2017-10-11 09:45:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ


እ.ኤ.አ. ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓም. እኩለ ቀን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ ከ 30 ሺሕ በላይ የሚገመቱ ከውጭና ከውስጥ የመጡ ምእመና በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በተገኙበት ከሐዋርያዊ መበራቸው መስኰት ሆነው ሰላምታን አቅርበው ጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር በመምራት ከምእመናኑ ጋር በሁባሬ ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ በላቲን ሥርዓት የእለቱ ከመደበኛው የሊጡርጊያ ግጽዊ 27ኛው እሁድ ከማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 21, 33-43 የተወሰደውን ምንባብ ተንተርሰው፥

 የዕርሻው ባለቤት፥ የገበሬዎችን እምነት ለመፈተን ዕርሻውን ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ፡  የመከር ወራት ሲደርስ ፍሬውን ለመቀበል የላካቸው አገልጋዮች ሁሉ የእርሻን ፍሬ እንሰጥም ባሉት ገበሬዎች እጅ ለሞት ይዳርጋሉ። በመጨረሻም ልጄን ያከብሩት ይሆናል ሲሉ ፍሬውን እንዲረከብለት ልጁን ይልካል። ይባስ ብለው ይኽማ ወራሹ ነው፡ እንግደለውና ርስቱን እንውረስ ተባብልው እርሱንም ይገድሉታል።

ይኽ ታሪክ በቀጥታ እኛንም ይመለከታል፡ ይኽ እግዚአብሔር ከሰው ዘር ጋር ስለ ገባው ሁላችን ሱታፌው እንዲኖረን ሲል ስላጸናው ቃል ኪዳን የሚናገር ነው።  እንደ ማንኛውም የፍቅር ታሪክ ሁሉ፡ ይኽ ታሪክ የገዛ እራሱ አወንታዊ ገጽታ አለው። የመካድና እምቢ ተባይነትንም ያጋጥመዋል። የዚህ የወንጌሉ ምሳሌ የመቋጫው ነጥብ፥ የወይኑ እርሻ ባለቤት በመጣ ጊዚ እነዚያን ገበሬዎች ምን የሚያደጋቸው የመስላችኋልየሚል ጥያቄ ነው። ሰዎች የሚሰቃዩበት ክፋት ለዚያ ቅር ለሚሰኘው እግዚአብሔር የመጨረሻ ቃል አይደለም።  እዚህ ላይ ነው የክርስትናው እምነት አዲስነቱ የሚገለጠው። በክፋታችንና በመሳሳታችን እግዚአብሔር ቅር ቢሰኝም ቃሉን ግን አይለውጥም፡ በሐጢአታችን አይገታም በተለይ ደግሞ መበቀልን አይሻም። እግዚአብሒር ያፈቅራ። የሚበቀል አይደለም። ምህረቱን ሊሰጠን በእቅፉ ሊያኖረን ይጥባበቀናል።

በደካማነታችንና ኃጢኣተኛታነችን ሁነት ምክንያት እግዚአብሔር የምህረቱን እዲሱን ወይን እርሱም ደሙን ያፈሳል፡ ነገር ግን ይኸንን የእግዝአብሔር ፍጹም መሐሪነት ወደ እኛ እንዳይደርስ የሚያግደው ነገር ቢኖር፥ ትምክህተኛነታችንና እብሪተኛነታችን ነው፡ ምክንያቱም ትምክህተኛነትና እብሪተኛነት አመጽ ስለ ሚሆንም ነው፡

የእግዚአብሔር ቃል በዚህ ዓይነቱ ሰብአዊ ጠባይና ምንም ዓነይነት ፍሬ በማይሰጥበት ሁነት ሁሉ፡ ምን እንደሚደርስብን የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ተወስዳ ፍሬዋን ለሚያፈራ ሕዝብ ትሰጣለችሲሉ ማስጠንቀቂያዎችና ነቀፋዎችን ሁሉ ግልጥ አድርጎ ያቀብልናንል፡ ምርጫው የእኛ ነው።

ይህ ፍሬ የማፍራቱ ተግባር የክርስትናው እምነት አዲስነቱ እና ቀዳሜ መለያው ይገኛል። ስለዚህ የክርስትናው እምነት የሥርዓቶችና የግብረ ገብ ሕጎች ድምር ማለት አለ መሆኑ ያስገነዝበናል። የክርስትናው እምነት የፍቅር ታሪክ ነው፡ የፍቅር ጥያቄ ነው፡ ይኽ የፍቅር ጥያቄ ለመላ ሰው ዘር በኢየሱስ አማካኝነት ዕለት በዕለት የሚቀርብ ነው፡ በዚህ የፍቅር ታሪክ የመግባት ጉዳይ ነው፡ የፍቅር ታሪክ በወይን ፍሬ የተሞላ በፍሬው ሃብታምና ለሁሉም ክፍት የሆነ የተስፋ ታሪክ ነው፡ ቅርብና እሩቅ ላሉት ሁሉ ክፍት ነው፡ ለሁሉም ሰው ዘር እግዚአብሔር የዘራው የወይን እርሻ ነው፡ ሁሉንም የሚያስተናግድ የሚቀበል ነው ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው እ.ኤ.አ. ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም. በሚላኖ ሰበካ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ብፅዕና ያወጀችለትን አባ አርሰኒዮ ዘትሪጎሎን በማሰብ፡ በዚህ የፍራንቸስካውያን ካፑቺን ንኡሳን አኃው አባል የአጽናኚቱ ቅድስት ማርያም ደናግል ማኅበር መሥራች ካህን ብፅዕ ትሁት የጌታ ደቀ መዝሙር በፈተና በመከራም ምንም ተስፋ ሳይቆርጥ ታማኝ ሆኖ ስለ ተገኘ እግዚአብሔርን እናወድስ ብለው ጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር ደግመው ሐዋርያዊ ቡራኪ ሰጥተው ሁሉንም ወደ መጡበጥ ማሰናበታቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.