2017-11-24 15:32:00

የቅዱስ አባታችን ወደ እስያ የሚያካሂዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት የተስፋ ትእምር ነው


የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዚህ በእስያ ለሁለተኛ ጊዜ በምያንማርና በባንግላደሽ ደግሞ የመጀመሪያ የሚፈጽሙት ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት በማስመልከት በፊሊፒንስ የማኒላ ሊቀ ጳጳሳት በካሪታስ ለሚጠራው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበራት እንዲሁም የተለያዩ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የበጐ አድራጎት ማኅበራትን የሚጠረንፈው ካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ ለተሰየመው ተቋም ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ታግለ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ የቅዱስ አባታችን ወደ እስያ የሚያካሂዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት የተስፋ ትእምር ነው በማለት ከገለጡ በኋላ፤ በሁለቱ አገሮች የሚገኙት ካቶሊካውያን በቁጥር እጅግ አነስተኛ ናቸው ስለዚህ ከዚህ አንጻር ሲታይም፡ ውሁዳኑ የአስፍሆተ ወንጌል ልኡካን የሆኑባቸው አገሮች ዜጎች ናቸው። ውሁዳኑ ሰባኬ ወንጌል በማለት ገልጠው፡ ይኽ ደግሞ ያንን የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የወንጌላዊ ልኡክነት ስልጣናዊ ትምህርት የሚገልጠው የቤተ ክርስቲያን ታታሪነት በትክክል የሚጎላ ተጨባጭ የወንጌላዊ ልኡክነት ሁነት ነው ብለዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ታግለ እ.ኤ.አ. ህዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ወንጌል የሚያበስር ኅዳጣን፡ የቤተ ክርስቲያን የወንጌላዊ ልኡክነት ታታሪነት በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ስልጣናዊ ትምህርት፡ በሚል ርእስ ሥር በተካሄደው ዓውደ ጥናት ተገኝተው ባሰሙት ንግግር፥ አዲስ ዜና አብሳሪነት የሁሉ ሰብአዊ ፍጥረት ባህርይ ነው፡ ትክስ ዜና ማበሰር ትኩስ ዜና የመስማቱ ፍላጎት የሁሉም ነው፡ ስለዚህ መልካም ዜና ማበሠር ከዚህ በዘለለ እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ለመረዳቱ አያዳግትም፡ አዲስ ዜና ለማበሰር ብዙ ጥረት የሚደረግ ከሆነ መልካም ዜና (ወንጌላዊው ዜና) ለማበሰርት ምንኛ የበለጠ ጥረት መደረግ እንዳለበት ክዚህ አንጻር ለሁሉም ግልጽ ነው። ኢየሱስ ጋር መገናኘት ማለትም በድኾች በተናንሾች አማካኝነት ስንገናኘው በእውነቱ ከእውነተኛው ኃሴት ጋር እንገናኛለን። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ድኻይቱ ለድኾች የሆነች ቤተ ክርስቲያን መሆን ያስፈልጋል ይላሉ ፥ ቤተ ክርስቲያን የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እና የወንጌላዊ ልኡክነት ሕሊና ምርመራ ልታደርግ ይገባታል ብሏል።

ብፁዕ ካርዲናል ታግለ ከዓውደ ጉባኤ ፍጻሜ በኋላ ከቫቲካን ርዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስም፥ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ውሳኔ መሠረት እ.ኤ.አ. ህዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም. የተከበረው ዓለም አቀፍ የድኾች ቀን አስታውሰው፡ የድኾች ቀን ከተከበረበት ጥቂት ቀናት በኋላ ቅዱስ አባታችን በምያምናር እና በባንግላደሽ የሚያካሂዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት በድኾች እሱነቱን ሊገልጥ ከመረጠው ኢየሱስ ጋር እንድንገናኝ የሚያነቃቃ ነው ብሏል።

ብዙውን ጊዜ ስለ ድኾች ሲነገር፡ ድኽነት እንደ አንድ ፅንሰ ሐሳብ ነው የሚተነተነው፡ ድኻው ወዳለበት ጎንበስ ብሎ ከማገልገል ይልቅ ድኽነት ርእስ አድርጎ እና አርቆ መተንተን የሚሻ ዓለም ውስጥ ነው ያለነው። ስለዚህ ዓለም አቀፍ የድኾች ቀን ከፅንሰ ሐሳብ ተላቆ በተጨባጭ ለተናናሾች ለድኾች ለተናቁት ለተረሱት በከተሞቻችን እና በህልውና ዳር ወደ ሚገኙት ሁሉ በማቅናት አብሮነትን በቃልና በሕይወት መመስከር እንዳለብን የሚያሳስብ ዕለት ነው፡ ድኾች የቤተ ክርስቲያን ማእከል ናቸው፡ ስለዚህ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በባንግላደሽ እና በሚያንማር የሚያካሂዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት ወንጌላውነት በተግባር እንዲኖር የሚያነቃቃ ለክርስቲያን የህሊና ምርመራ ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.