2017-08-07 09:09:00

የሐምሌ 30/2009 ዓ.ም. የእለተ ሰንበት ምንባባት እና አስተንትኖ በአባ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ

የሐምሌ 30/2009 ዓ.ም. የእለተ ሰንበት ምንባባት እና አስተንትኖ

የእለቱ ምንባባት

  1.  ቲቶ 3:1-15 በጎ የሆነውን ማድረግ

    ሰዎች ለገዦችና ለባለ ሥልጣናት እንዲገዙ፣ እንዲታዘዙና መልካም የሆነውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ እንዲሆኑ አሳስባቸው። እንዲሁም በማንም ላይ ክፉ እንዳይናገሩ፣ ሰላማውያን እንዲሆኑ፣ ለሰዎችም ሁሉ ከልብ የመነጨ ትሕትና እንዲያሳዩ አስገንዝባቸው።

    ቀደም ሲል እኛ ራሳችን ማስተዋል የጐደለን፣ የማንታዘዝ፣ የተታለልን፣ ለተለያየ ምኞትና ምቾት ባሪያ ሆነን የተገዛን ነበርን፤ እየተጣላንና እርስ በርስ እየተጠላላን በክፋትና በምቀኝነት እንኖር ነበር። ነገር ግን የአዳኛችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ፍቅር በተገለጠ ጊዜ፣ ስላደረግነው የጽድቅ ሥራ ሳይሆን፣ ከምሕረቱ የተነሣ አዳነን። ያዳነንም ዳግም ልደት በሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ መታደስ ነው፤ ይህንም መንፈስ እግዚአብሔር በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእኛ ላይ አትረፍርፎ አፈሰሰው፤ ይኸውም በጸጋው ጸድቀን የዘላለምን ሕይወት ተስፋ ይዘን ወራሾች እንድንሆን ነው። ይህም የታመነ ቃል ነው። በእግዚአብሔር ያመኑቱ መልካሙን ነገር ለማድረግ ራሳቸውን አሳልፈው ይሰጡ ዘንድ እነዚህን ነገሮች አስረግጠህ እንድትናገር እፈልጋለሁ። ይህ መልካምና ለማንኛውም ሰው የሚጠቅም ነው።

    ነገር ግን ከንቱ ከሆነ ክርክርና ከትውልድ ሐረግ ቈጠራ፣ ከጭቅጭቅና ስለ ሕግ ከሚነሣ ጠብ ራቅ፤ ይህ ዋጋ ቢስና ከንቱ ነውና። መከፋፈል የሚያመጣን ሰው አንድ ጊዜ ምከረው፤ ለሁለተኛ ጊዜ አስጠንቅቀው፤ ከዚያ ካለፈ ከእርሱ ጋር አንዳች ነገር አይኑርህ። እንዲህ ዐይነቱ ሰው የሳተና ኀጢአተኛ ነው፤ ራሱንም እንደሚኰንን ዕወቅ።

  2. ለእግዚአብሔር መኖር 1 ጴጥሮስ 4:6-11 ይህን በመሰለ ብኩን ሕይወት ከእነርሱ ጋር ስለማትሮጡ እንግዳ ሆኖባቸው በመደነቅ ይሰድቧችኋል። ነገር ግን በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ ለተዘጋጀው መልስ ይሰጣሉ። ወንጌል ለሙታን እንኳ ሳይቀር የተሰበከው በዚህ ምክንያት ነው፤ ስለዚህ እንደ ማንኛውም ሰው በሥጋ ይፈረድባቸዋል፤ በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ይኖራሉ።

የዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

የሁሉ ነገር መጨረሻ ተቃርቦአል፤ ስለዚህ መጸለይ እንድትችሉ ንቁ አእምሮ ይኑራችሁ፤ ራሳችሁንም የምትገዙ ሁኑ። ፍቅር ብዙ ኀጢአትን ይሸፍናልና ከሁሉ በላይ እርስ በርሳችሁ ከልብ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ያለ ማጒረምረም እንግድነት ተቀባበሉ። እንደ ታማኝ የእግዚአብሔር ልዩ ልዩ ጸጋ መጋቢ እያንዳንዱ ሰው በተቀበለው የጸጋ ስጦታ ሌላውን ያገልግል፤ ከእናንተ ማንም የሚናገር ቢኖር እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢኖር እግዚአብሔር በሚሰጠው ብርታት ያገልግል፤ ይኸውም እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት እንዲከብር ነው፤ ክብርና ኀይል ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን፤ አሜን።

  1. የማርቆስ ወንጌል 6:47-56

እየሱስ በውሃ ላይ ተራመደ

በመሸም ጊዜ ጀልባዋ ባሕሩ መካከል ነበረች፤ እርሱም ብቻውን በምድር ላይ ነበር። ነፋስ በርትቶባቸው ስለ ነበር፣ ደቀ መዛሙርቱ ከመቅዘፊያው ጋር ሲታገሉ አያቸው፤ በአራተኛውም ክፍለ ሌሊት ገደማ፣ በባሕር ላይ እየሄደ ወደ እነርሱ መጣ፤ በአጠገባቸውም ዐልፎ ሊሄድ ነበር። ነገር ግን በባሕር ላይ ሲሄድ ባዩት ጊዜ ምትሐት መስሎአቸው ጮኹ፤ ሁሉም እርሱን ባዩት ጊዜ ደንግጠው ነበርና።እርሱም ወዲያውኑ አነጋገራቸውና፣ “አይዞአችሁ እኔ ነኝ፤ አትፍሩ!” አላቸው። እርሱም በጀልባዋ ላይ ወጥቶ አብሮአቸው ሆነ፤ ነፋሱም ተወ፤ እነርሱም እጅግ ተደነቁ፤ የእንጀራውን ታምር አላስተዋሉም ነበርና፤ ልባቸውም ደንድኖ ነበር።በተሻገሩም ጊዜ፣ ጌንሴሬጥ ደርሰው ወረዱ፤ ጀልባዋንም እዚያው አቆሙ። ወዲያው እንደ ወረዱም፣ ሕዝቡ ኢየሱስን ዐወቁት፤ ወደ አካባቢውም ሁሉ በመሮጥ ሕመምተኞችን በዐልጋ ላይ እየተሸከሙ እርሱ ወደሚገኝበት ስፍራ ሁሉ ያመጡ ነበር። በየደረሰበት መንደር ወይም ከተማ ወይም ገጠር ሁሉ ሕመምተኞችን በየአደባባዩ እያስቀመጡ የልብሱን ጫፍ እንኳ ለመንካት ይለምኑት ነበር፤ የነኩትም ሁሉ ይድኑ ነበር።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንዲሁም በጎ ፈቃድ ያላችሁ ሁሉ

እንደየ ተግባራችን ሳይሆን በምሕረቱና በቸርነቱ ደግፎን በጸጋውና በበረከቱ ሞልቶን፣ ተንከባክቦን ለእዚህች እለት ያደረሰን እግዚኣብሔር አምላካችን ስሙ ለዘልዓለም የተመሰገነ ይሁን።

በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ ኢየሱስ ያከናወናቸውን ሦስት ዋና ዋና ተግባሮችን እናገኛለን። በመጀመሪያም ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ተለይቶ ብቻውን ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣቱን የሚያመልክት ሲሆን ይህም እኛም ብንሆን ይህንን የኢየሱስን አራያ በመከትል ለራሳችን ጊዜ በመስጠት በጸጥታ ከእግዚኣብሔር ጋር በመሆን ብቻችንን ከእርሱ ጋር ማውራት መመካከር፣ የልባችንን ማካፈል የመንፈስ ደስታን ይሰጣል፣ ቡራኬንም እንደ ሚያስገኝ አወቀን ለእግዚኣብሔር ጊዜ መስጠት እንደ ሚገባን ያሳስበናል።

በሁለተኛ ደረጃ በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ  የተገለጸው የእየሱስ ድርጊት “በመሸም ጊዜ ጀልባዋ ባሕሩ መካከል በነበረችበት ወቅት ነፋስ በርትቶባቸው ስለ ነበር፣ ደቀ መዛሙርቱ ከመቅዘፊያው ጋር እየታገሉ በነበሩበት ወቅት ኢየሱስ በባሕር ላይ እየተራመደ ወደ እነርሱ መሚመጣበት ወቅት እረሱ ሌላ መንፈስ መስሎዋቸው ስለነበረ በፍርሃት እየጮኹ በነበሩበት ወቅት “አይዙዋችሁ አትፍሩ” በማለት ወደ ጀልባው ገብቶ ከእነርሱ ጋር በተቀመጠ ጊዜ አውሎንፋሱ ጸጥ እንዳለ የሚገልጽ ነው።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንዲሁም በጎ ፈቃድ ያላችሁ ሁሉ! ዛሬም ቢሆን እየሱስ አይዞአችሁ! እኔ ነኝ አትፍሩ! ይለናል።  

በዛሬው ወንጌል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅ የሆነ የምንፅናናበት ቃል ይናገረናል። በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ ይብዛም ይነስም የየራሳችንን ፍርሐት ወይንም ስጋት አለን፡፡ ይህ ከምን የመነጨ ይሆን? ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ስለምን እንዲህ ትፈራላችሁ? እስከዚህ እምነት የላችሁምን ይለናል፡፡ /ማር 4፡4ዐ/ ፍርሃት ምንድን ነው? ፍርሃት በሰው ሕይወት ውስጥ የሚከሰት የድንጋጤ ስሜት ነው፡፡ ይህ ስሜት አእምሮን ሲቆጣጠር ሰው በትክክል ማሰብና መስራት፣ የሚገባውን ማድረግ ወይም መሆን የሚገባውን መሆን ያቅተዋል፡፡ በእርግጥ በአጠቃላይ አነጋገር ሦስት አይነት ፍርሐት አለ፡፡

በሦስተኛ ደረጃ በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰው የእየሱስ ተግባር ደግሞ ባሕሩን በተሻገሩም ጊዜ፣ ወዲያው እንደ ወረዱም፣ ሕዝቡ ኢየሱስን አውቀውት ስለነበር፤ ወደ አካባቢውም ሁሉ በመሮጥ ሕመምተኞችን በአልጋ ላይ እየተሸከሙ እርሱ ወደ ሚገኝበት ስፍራ ሁሉ ያመጡ እንደ ነበረ፣ እነርሱም በየደረሰበት መንደር፣ ከተማና ገጠር ሕመምተኞችን በየአደባባዩ እያስቀመጡ የልብሱን ጫፍ እንኳ ለመንካት ይለምኑት ነበር፤ የነኩትም ሁሉ ይድኑ ነበር የሚለው ነው።

ኢየሱስ ወዲያውኑ ከጀልባው እንደ ወረደ ሕዝቡ ወዲያውኑ አውቁት ይለናል። ማርቆስ በዛሬው ወንጌሉ ከተለያዩ አከባቢዎች የተውጣጡ ብዙ ሕዝቦች ኢየሱስን ፍለጋ እንደ መጡ ይነግረናል። ታዲያ ይህን ያህል ብዙ ሕዝብ ኢየሱስን እንዲከተል ያነሳሳው ጉዳይ ምን ይሆን? ብለን መጠየቅ ተገቢ ይመስለኛል።

በዛሬው ቅዱስ ወንጌል እንደ ተጠቀሰው ይህ ሰፊ የሆነ ሕዝብ ኢየሱስን ፍለጋ የወጣበት ምክንያት ኢየሱስ የሚባለውን የእግዚኣብሔር ልጅ ለማየት ካደረባቸው ጉጉት የተነሳ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ከሕመማቸውና ከተለዩዩ ደዌዎቻችው ለመፈወስ ስለፈለጉ ጭምር ነው።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ

ታዲያ ዛሬ እኔና እናንተ እየሱስን የምንፈልገው ለምንድነው? ከሕመማችን፣ ከጭንቀታችን፣ ከሽክማችን ወዘተ. . . እንዲያድነን ስለምንፈልግ ነው? ብለን እራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል። ዛሬ የምንኖርበት ዓለማችን በብዙ ነገሮች ተወጥረን እንገኛለን። ታዲያ “አይዙዋችሁ አትፍሩ እኔ ነኝ” የሚለውን እየሱስ፣ በሕይወታችን ውስጥ በእየለቱ የሚነሳውን ማእበል ለማጥፋት ብቃት ያለውን እርሱን፣ በፍርሃት በምንዋጥበት እና የዚህ ዓለም ነገሮች እንደ ማእበል ሆነው ሕይወታችንን በሚያናውጡበት ሰዓት ይህንን የሕይወት ማዕበል “ጽጥ በል” ብሎ ሊያረጋጋን ብቃት ያለውን እየሱስን፣ የሕይወታችን ዋስትና ይሆን ዘንድ እንፈልገዋለን ወይ? መልሱን ለእያንዳዳችሁ እተዋለሁኝ።

እየሱስ የዚህ ምድር ተልዕኮውን በይፋ በጀመረበት ወቅት አገልግሎቱን በስፋት የጀመረው በየመንደሩ እይዞረ በማስተማር፣ በማጽናናት፣ የሞተን በማስነሳት፣ የታመመን በመፈወስ መሆኑን የማርቆስ ወንጌል ያስተምረናል።

ለምሳሌም ጊዜው ደርሶአል፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለች፤ ንስሓ ግቡ፤ በወንጌልም እመኑ” እያለ ከሰበከበት ከገሊላ አንስቶ፣ በቅፍርናሆም  በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገብቶ ማስተማር እንደ ጀመረ፣ ወደ በረሃ መሰደዱንና በዚያም ሕዝቡ ሊፈልገው መምጣቱን፣ በባሕር ዳር ቆጭ ብሎ ሕዝቡን ማስተማሩን፣ ከፍተኛ ወደ ሆነ ስፍራ በውጣት በዚያም ሕዝቡን የተራራው ላይ ስብከት ተብሎ ይሚታወቀውን መስበኩን፣ በእየደባባዩ እና በየከተማው እየተዘዋወረ ሕሙማንን መፈወሱን፣ የመሳሰሉትን ነገሮች እየሱስ በመፈጸሙ የተነሳ ከሕዝቡ ዘንድ አድናቆት ተችሮት ነበር። በእነዚህ እና እነዚህን በመሳሰሉት ምክንያቶች ነው እንግዲህ ሕዝቡ ኢየሱስን ለመፈለግ የሚወጣው።

እየሱስ በሕዝቡ የተፈለገበት ዋንኛው ምክንያት እርሱ በሽተኞቻችውን ስለፈወሰ፣ ስላዳቸው፣ ስለአበላቸው ስለአጠጣቸው ብቻ ሳይሆን ይፈልጉት የነበሩት ነገር ግን ከእነዚህ ሥጋዊ ፍልጎቶች ባሻገር በማርቆስ ወንጌል 6:34 ላይ እንደ ተጠቀሰው “ሕዝቡ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች” ተጥለው የነበሩ በመሆናቸው የተነሳ ጭምር ነው። ኢየሱስ ይህንን ታሪክ በመቀየር በየሰፈሮቻቸው፣ በየቄያቸው በየከተሞቻቸው ሳይቀር እየተዘዋወረ ያስተምር ስለነበር ይህ ትሕትናው እና ትጋቱ የሕዝቡን ልብ ቆርቁሮ አነሳስቶም ነበር። የስበከውን በሕይወቱ አሳይቱዋል፣ በሕይወቱ ተጨባጭ በሆነ መልክ የኖረውን ኑሮ በቃላት ስበኮታል። ከዚህም የምንረዳው ማንኛችንም ብንሆን ሰዎችን ወደ እኛ ለመሳብ ከፈለግን፣ የክርስቶስን ቃል በመጽናት መስብክ ከፈለግን፣ ስብከታችን ውጤታማ እና ፍሬያማ መሆን የሚችለው ቃላችን ከተግባራችን፣ ተግባራችን ደግሞ ከቃላችን ጋር የተገጣጠመ ሲሆን ብቻ እንደ ሆነ ከእየሱስ ሕይወት መማር እንችላለን። ስለዚህም በዛሬው እለተ ሰንበት እየሱስ ልባችንን ከማንኛውም ፍርሃት ያላቅቅልን ዘንድ፣ በኑሮዋችን እርሱን በመምሰል በመኖር ለሌሎች በረከት የምኖንበትን ጸጋ ይሰጠን ዘንድ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማሪያም አማላጅነት ልንልምነው ይገባል። የሰማነውን በልቦናችን ያሳድርልን። አሜን!

  1. በተፈጥሮ እግዚአብሔር ለሰው የሚሰጠው ፍርሃት፡ ለምሳሌ አደጋን በመፈራት የምንጠነቀቅበት፣ እሳትን ፈርቶ መሸሽ፣ መኪና እንዳይገጨን መሸሽ ወዘተ…
  2. ፈሪሃ እግዚአብሔር፡ ትክክል፤ አስፈላጊ ከማክበር የሚመነጭ ቅዱስ ፍርሃት ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ለመኖር፣ ትዕዛዙን ለመጠበቅ እግዚአብሔርን መፍራት መልካምና ትክክለኛ ነው፡፡ እግዚአብሔርን መፍራት እኛን ከኃጢያት አደጋ ከመጠበቁም በላይ የእግዚአብሔርን ክብር ዝቅ እንዳናደርግ ይረዳናል፡፡ ፈርሃ እግዚአብሔር ወደ እግዚአብሔር እና ወደ እውተኛው አምላክ የሚያደርሰን ጐዳና ነው፡፡
  3. ያልተገባ ፍርሃት፡- በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚብሔር ለብዙ ሰዎች “አትፍራ፣ አትፍሪ” በማለት ሲናገር እንሰማዋለን፡፡ ምንም ዓይነት ፍርሃት ይሆን እምነት የሚያዳክመውን፣ ንፁህ ራእይ እንዳይኖረን የሚጋርደን፣ ተስፋችንን የሚያጨልመውን፣ ተጠራጣሪ፣ በቃላችን እንዳንቆም የሚያደርገንን ዓይነት ፍርሃት ነው፡፡ በዛሬው ወንጌል የምናየው እውነት ይህንኑ ነው፡፡ ሐዋርያት የነበራቸው ውጣ ውረድ ወይም ማዕበል እንዲጠራጠሩ አደረጋቸው፡፡ ስለዚህ ጌታቸውን እንኳን መለየት እስኪያቅታቸው አይናቸውን ጋረዳቸው፡፡ ነገር ግን ጌታቸውና መምህራቸው ከእነርሱ ጋር መሆኑን በተረዱ ግዜ የጌታን ኃይል አዩ፣ ተደነቁ፣ መለኮታዊ ኃይሉን ተረዱ፡፡ እያንዳንዳችን በሚገጥሙን ማዕበሎች ጌታ ትቶኛል የምንልባቸው አጋጣሚዎች ብዙ ናቸው፡፡ ስለዚህ ውስጣችንን እንመልከት፣ ምናልባትም እሱ ሳይሆን እኛ እርቀን እንዳይሆን!

በሦስተኛ ደረጃ በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰው የእየሱስ ተግባር ደግሞ ባሕሩን በተሻገሩም ጊዜ፣ ወዲያው እንደ ወረዱም፣ ሕዝቡ ኢየሱስን አውቀውት ስለነበር፤ ወደ አካባቢውም ሁሉ በመሮጥ ሕመምተኞችን በአልጋ ላይ እየተሸከሙ እርሱ ወደ ሚገኝበት ስፍራ ሁሉ ያመጡ እንደ ነበረ፣ እነርሱም በየደረሰበት መንደር፣ ከተማና ገጠር ሕመምተኞችን በየአደባባዩ እያስቀመጡ የልብሱን ጫፍ እንኳ ለመንካት ይለምኑት ነበር፤ የነኩትም ሁሉ ይድኑ ነበር የሚለው ነው።

ኢየሱስ ወዲያውኑ ከጀልባው እንደ ወረደ ሕዝቡ ወዲያውኑ አውቁት ይለናል። ማርቆስ በዛሬው ወንጌሉ ከተለያዩ አከባቢዎች የተውጣጡ ብዙ ሕዝቦች ኢየሱስን ፍለጋ እንደ መጡ ይነግረናል። ታዲያ ይህን ያህል ብዙ ሕዝብ ኢየሱስን እንዲከተል ያነሳሳው ጉዳይ ምን ይሆን? ብለን መጠየቅ ተገቢ ይመስለኛል።

በዛሬው ቅዱስ ወንጌል እንደ ተጠቀሰው ይህ ሰፊ የሆነ ሕዝብ ኢየሱስን ፍለጋ የወጣበት ምክንያት ኢየሱስ የሚባለውን የእግዚኣብሔር ልጅ ለማየት ካደረባቸው ጉጉት የተነሳ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ከሕመማቸውና ከተለዩዩ ደዌዎቻችው ለመፈወስ ስለፈለጉ ጭምር ነው።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ

ታዲያ ዛሬ እኔና እናንተ እየሱስን የምንፈልገው ለምንድነው? ከሕመማችን፣ ከጭንቀታችን፣ ከሽክማችን ወዘተ. . . እንዲያድነን ስለምንፈልግ ነው? ብለን እራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል። ዛሬ የምንኖርበት ዓለማችን በብዙ ነገሮች ተወጥረን እንገኛለን። ታዲያ “አይዙዋችሁ አትፍሩ እኔ ነኝ” የሚለውን እየሱስ፣ በሕይወታችን ውስጥ በእየለቱ የሚነሳውን ማእበል ለማጥፋት ብቃት ያለውን እርሱን፣ በፍርሃት በምንዋጥበት እና የዚህ ዓለም ነገሮች እንደ ማእበል ሆነው ሕይወታችንን በሚያናውጡበት ሰዓት ይህንን የሕይወት ማዕበል “ጽጥ በል” ብሎ ሊያረጋጋን ብቃት ያለውን እየሱስን፣ የሕይወታችን ዋስትና ይሆን ዘንድ እንፈልገዋለን ወይ? መልሱን ለእያንዳዳችሁ እተዋለሁኝ።

እየሱስ የዚህ ምድር ተልዕኮውን በይፋ በጀመረበት ወቅት አገልግሎቱን በስፋት የጀመረው በየመንደሩ እይዞረ በማስተማር፣ በማጽናናት፣ የሞተን በማስነሳት፣ የታመመን በመፈወስ መሆኑን የማርቆስ ወንጌል ያስተምረናል።

ለምሳሌም ጊዜው ደርሶአል፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለች፤ ንስሓ ግቡ፤ በወንጌልም እመኑ” እያለ ከሰበከበት ከገሊላ አንስቶ፣ በቅፍርናሆም  በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገብቶ ማስተማር እንደ ጀመረ፣ ወደ በረሃ መሰደዱንና በዚያም ሕዝቡ ሊፈልገው መምጣቱን፣ በባሕር ዳር ቆጭ ብሎ ሕዝቡን ማስተማሩን፣ ከፍተኛ ወደ ሆነ ስፍራ በውጣት በዚያም ሕዝቡን የተራራው ላይ ስብከት ተብሎ ይሚታወቀውን መስበኩን፣ በእየደባባዩ እና በየከተማው እየተዘዋወረ ሕሙማንን መፈወሱን፣ የመሳሰሉትን ነገሮች እየሱስ በመፈጸሙ የተነሳ ከሕዝቡ ዘንድ አድናቆት ተችሮት ነበር። በእነዚህ እና እነዚህን በመሳሰሉት ምክንያቶች ነው እንግዲህ ሕዝቡ ኢየሱስን ለመፈለግ የሚወጣው።

እየሱስ በሕዝቡ የተፈለገበት ዋንኛው ምክንያት እርሱ በሽተኞቻችውን ስለፈወሰ፣ ስላዳቸው፣ ስለአበላቸው ስለአጠጣቸው ብቻ ሳይሆን ይፈልጉት የነበሩት ነገር ግን ከእነዚህ ሥጋዊ ፍልጎቶች ባሻገር በማርቆስ ወንጌል 6:34 ላይ እንደ ተጠቀሰው “ሕዝቡ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች” ተጥለው የነበሩ በመሆናቸው የተነሳ ጭምር ነው። ኢየሱስ ይህንን ታሪክ በመቀየር በየሰፈሮቻቸው፣ በየቄያቸው በየከተሞቻቸው ሳይቀር እየተዘዋወረ ያስተምር ስለነበር ይህ ትሕትናው እና ትጋቱ የሕዝቡን ልብ ቆርቁሮ አነሳስቶም ነበር። የስበከውን በሕይወቱ አሳይቱዋል፣ በሕይወቱ ተጨባጭ በሆነ መልክ የኖረውን ኑሮ በቃላት ስበኮታል። ከዚህም የምንረዳው ማንኛችንም ብንሆን ሰዎችን ወደ እኛ ለመሳብ ከፈለግን፣ የክርስቶስን ቃል በመጽናት መስብክ ከፈለግን፣ ስብከታችን ውጤታማ እና ፍሬያማ መሆን የሚችለው ቃላችን ከተግባራችን፣ ተግባራችን ደግሞ ከቃላችን ጋር የተገጣጠመ ሲሆን ብቻ እንደ ሆነ ከእየሱስ ሕይወት መማር እንችላለን። ስለዚህም በዛሬው እለተ ሰንበት እየሱስ ልባችንን ከማንኛውም ፍርሃት ያላቅቅልን ዘንድ፣ በኑሮዋችን እርሱን በመምሰል በመኖር ለሌሎች በረከት የምኖንበትን ጸጋ ይሰጠን ዘንድ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማሪያም አማላጅነት ልንልምነው ይገባል። የሰማነውን በልቦናችን ያሳድርልን። አሜን!

All the contents on this site are copyrighted ©.