2017-08-20 10:35:00

ር. ሊ. ጳ. ፍራንቸስኮ በሰራሊዮን በደረሰው የጎርፍ አደጋ በተጎዱ ሰዎች ማዘናቸው ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በላፈው ሰኞ እለት በሰራሊዮን በደረሰው የመረት መንሸራትና የጎርፍ አደጋ ሰላባ በሆኑ ሰዎች ማዘናቸው እና ከአደጋው ለተረፉ ሰዎች ያልቸውን አጋርነት መግለጻቸው ከላኩት የሐዘን መግለጫ  መልእክት ለመረዳት ተችሉዋል።

ቅዱስነታቸው በላኩት  የሐዘን መግለጫና አጋርነታቸውን በሚገልጸው መልእክት እንደ ገለጹት በዚህ አደጋ የተጎዱትን ሰዎች ለመርዳት ዓለማቀፋዊ የሆነ ርብርብ እንዲደረግ ጥሪ ማቅረባቸውም የታወቀ ሲሆን በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሀገራት የዚሁ አደጋ  ሰላብ የሆኑትን ሕዝቦች በተቻላቸው ፍጥነት እንዲያግዙ ጥሪ ማቀረባቸውም ታውቁዋል።

በዚሁ የጎርፍ እና የመረት መንሸራተት አደጋ ከ100 በላይ ሕጻናት የሚገኙበት 400 ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸው የተገለጸ ሲሆን አስክሬናቸውም በቁፋሮ እየወጣ በጅማላ መካነ መቃብር ውስጥ እየተቀበረ መሆኑንም ለመረዳት ተችሉዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚሁ ስፍራ ለብዙ ጊዜ መንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት የሚታወቁት አባ ቪንቼንሶ ሙናሪ ይህንን አደጋ አስመልክተው ከሬዲዮ ቫቲካን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደ ገለጹት አደጋው በጣም አስከፊ እንደ ሆነ ገልጸው በተለይም ደግሞ ከጥቂት ወራት በፊት ተከስቶ የነበረው የኢቮላ ወረርሽኝ ከፍተኛ ጉዳት አድርሶ ባለፈበት ማግሥት መከሰቱ አስደንጋጭ እና ልብን የሚነካ ክስተት እንደ ሆነ ገልጸዋል።

ከደረሰው የሞት ደጋ ባሻገር ከ600 በላይ ሰዎች ከቄያቸው በመፈናቀላቸው የተነሳ የዓለማቀፉ ማኅብረሰብ ክፍተኝ እርዳታ እንደ ሚያስፈልግ የገለጹት አባ ቪንቼንሶ በአደጋው ምክንያት ቤት ንብረታቸውን ሙሉ በሙሉ በማጣታቸው የተነሳ ለከፍተኛ ጉዳት ተጋልጠው የሚገኙ ሰዎች በመኖራቸው ይህንን ጉዳት በዘላቂነት ለመፍታት በቂ ዝግጅት እና የዓለማቀፉ ማኅብረሰብ ድጋፍ እንደ ሚያስፈልግም ጨምረው ገልጸዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.