2017-09-26 08:47:00

ዝክረ ሁለተኛው ዓመት የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለተባበሩት መንግሥታ አመሪካ ያስደመጡት ንግግር


የዛሬ ሁለት ዓመት ልክ እ.ኤ.አ. ከመስከረም 22 ቀን እስከ መስከረም 28 ቀን 2015  ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ዓለም አቀፋዊ ሓዋርያዊ ጉብኝት እካሂደው እንደነበርና፡ መስከረም 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ዋሽንግተን ተገኝተው በአገሪቱ የሕዝብ ተመራጮች ምክር ቤትና የሕግ መወሰኛው የበላይ ምክር ቤት በጣምራ በተገኙበት በአገሪቱ መንግሥት ምክር ቤተ ሕንፃ ተገኝተው ምክር ቤቱ ለይፋዊ ዓመታዊ ጉባኤ በተሰበሰበበት ወቅት ያስደመጡት ንግግር ዝክረ ሁለተኛ ዓመት ምክንያት በሮማ ለተባብሩት የአመሪክ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ካቶሊክ ኒውስ ሰርቪስ ለተሰየመው የዜና አገልግሎት ተጠሪ ሲድንይ ዉደን ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ በተባበሩ የአመሪካ መንግሥታት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፊት ተገኝተው ንግግር ሲያሰሙ ቀዳሜ ር.ሊ.ጳ. መሆናቸው ጠቅሰው፥ ያስደመጡት ንግግር ለተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ካቶሊክ ምእመናን ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንና ለአገሪቱ የፖለቲካ አካላት ፈታኝ ሆኗል። በአሁኑ ሰዓት የሚታዩት ተግዳሮቶች የዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ከነበሩት ጋር ሲነጻጸር እግጅ የተወሳሰበም ቢሆንም ቅሉ ሆኖም ዛሬ መለስ ብለን ስንመለከት ከካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በስተቀረ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት አግኝቶ እግብር ላይ ውሏል ለማለት ያዳግታል ብሏል።

ቅዱስ አባታችን የላቲን አመሪካ ተወላጅ መሆናቸው ማስታወስ ያስፈልጋል። በመሆኑም በሰሜን አመሪካና ደቡብ አመሪካ መካከል ለበለጠው የክልሉ ዘርፈ ብዙ እድገት አብሮ መሥራት ዕጣ ፈንታ መሆኑ ጠንቅቀው በቅርብ የሚያውቁት ጉዳይ ነው። ይኸንን ሲያሳስቡም ታላላቅ አራት የአመሪካ ልጆችን አብርሃን ሊንከን፡ ማርቲን ሉተር ኪንግ፡ ዶሮትይ ደይ እና ቶማስ መርቶንን በማጣቀስ እነዚህ አበይት የአገሪቱ ልጆች ነጻነት እኩልነት የመሳሰሉትን እሴቶች አማክለው የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት እንደ አገር ልትጸናባቸው በይገባል የሰጡት የቃልና የሕይወ አብነት የነበራቸው ህልም ነጻነት እኩልነት ውይይት ለድኾችና ለአናቁት ማሰብ የሚል እንደነበር ገልጠዋል ያሉት የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ብፁዓ ጳጳሳት ምክር ቤት የዜና አገልግሎት ተጠሪና ልእክት ጋዜጠኛ ዉድይ አክለው፥ ሆኖም እነዚህ እሴቶች አገሪቱ የተመሠረተችባቸው ሆነው እያሉ በአሁኑ ወቅት ትግባሬአቸው እጅግ የዛለ ይመስላል። ስደተኞችን ማስተናገድ፡ በሰሜን አመሪካ መሬት የሚገኙት ስደተኞችና ልጆቻቸው እንዲደገፉና የሰው ልጅ በሙላት ከተደገፍ ለሚስተናገድበት አገር ጫና ሳይሆን ዕድል እንደሚሆ የሚያብራራ ቅዱስ አባታችን ያሰመጡት ንግግር ታሪካዊ ነው፡፡ የዚያ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ንግግር መንፈሳዊ ውርሱ ወይንም ቅርሱ፥ በተለይ ደግሞ ለፖለቲካው ዓለምና በማኅበራዊ ዘርፍ ተጠምደው ለሚያገለግሉት ካቶሊካውያን ሁሉ፥ የሚሰጡት አገልግሎት ጥሪያዊ እንዲሆን የሚል ነው፡ ማንም ሰው የሚሰማራበት ዘርፍ ጥሪ መሆኑ አምኖ ከተቀበለ የሚሰጠው አገልግሎ ሰውን አገርን ሕዝብን የሚጎዳ ሊሆን አይችልም። በመሆኑም የፖሊቲካ አካላት በዚህ አገልግሎ እንዲሰማሩ የሚያርጋቸው እውነት የጥሪ ጉዳይ መሆን አለበት የሚል ነው፡ ሁሉም ይኸንን ከተረዳ በተሻለ ሁኔታ እንደምንገኝ አልጠራጠርም በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.