2017-11-28 15:00:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ምያንማር በያንጎን በሚገኘው ዓለማቀፍ የአይሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ደረሱ


ቅዱስ አባታችን ... ፍራንቸስኮ ምያንማር ደረሱ

ቅዱስ አባታን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ህዳር 18 ቀን 2010 ዓ.ም. በማያንማር በያንጎን በሚገኘው የአይሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በፊት ልክ 04 ሰዓት ላይ ደርሰው በማያንማር እና በመቀጠልም ወደ ባንግላደሽ የሚያደርጉት 21ኛው ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው በይፋ ጀምረዋል።

ቅዱስ አባታችን በአየር ማረፊያው እንደደረሱም ወደ አይሮፕላኑ ውስጥ በመግባት በታይላንድ ካምቦጃ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልዑክ በላኦስ ደግሞ ሐዋርያዊ ወኪል በሆኑት በብፁዕ አቡነ ፓውል ቻንግ ኢን ናም እና የቅድስት መንበር እና የምያንማር የውጭ ጉዳይ ግኑኝነት ሥነ ስርዓት ተጠሪ አማካኝነት ታጅበው  ከአይሮፕላኑ እንደወረዱ እዛው ይጠባበቁዋቸው በነበሩት በምያንማር ረፓብሊካዊት ርዕሰ ብሔር ልዩ ሚኒስትር ህቲን ክያዋ በምያንማር የጠቅላይ ቤተ ክርስቲያን ብፁዕን ጳጳሳት እና ወደ መቶ በሚገመቱ ሕፃናትና ባህላዊ ልብስ በለበሱ የምያንማር ብሔር ብሔረሰቦችን በወከሉት እና በመንግሥት ሰልፈኛው ክቡር ዘብ አቀባበል እንደተደረገላችው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስነታቸው በቀጥታ ያንጎን ወደ ሚገኘው ወደ ሊቀ ጳጳሳዊ ሕንፃ ደርሰው በግል መሥዋዕተ ቅድሴ አሳርገዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.