2017-10-31 14:30:00

ከሕግ ሁሉ የሚበልጠው ትልቁ ትእዛዝ ፍቅር ነው


ዘወትር እሁድ እለት በዓሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን እና የሀገር ጎቢኚዎች በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ አማክይነት በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ የሚደረገውን አስተንትኖ ለመከታተል በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እንደ ሚሰበሰቡ ይታወቃል። ቅዱስነታቸው በትላንትናው እለት ማለትም የጥቅምት 19/2010 ዓ.ም. ያደርጉት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ትኩረቱን አድርጎ የነበረው በእለቱ በላቲን የሥርዓተ አምልኮ ደንብ አቆጣጠር መሠረት በማቴዎስ ወንጌል ከምዕራፍ 22.34-40 ላይ በተጠቀሰው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ ያጠነጠነ እንደ እንደ ነበረ የታወቀ ሲሆን በዚህም የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ  አንድ የሕግ አዋቂ ኢየሱስን ሊፈትነው ፈልጎ መምህር ሆይ፥ ከሕግ ሁሉ የሚበልጠው ትልቁ ትእዛዝ የትኛው ነው? ብሎ በጠየቀው ጊዜ ኢየሱስም “ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነብስህ በፍጹም አሳብህ ውደድ። ይህም ታላቁና ቀዳሚው ትእዛዝ ነው። ሁለተኛውም ይህንን ይመስላል። ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትለው ነው” ብሎ እንደ መለሰለት በሚገልጸው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ ትኩረቱን ያደረገ እንደ ነበረም ለመረዳት ተችሉዋል። 

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች በማስከተል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ያደርጉትን የወንጌል ላይ አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዱሁ እንጋብዛለን።

የዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በዛሬው እለት የተነበበልን ቅዱስ ወንጌል አጠር ያለ ቢመስልም ነገር ግን በጣም አስፈላጊ የወንጌል ክፍል ነው። ዛሬ ወንጌላዊው ማቴዎስ ፈሪሳዊያን ኢየሱስን ለመፈተን አስበው ተሰብስበው እንደ ነበረ ይተርክልናል። ከእነርሱም መካከል አንዱ የህግ አዋቂ የነበረ አንድ ሰው ኢየሱስንከትእዛዛት ሁሉ የሚበልጠው ትልቁ ትእዛዝ የትኛው ነው?” በማለት ይጠይቀዋል። በሙሴ ሕግ ውስጥ ከስድስት መቶ በላይ የሚሆኑ ትእዛዛት እያሉ የተጠየቀ ጥያቄ በመሆኑ ይህ ጥያቄ መሰሪ የሆነ ጥያቄ ነው። ታዲያ ከእነዚህ ሁሉ ትእዛዛት መካከል ትላቅ የተባለውን ትእዛዝ እንዴት መለየት ይቻላል? ኢየሱስ ግን ምንም ሳያቅማማ በማቴዎስ ወንጌል 22.37 እና 39 ላይ እንደ ተጠቀሰውጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ሐሳብህ ውደድይህ የመጀመሪያውና ከሁሉ የሚበልጠው ትእዛዝ ነው፤ ሁለተኛውም ያንኑ ይመስላል፤ ይህም፣ጎረቤትህን እንደ ራስህ ውደድየሚለው ነውበማለት ይመልሳል።

ይህ የኢየሱስ መልስ  ተቀባይነት የለውም ምክንያቱም። በአይሁዶች ህግ ውስጥ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆኑት እግዚአብሔር በቀጥታ ለሙሴ ከህዝቡ ጋር የጋብቻ ቃል ኪዳኑን የመስረተበት አሥርቱ ትዕዛዛት ብቻ ስለነበሩ ነው። ነገር ግን ኢየሱስ ለእግዚአብሔርን እና ለጎረቤቶቻችን ፍቅር ካልሰጠን በቀር ከእግዚአብሔር ጋር በእውነተኛና  ታማኝ የሆነ ቃል ኪዳን መግባት እንደ ማይቻል ግልፅ ለማድረግ አስቦ የተናግረው ነው። ብዙ መልካም የሆኑ ነገሮችን ማድረ ትችል ይሆናል፣ ብዙ መልካም የሆኑ መመሪያዎችን ተግባራዊ ታደርግ ይሆናል፣ ፍቅር ከሌለህ ግን ሁሉም ነገር ዋጋ ቢስ ነው።

ይህም በሌላ መልኩ በኦሪት ዘፀአት መጽሐፍ ውስጥአንድ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ያሰረ ሰው በእግዚኣብሔር ጥበቃ ሥር በሚገኙ ሰዎች ላይ በደል መፈጸም እንደ ሌለበት ያርጋግጣል። መጽሐፍ ቅዱሳችን እንዲህ ይላልባል በሞተባት ወይም አባትና እናት በሌለው ልጆች ላይ፣ እንዲሁም መጻተኛውን (ሰደተኛ) አትበድሉት ወይም አታስጨንቁት፤ እናንተ በግብፅ መጻተኛ ነበራችሁናይላል በኦሪት ዘፀኣት 22.20-21

ይህንን ጥያቄ ላቀረቡለት ፈሪሳዊያን ኢየሱስ በሰጠው ምላሽ መንፈሳዊነታቸውን መስመር ለማስያዝ እና በእውነት በጣም አስፈላጊ ለሆነው ነገር በጣም አስፈላጊ ካልሆነው ነገር በተሻለ መልኩ ዋጋ ሊሰጡ እንደ ሚገባቸው ያስተምራል። ለዚህም ነው ኢየሱስሕግና ነቢያት በሙሉ በእነዚህ ሁለት ትእዛዛት ላይ የተንጠለጠሉ ናቸው።በማለት የመለሰላቸው።

ኢየሱስም በእነዚህ ሁለት ትእዛዝት ላይ በተመሰረተ መልኩ ነበረ ወንጌልን እየስበከ፣ በጣም አስፈላጊ እና ዋጋ ሊሰጠው ለሚገባው ነገር ቅድሚያ እየሰጠ ይህም ማለት ለፍቅር ከፍተኛ ቦታ እየሰጠ ነበር ስብከቱን ሲፈጽም የነበረው፣ ሕይወቱንም በዚሁ መልክ ነበር የኖረው። ፍቅር በፍጥነት እና ፍሬያማ በሆነ መልኩ  ወደ ሕይወት እና ወደ እምነት መንገድ ያመጣል፣ ያለ ፍቅር ሕይወታችን ይሁን እምነታችን መካን ሆነው ይቀራሉ። ኢየሱስ በዚህ ወንጌላዊ ክፍል ውስጥ ያቀረብልን ሐሳብ እጅግ በጣም ከልባችን ፍላጎት ጋር የሚስማማ ድንቅ መሻት ነው። በእርግጥ እኛ የተፈጠርነው ሰዎችን ለመውደድ እና እኛ ራሳችን ተወዳጅ ለመሆን ነው። ፍቅር የሆነ እግዚኣብሔር እኛን የፈጠረን የእርሱ ፍቅርና ሕይወት ተካፋዮች እንድንሆን፣ በእርሱ እንድንወደድ እና እርሱን እድንወደው፣ እንዲሁም ከእርሱ ጋር በመሆን ሁሉንም ሰዎች መውደድ እንድንችል ነው። ይህም እግዚኣብሔር ለሰው ልጆች ሁሉ የሚያልመውሕልምነው። ይህንንም ተጨባጭ በሆነ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ የእርሱ ፀጋ ያስፈልገናል፣ እንዲሁም ፍቅር ሁል ጊዜም ቢሆን የሚመነጨው ከእርሱ ከእግዚኣብሔር ዘንድ እንደ ሆነ የመረዳት ብቃት ያስፈልገናል። ኢየሱስ በቅዱስ ቁራባን መስዋዕት በመሆን ለእኛ የሚያቀርብልን ይህንኑ ፍቅር ነው። በቅዱስ ቁርባን የኢየሱስን ሥጋ እና ደም በምንቀበልባቸው ጊዜያት ሁሉ እርሱ ራሱን እኛን ለማዳን ፈልጎ ራሱን ለአባቱ መስዋዕት ያደርገበት ምስጢር በመሆኑ የእርሱን ታላቅ የሆነ ፍቅር እናገኝበታለን።

ይህንን ታላቅ የሆነ ለእግዚኣብሔር እና ለጎሬበቶቻችን ጥልቅ የሆነ ፍቅር ይኖረን ዘንድ ቅድስት እና ድንግል የሆነች እመቤታችን ማሪያም ትርዳን። አሜን!!

 








All the contents on this site are copyrighted ©.