰግናለሁ


 

ዘወትር ርዕቡ እለት  በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የትምህርተ ክርስቶስ አሰትምህሮን እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። በዛሬው እለት ማለትም በኅዳር 27/2010 ዓ.ም. ዘወትር ረዕቡ እለት በምያደርጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ፈነታ ከኅዳር 17-23/2010 ዓ.ም በማያንማር እና በባንግላዲሽ ያደርጉትን 21ኛውን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸውን አስመልክተው አድርገውት ስለነብበረው ጉብኝት ጠቅላላ ይዘት መልእክት አስተላፈዋል እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

የተወደዳችሁ ወንድሞች እና እህቶች እንደምን አረፈዳቹሁ!

በዛሬ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምግሮ ፈነታ በማያንማር እና ባንግላዲሽ ከቅርብ ጊዜያት በፊት አድርጌ ስለነበረው ሐዋሪያዊ ጉዞ መናገር እፈልጋለሁ። ይህ ጉዞ ከእግዚአብሔር የተሰጠኝ ታላቅ ስጦታ ነው፣ ስለዚህ ስለ ሁሉም ነገር በተለይም ደግሞ አድርጌያቸው ስለነበሩ ስብሰባዎች ምስጋና ማቅረብ እወዳለሁ። በሁለቱም ሀገራት ለሚገኙት ባለስልጣናት፣ የተከበሩ ጳጳሳት እንዲሁም ይህ የእኔና ከእኔ ጋር ይህንን ጉዞ ያደረጉ ሰዎች ጉብኝት የተሳካ እንዲሆን ለተባበሩ ሰዎች ሁሉ በድጋሚ ማስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ። በማያንማር እና በባግላዲሽ ለሚኖሩና ታላቅ እመንት እና ፍቅር ላሳዩኝ ሰዎችም ሁሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ። በድጋሚም አመሰግናለሁ ለማለት እወዳልሁ።

አንድ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የሆነ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ማያንማርን ሲጎበኝ የመጀመሪያው ጊዜ ቢሆንም ይህ ጉብኝት ደግሞ በቅርብ ጊዜ በሁሉቱም ሀገራት ማለትም የቅድት መንበር እና በማያንማር መንግሥት መካከል የተደረገው የዲፕሎማሲ ግንኙነት ወጤት ነው።

እንደዚሁም በዚህ ጉብኚቴ በግጭቶች እና በአደገኛ ጫናዎች ምክንያት እይተሰቃዩ ለሚገኙ፣ አሁን ደግሞ ቀስ በቀስ ወደ ሰላም እና ወደ ነጻነት እያተጓዙ ለሚገኙ ሰዎች ቤተክርስቲያን እና ክርስቶስ ከእነርሱ ጎን እንደ ሚቆሙ ለመግለጽ አስቤም ያደርኩት ጉብኝት ነው። የቡዳ እምነት በከፍተኛ ደረጃ ሥር የሰደደበት፣ መንፈሳዊ እና ሥነ-ምግባራዊ መርሆዎች በከፍተኛ ደረጃ በሚከበሩበት ሀገር ውስጥ የሚገኙት ክርስቲያኖች እንደ አንድ አነስተኛ የእግዚአብሔር መንጋ ሆነው የእግዚኣብሔር መንግስት እርሾ በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ። ይቺህ በማያንማር የምትገኘው ሕያውና ትጉ የሆነች ቤተክርስቲያን መሆኑዋንም ከአገሪቱ የጳጳሳት በተገናኘውበት ወቅት እና መስዋዕተ ቅዳሴን ባደረኩበት ወቅት ለማረጋገጥ በመቻሌ ደስታ ይሰማኛል። በቅድሚያ በያንጎን በሚገኘው የእስፖርት ማዕከል ላይ በተሰራው ጊዜያዊ መነበረ ታቦት ላይ ባደርኩት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ የተነበበው ወንጌል በኢየሱስ በማመናቸው ምክንያት በእርሱ ደቀ መዛሙርት ላይ የሚደርሰው ስደት የሚጠበቅ እና ጤናማ የሆነ ስደት እንዲሁም እየሱስን የመመስከር እድል የሚፈጥር መሆኑን የተረዳንበት የወንጌል ክፍል ሲሆን ነገር ግን በሉቃስ ወንጌል 21፡12-19 ላይ እንደ ተጠቀሰው “ከጸጉራቸው አንድም እናኳን እንደ ማይጎድል” ያሳየናል። በመቀጠልም በማያንማር ያደርኩትን ሐዋሪያዊ ጉብኝት  ማብቂያ ምክንያት በመድረግ ከወጣቶች ጋር ቆያታ አድጌ ነበረ፡ እነርሱ የተስፋ ምልክቶች የሆኑ እና ከእነርሱ ጋር የነበረኝ ቆይታ ደግሞ በማሪያም ስም በተሰየመው ካቴድራል ውስጥ የነበረ በመሆኑ የተነሳ እነርሱም የማሪያም ስጦታዎች አድርጌ እቆጥራቸኃለሁኝ። የእነዚህ ወጣቶች የፊት ገጽ በደስታ የተሞላ ሆኖ በማዬቴ የወደፊቱ የኤሽያ ተስፋ መሆናቸውን ተመልክቻለሁ፡ ይህም መጪው ጊዜ መልካም እና በተስፋ የተሞላ እንዲሆን የሚያደርገው የጦር መሳሪያዎች በሚያመርቱ ሰዎች ሳይሆን ነገር ግን የወንድማማችነት ዘር በሚዘሩ ሰዎች አማካይነት መሆኑን ያሳያል። 16 አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናት፣ ዘረዕ ክህነት እና በሀገሪቷ የሚገነባውን አዲስ የቅድስት መንበር ጸሐፊ ቤት የሚገነቡባቸውን ስፍራዎች ለመባረክ በመታደሌ ትልቅ የተስፋ ምልክት ሆኖኛል።

ከካቶሊክ እመነት ተከታይ የማኅብረሰብ ክፍሎች ጋር ከነበረኝ ቆያት ባሻገር ከሀገሪቷ ባለስልጣናት ጋር በነበረኝ ቆይታ ደግሞ በሀገሪቷ የሚገኙትን የማህበረሰብ ክፍሎችን፣ ማንንም ባላገለለ መልኩ ማለት ነው ሰላም ይሰፍን ዘንድ፣ በጋር መግባባት እና መከባበር የሰፈነበት የማኅብረሰብ ክፍል እንዲመሰረት የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ በዚህም እንዲበረቱም ጥሪ አድርጊያለሁኝ። በእዚህ አግባብ እና መንፈስ ከተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር ተገናኝቻለሁ። በተለይም ደግሞ የቡዳ እምነት የመማክርት ጉባሄ ዋን ሰብሳቢ ከሆኑት ሰው ጋር በነበረኝ የግል ቆይታ ለእነርሱ ጥንታዊ ለሆነው መንፈሳዊ ባህላቸው ቤተክርስቲያን ያላትን ክብር በመግለጽ ክርስቲያኖችን እና የቡዳ እማነት ተከታይ የሆኑ የማኅብረሰብ ክፍሎች በአንድነት ሰዎች እግዚኣብሔርን እና ባልንጄራቸውንም ሳይቀር መወደድ እንዲችሉ፣  እንዲሁም በአጠቃላይ ሁከቶችን እና ብጥብጦችን በመቃወም ክፉን ነገር በመልካም መቀየር እንደ ሚችሉ ገልጨላቸዋለሁ።

በማያንማር የነበረኝ ጉብኝት አጠናቂቄ ወደ ባንግላዲሽ በሄድኩበት ወቅት ደግሞ በቅድሚያ ለሀገራቸው ነጻነት በመውጋት ደማቸውን ያፈሰሱ ሰማዕታት “የሀገሪቷ መስራች አባቶች” ሐውልትን ጎብኝቻለሁ።  በባንግልዲሽ የሚኖሩ የመኅበርሰብ ክፍሎች አብዛኞችሁ የእስልምና እምነት ተከታይ በመሆናቸው የተነሳ የህ ጉብኝት ከእኔ በፊት የነበሩ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ እና ዩሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ በነበራቸው መርሕ ላይ ተመስርቶ የነበረ ሲሆን በዚህም ላይ ተመርኩዤ በሙስሊምና በክርስቲያን የማኅብረሰብ ክፍሎች መካከል በመከባበር ላይ የተመሰረት ውይይቶች ይደረጉ ዘንድ ጥሪ አቅርቢያለሁኝ።

ከሀገሪቷ ባለስልጣንት ጋር በነበረኝ ቆይታ ደግሞ ቀደም ካሉት ጊዜያት ጀመሮ እስካሁኑ ድረስ ባንግላዲሽ ራሷን የቻለች ነጻ ሀገር መሆኑዋን እና የሐይማኖት ነጻነት የሚከበርባት ሀገር መሆኗን በቅድስት መንበር እውቅና የተሰጠው ጉዳይ መሆኑን አረጋግጨላቸዋለሁ። በተለይም ደግሞ በአሁኑ ወቅት ከማያንማር ተሰደው ለመጡ የሮጋያን የማሕበርሰብ ክፍሎች የባንግላዲሽ መንግሥት እያደረገው ለሚገኘው ድጋፍ አጋርነቴን አረጋግጫልሁ።

በዳካ በሚገኘው ታሪካዊ በሆነ ሥፍራ ላይ በጊዜያዊነት በተሰራው ስፍራ ላይ ተገኝቼ ያሳረኩት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ማዕረገ ክህነትን ለአዳዲስ ካህናት ለመስጠት በመቻሌ በዚህ ሐዋሪያዊ ጉብኝቴ ወቅት ከፍተኛ ትርጉም የሰጠኝ እና ደስታንም የፈጠረብኝ አጋጣሚ ነበረ። በእርግጥ በባንግላዲሽ ይሁን በማያንማር እንዲሁም በደቡብ ኤሲያ ሀገራት ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ መነፍሳዊ ጥሪን እየተቀበሉ የሚመጡ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨረ በመምጣቱ እግዚኣብሔርን እያመሰገንኩኝ ይህም በዚያ የሚኖሩ የማኅብረሰብ ፍሎች አሁንም ከፍተኝ እንቅስቃሴ እያደርጉ እና እንድንከተለው ዘወትር የሚጠራን የኢየሱስ ድምጽ አሁኑም ሕያው መሆኑን ያሳያል።  ይህንንም ደስታዬን በባንግላዲሽ ለሚገኙ ጳጳሳት የገለጽኩላቸው ሲሆን ለቤተሰቦች፣ ለድኾች ለትምህርት ቤቶች እንዲሁም ለሰላም እና ለማኅብራዊ እድገት እይደርጉ የሚገኘውን አስትዋጾ እና ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ አደራ ብያለሁ። በተጨማሪም ይህንኑ ደስታዬን በዚያ ከተገናኘዋቸው ካህናት፣ ገዳማዊያ እና ገዳማዊይያት፣ ከዘረዐ ክህነት ተማሪዎች ጋር ሳይቀር በተገናኘውበት ወቅት የጠቀስኩላቸው ሲሆን እነርሱንም በማዬቴ በተክርስቲያን በዚያ ሀገር እያበበች እንደምትገኝ ለመረዳት ችያለው።

በዳካ ከተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት ጋር በነበረን ግንኙነት ወቅት ያደርገነው ውይይት ጠንከር ያለ ጊዜ አጋጥሞናል፣ ይህም ሰላም እና ኅብረት ሊፈጠር የሚችለው ለውይይት ልባችንን ክፍት የማድረግ ባሕል ማዳበር ስንችል ብቻ መሆኑን እንድገነዘብ አድርጎኛል። በዳካ የሚገኘዋን የማዘር ትሬዛ ቤት ጎብኚቼ የነበረ ሲሆን በዚያም ብዙ በጣም ብዙ ወላጅ አልባ ሕጻናት እና አካል ጉዳተኝኞችን ተመልክቻለሁ። በዚያ የሚኖሩ የእማሆይ ትሬዛ ማኅበር ደናግላን የራሳቸው ማሕበር መንፈሳዊ መክሊት በመከተል በእየቀኑ ክርስቶስን በማምለክ እና በድኾች እና በሚሰቃዩ ሰዎች ውስጥ የሚኖረውን ክርስቶስን በማገልገል ላይ ይገኛሉ። ከፊታቸው ገጽታ ላይ ፈገግታ ጠፍቶ አያውቅም፣ በጣም ብዙ ይጸልያሉ፣ የተሰቃዩ እና የተቸገሩ ሰዎችን ያገለግላሉ ይህንንም ሁሉ ሲያደርጉ በታላቅ ደስታ ነው። እንዴት ደስ የሚል ምስክርነት ነው? እነዚህን ደናግላንን ማመስገን እፈልጋለሁ።

በሐዋሪያዊ ጉብኚቴ ማገባደጃ ላይ በባንግላዲሽ ከሚኖሩ የወጣት ማኅብረሰብ ክፍሎች ጋር ቆያት ባደረኩበት ወቅት ያሳዩት ምስክርነት፣ ያስሙት ዜማ እና ዳንስ ትዝ ይለኛል። እነዚህ ወጣቶች የወደፊቱ የባንግላዲሽ የተፋ ምልክቶች ናቸው። ስለሁሉም ነገር በጣም አመሰግናልሁ።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.