2017-09-19 13:50:00

የሰማያዊ ኣባታችን ኣብነት በመከተል ልባችንን የሚበድሉን ይቅር ብለን ልባችንን እንክፈትላቸው! ር.ሊ.ጳ


ቅ.ኣ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና እሁድ እኩለ ቀን ላይ የመልአከ እግዚኣብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት በዕለተ ቃለ ወንጌል ዙርያ ‘ይቅር ማለት የተፈጸመውን ጥፋት መቀበል ሳይሆን በእግዚአብሔር ኣርኣያ የተፈጠረው ሰው ከሚፈጽመው በደል እጅግ የላቀ መሆኑን ማወቅ ነው’ ሲሉ ኣስተምረዋል፣

ላቲናዊ ሥርዓተ ኣምልኮ በምትከተል ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ትናንትና የተነበበው ወንጌል የማቴዎስ ሆኖ ከምዕራፍ 18 ‘በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ወደ እርሱ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ልተውለት? እስከ ሰባት ጊዜን? አለው።  ኢየሱስ እንዲህ አለው። እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ አልልህም።’ የሚል ነበር፣  የዚህ ትርጉም ኣንድ ሁለት ብሎ እስከ ሰባ ግዜ ሰባት መቊጠር ሳይሆን ለሁሉ ግዜ መሆኑንም ገልጠዋል፣ ቃለ ወንጌል ቀጥሎ የሚያቀርበው ምሳሌም ይህንን ያረጋግጥልናል፣ ከሚከፍለው ኣጥሮ በብዙ ሺዎች የሚቆጠር ዕዳ የነበረው ታገሰኝ ሁሉን እከፍላለሁ ሲል ተማጥኖ ዕዳውን ሁሉ እንደተወለት እና ያ ነጻ የተበለ ሰው ሌላ ትንሽ ገንዘብ ሊከፍልለት የነበረ ጓደኛውን ኣግኝቶ እስከ እስር የወሰደ መጥሮ ሰው ምሳሌ ያብራረዋል፣

ይቅሬታ ተቀብሎ ይቅሬታን ለሌሎች መንፈግ እርስ በእርስ የሚጋጭ ሓሳብ ነው፣ እላይ በጠቅስነው ምሳሌ ንጉሱ እጅግ ሩህሩህ ሆኖ የለመነውን ኣገልጋይ ምሕረት ሰጥተዋል ነገር ግን ኣገልጋዪ ምህረት እዳገኘ ምህረት ኣይሰጥም፣ ምናልባት በዚሁ ኣገልጋይ ላይ እንፈርድ ይሆናል ነገር ግን እኛም ይቅሬታ ለሚጠይቁን ወንድሞቻች እምቢ ስንል እንመስለዋለን፣ እግዚአብሔር በምህረት እና ፍቅር እጅግ ሃብታም ስለሆነ ለዘለዓለም ያፈቅረናል ይምረናም፣ ይህንን የምሕረት ተግባር ወዲያውኑ ስንጠመቅ ይጀምረዋል፣ ስንጠመቅ በኣባታችን ኣዳም ሓጢኣት ምክንያት ከደረሰን ከባድ ዕዳ ነጻ ያወጣናል፣ ስለዚህ ስንጠመቅ ጀምሮ እግዚኣብሔር ዘወትር በምሕረት ዓይን እየተመለከተን ነው፣ ምሕረት በምሕረት ስለሚገኝም እኛ በበኩላችን የግድ ይቅር ማለትና ምሕረት መለገስ እንዳለብን በወንጌሉ ምሳሌ ያ መጥፎ ኣገልጋይ ምሕረት ተቀብሎ ምሕረት ኣልሰጥ ባለ ግዜ ጌታው ‘አንተ ክፉ ባሪያ፥ ስለ ለመንኸኝ ያን ዕዳ ሁሉ ተውሁልህ፤  እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህ የሆነውን ያን ባሪያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን?’ የሚለው ፍርድ ይጠባበቀናል፣

ምህረት ስትቀበል የሚሰማህ ደስታ ኣንተም መሓሪ እንድትሆን ጥሪ ያቀርብልሃል፣ እመቤታችን ድንግል በምህረት እግዚኣብሔር እንድንመስል ትርዳን፣ የእግዚኣብሔር ይቅር ማለት ለእያንዳችን ያለውን ኣባታዊ ፍቅር ያሳያል፣ ሲሉ ካስተማሩ በኋላ የመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት በማሳረግና ሓዋርያዊ ቡራኬ በመስጠት ሕዝቡን ኣሰናብተዋል፣ 








All the contents on this site are copyrighted ©.