2017-09-23 09:15:00

ቅዱስ አባታችን፥ ተገቢ ያልሆነ አድራጎት በቤተ ክርስቲያ በዝምታና በትእግስት የማይታለፍ ግድፈት ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ለአቅመ አዳም ያልደረሱት ሕፃናት ጥበቃ ጉዳይ ድርገት አባላት ድርገቱ ለሚያካሂደው ጠቅላይ ዓመታዊ ምሉእ ጉባኤ መክፈቻ ምክንያት አገረ ቫቲካን የገቡትን ተቀብለው መሪ ቃል መለገሳቸው የቫቲካ ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኤማኑኤላ ካምፓኒለ ገለጡ።

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለአቅመ ኣዳም ባልደረሱት ሕፃናት ላይ የሚፈጸመው የወሲብ ዓመጽ በምንም ተአምር በዝምታ የማይታለፍና ምንም መታደግ  የማይገባው ጸረ ሰብአዊ ተግባር ነው፡ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያ ምንም’ኳ ችግሩን እውቅና ሰጥታበት ነቅታ ተገቢ ምላሽ በመስጠቱ ረገድ ይዘገየች እንደነበረች አስታውሰው። አንድ ችግር ዘግይቶ ሲስተዋል መፍትሔም እንደ መስተዋሉ ጭምር የዘገየ ነው የሚሆነው፡ ነገር ግን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን ችግሩ እንዲወጣ እውቅና አግኝቶ ተገቢ ምላሽ እንዲሰጥበ ያነቃቁ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ጽኑና ብርቱ ሰዎች ተነቃቅቱል። ችግሩን ፊት ለፊት እንዲታይ አድድርገዋ። የወሲብ ዓመጽ ሰለባ ስለ ሆኑት ጉዳይና ይኽ ከባድ ወንጀል በተመለከተ የአንቀጸ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር በመከታተል በማጣራት ረገድ አቢይ ጥረት እያደረገ ነው፡ ሆኖም በተገቢ ፍጥነት መጣራት የሚገባቸው ጉዳዮች አሁንም እንዳሉነው። ስለዚህ እሰኳይ ምልሽ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮችን ኣጣጥፎ መቀመጥ አያስፈልግም ካሉ በኋላ አክለው፥ በቤተ ክርስቲያን ተፈጽመዋል ስለ ሚባሉት በሕፃና ላይ የተፈጸሙ የወሲብ ዓመጽ ዙሪያ አንድ የጥናት ሰነድ አለ፡ ይኸንን ሰነድ በሚገባና በጥልቀት መርምሮ ተገቢ ምላሽ በመስጠቱ ረገድ የሚደረገው ሥራ ፈጣን እንዲሆን ለማድረግ የሰነዱ እጥኚ አባላት ቁጥር ከፍ እንዲል ተደርገዋል፡ ወንጀሉ መፈጸሙ በርግጠኝነት ማስረጃ ካለ የይግባኝ ጥያቄ ላለ መቀበል ግድ ይሆናል። የማይታበል ማስረጃ የቀረበበት ተከሳሽ ግለ ሰብ ወንጀለኛ ነው፡ በርግጥ ጤነኛም አይደለም። በፈጸመው በደል ታምኖ ቢጸጸትም በትክክል ከሁለት ዓመት በኋላ ይቅርታ ሊያገኝ ይችላል፡ ከተበየነበት ፍርድ ነጻ ነው ማለት ግን አይደለም እኔ ነጻ ተብሎ እንዲለቀቅ ምኅረት ይሰጥ ብየ አልፈርምም ፍርዱን በሚገባ ማጠናቀቅ ይኖርበታል እንዳሉ ካምፓኒለ ገለጡ።

ድርገቱ ከተቋቋመበት ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ያከናወናቸው ሥራዎች የሚመሰገን ነው። አንዳንድ የውሉደ ክህነት አባላት በፈጸሙት የወሲብ ዓመጽ ጥልቅ ሀዘንና ሀፍረትም ጭምር እንደተሰማኝና በይፋ ገልጫለሁ። በዚህ ብቻ ሳልወሰን ይኽ ድርገት ላቅመ አዳም ያልደረሱትን ዜጎች በመከላከሉ ረገድ ሊበረታና ጥልቅ እምነት የሚያስፈልገው በመሆኑም እምነቱን ሊያጎለበት የሚያግዙት መንገዶችን አብሬ በመጓዝ እያመላከትኩኝ እገኛለሁ። ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጠን ወንጌል ለአቅመ አዳም ያልደረሱትንና ገዛ እራሳችውን የመከላከሉ ብቃትም ሆነ አቅሙም የሌላቸውን እንከላከል ዘንድ ግድ ይለናል ጥሪያችንም ነው፡ የወንጌል ተልእኮም ነው፡

የወሲብ ዓመጽ ሰለባ የሆኑት የሰጡት ምስክርነት ቀርቤ ከአፋቸው ሰምቼዋለሁ። የወሲብ ዓመጽ ክርስቶስና ቤተ ክርስቲያን የምታስተምረው ትምህርት የሚጻረር ከባድ ኃጢአትም ነው። የወሲብ ዓመጽ ዙሪያ ቤተ ክርስትያን የምታካሂደው ትግል ዳግም በማረጋገጥ፡ በእግዚአብሔር ልጆች ላይ ይኸንን አሰቃቂው በደል የሚፈጽም ከፈጸመው ወንጀል ጋር የሚመጣጠን ተገቢ ፍርድ ሊያገኝ ይገዋል ካሉ በኋላ ቅዱስ አባታችን በተለያዩ አገሮች የሚገኙት የብፁዓ ጳጳሳት ጉባኤዎችና እንዲሁም የተለያዩ ገዳማትና መንፈሳዊ ማኅበራት ጠቅላይ አለቆች የዚህ ድርገት ምክር በመጠየቅ እያከናወኑት ያለው ትብብር የሚመሰገን ነው፡ ይኽ ድርገት በሌላው ረገድም ለእነዚያ የወሲብ ዓመጽ በተመለከተ የጠለቀ ግንዛቤውና ጉዳይ ለማጣራት አቅሙ ለሌላቸው የብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች አቢይ ድጋፍ እየሰጠ ነው፡ ከዓንቀጸ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበርና የአስፍሆተ ወንጌል ለአሕዛብ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ጋር የሚደረገው ትብብር እጅግ ወሳኝ ነው እንዳሉ   ካምፓኒለ አስታወቁ።

ቅዱስ አባታችን የድርገቱ ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ኦምለይና እንዲሁም የዚህ ድርገት መሥራች ከሆኑት ውስጥ ማሪየ ኮሊንስ በተለያየ መልኩ እየሰጡት ያለው የሕንጸት መርሐ ግብር አመስግነው፡ ድርገቱ ሰበካዎች መንፈሳውያን ማኅበራት ልኡካነ ወንጌል የካቶሊክ ተቛሞችም የወሲብ ዓመጽ አስቀድሞ መጠንቀቅ ዙሪያ እየሰጠው ያለው ሕንጸት እጅግ አስፈላጊ ነው። መቀጠልም ያለበት እቅድ ነው እንዳሉ የገለጡት ልእክት ጋዜጠኛ ካምፓኒለ አያይዘው፥ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያሰሙት ንግግር ሲያጠቃልሉ፡ ድርገቱና አባላቱ ለቅዱስ ማርያም አወክፈው ድርገቱ የወሲብ ዓመጽ ሰለባ የሆኑትን የሚያዳምጥ ስለ እነርሱ ፍትሕ እንዲቆም አሳስበው  ይኽ ወንጀል ጨርሶ ለማጥፋት የሚደረገው ትልግ ከባድና ብዙ ጥረት የሚጠይቅ ነው የሕጻናት መብትና ክብር ጥያቄ ውስጥ የማይገባ ጉዳይ  ስለ ሆነ በዚህ ጥረት መሰላቸት አይገባም እንዳሉም ጠቅሰው፡ 

በልጆች ላይ የሚደረግ ጥበቃ  አሁን በእኛ ዘመን በቤተክርስቲያኑ ካሉት ከፍተኛ ትኩረት ከሚሰጥባቸው መርሐ ግብሮች ውስጥ ቀዳሚ ነው፡ የወሲብ ዓመጽ ሰለባ የሆኑትና ቤተሰቦቻቸውም ጭምር ቤተ ክርስቲያን ቅርብ በመሆን በሁሉም ዘርፍ ተገቢ ድጋፍና ትኩረት ስጥታ ጥበቃ በማቅረብ ረገድ እያገለገለች መሆንዋ ብፁዕ ካርዲናል ሲን ኦማለይ የድርገቱን አባላትን በቅዱስ አባታችን ፊት አቅርበው ባስደመጡት ንግግር ያሰመሩበት ኃሳብ ሲሆን ቅዱስ አባታችን ስለ ሕፃናት ጥበቃ በመለከተ የሚሰጡት አስተህሮ ምክንያት ምስጋና ማቅረባቸው ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.