2017-07-31 15:38:00

"የምንፈልገውን ክቡር የሆነ ሀብት ለማግኜት በልባችን ውስጥ የሚቀጣጠል ፍላጎት ሊኖረን ያስፈልጋል"።


ዘወትር እሁድ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን፣ ነጋዲያን እና የሀገር ጎብኚዎች በእለቱ በሚነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ መሰረቱን ያደረገ አስተንትኖ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ እንደ ሚሰጥ ይታወቃል፣ ቅዱስነታቸው የዚሁ መርዐ ግብር አካል በሆነ የትላንትናው እለት አስተንትኖዋቸው በማቴዎስ ወንጌል 13፡ 44- 52 የተጠቀሰው የተሸሸገው ሐብት ምሳሌ ላይ ትኩረቱን ያደረገ እንደ ነበረም ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች የዚህን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት እንደሚከተለው ተርጉመነዋል እንድተከታተሉን እንጋብዛለን።

የተወዳዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ

በዛሬው በማቴዎስ ወንጌል በ13ኛው ምዕራፍ ላይ የተጠቀሰው የኢየሱስ የተናገረው ምሳሌ ሰባት ወሳኝ የሆኑ ቃላትን አቅፎ የያዘ ሲሆን ይህ ምሳሌአዊ አነጋገር የተሸሸገ ሀብት፣ የዕንቁ ምሳሌ እና የዓሳ ማጥመጃ መረብ  በሚሉትን ሦስት ተመሳሳይ በሆኑ ምሳሌዎችን ያጠቃልላል። የመጀመሪያዎቹ ሁለት ምሳሌዎች ላይ የተጠቀሱት ሁሉንም ነገር በመሸጥ የገኙትን አዲስ ሀብት ለመግዛት በአጽኖት በወሰኑት ግጸባሕሪያት ላይ ባነጣጠረው ምሳሌ ላይ ለአፍታ ያህል ማትኮር እፈልጋለሁ።

የመጀመሪያው ምሳሌ ላይ አንድ ገበሬ በሚሠራበት የእርሻ ቦታ አንድ የተሸሸገ ሀብት ማግኘቱን ይተርካል። የዚህ የእርሻ ቦታ ባሌቤት እርሱ ራሱ ስላልነበረ ይህንን የተሸሸገ ሀብት የእርሱ ለማድረግ ይችል ዘንድ ይህንን የእርሻ ቦታ ሊገዛ ይገባዋል። ስለዚህም ይህንን የእርሻ ቦታ የእርሱ ለማድረግና ይህንን በጣም ወሳኝ የሆነ እድል ላለማጣት በመወሰን ቀደም ሲል የነበሩትን ሀብቶቹን ለአደጋ ወይም ለኪሳራ በሚያግልጥ መልኩ ለመሸጥ ወሰነ። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በጣም ጥሩ የሆነ ዕንቁ ለመግዛት የሚፈልግ አንድ ነጋዴን እንገኛለን። የዕንቁ ባለሙያ በመሆኑ የተነሳ አንድ ክቡር የሆነ ዕንቁ አገኘ። እርሱም ቢሆን ትኩረቱን በዚሁ በከበረው ዕንቁ ላይ በማድረግ ያለውን ሀብት ሁሉ በመሸጥ እርሱን ለመግዛት ይወስናል።

በእነዚህ ምሳሌዎች ውስጥ የተጠቀሱት መፈለግ የሚለውና የፈለጉትን ለማግኘት መሥዋዕትነት መክፈል የሚሉት ሁለት ተመሳሳይ ባህሪያት የእግዚኣብሔርን መንግስት ለማግኘት የሚደረገውን ጥረት በምስክርነት ያሳያሉ። የእግዚኣብሔር መንግሥት ለሁሉም በስጦታነት የቀረበ ጸጋ መሆኑ እሙን ቢሆንም ነገር ግን በአንድ በብር በተሰራ ሳህን ላይ ተቀምጦ ለእኛ የቀረበ ነገር ሳይሆን መፈለግ፣ መራመድ መሥራት ወይም መትጋት የሚሉትን ተለዋዋጭ እንቅስቃሴዎችን የሚጠይቅ ነው። የፍለጋችን ዓይነተኛ ባህሪ የፈለግነውን ነገር ለማግኘት ወሳኝ ነገር ነው። ያንን የምንፈልገውን ክቡር የሆነ ሀብት ለማግኜት በልባችን ውስጥ የሚቀጣጠል ፍላጎት ሊኖረን ያስፈልጋል፣ ይህም ማለት ኢየሱስ የእግዚኣብሔር መንግሥት መገለጫ መሆኑን ማወቅ ይገባል ማለት ነው። የተሸሸገው ክቡር የሆነው ሀብትና እንዲሁም ክቡር የሆነው ዕንቁ ኢየሱስ ራሱ ነው።  እርሱን ፈልገን ማግኜት በጣም መሰረታዊ እና ለሕይወታችንም ቢሆን ወሳኝ የሆነ ትርጉም ያለው ሕይወት ለመኖር እንችል ዘንድ ያስፈልገናል።

ይህንን ያልተጠበቀ አጋጣሚ ያገኙት በእርሻ ስፍራ ይሠራ የነበረው ሰው ይሁን ያ ነጋዴ የነበረው ሰው፣ ይህ ልዩ የሆነ አጋጣሚ እንዲያመልጣቸው ስላልፈለጉ ያላቸውን ሁሉ ለመሸጥ ወሰኑ። ለዚህ ውድ ለሆነ ሀብት ያላቸው ግምገማ ወይም አመለካከት መስዋዕትነት፣ ከሚወዱት ነገር መለየት ወይም የሚወዱትን ነገር መተው  የመሳሰሉትን ዋጋ ሊያስክፍላቸው የሚችል ውሳኔ ማድረግ ነበረባቸው።

ክቡር የሆነውን ሀብት እና ዕንቁ ባገኙ ጊዜ ይህም ማለት ጌታን ፈልገን በምናገኝበት ወቅት፣ ይህ አዲሱ ግኝት እንዳያመልጠን ያሉንን ነገሮች ሁሉ መስዋዕት ማድረግ ይኖርብናል። ይህም በመጀመሪያ ለክርስቶስ ቀዳሚ የሆነ ሥፍራን በመስጠት የቀሩትን ነገሮች መናቅ ማለት ነው። ለእርሱ ቀዳሚ የሆነ ሥፍራ መስጠት ጸጋ ነው። የክርስቶስ ደቀ መዝሙር የሆነ ሰው  መሰረታዊ የተባሉ ነገሮችን የተነፈገ ሰው  መሆን ማለት ሳይሆን ከሁሉም ነገሮች የሚበልጥ ነገር ያገኘ፣ ጌታ ብቻ ሊሰጠን የሚችለውን ምልአት ያለው ደስታን መጎናጸፍ ማለት ነው። ይህም ከህመማቸው የተፈወሱ፣ ኃጢአታቸው ይቅር የተባለላቸው፣ ሌባ ለነበረው ሰው የተከፈተው የመግሥተ ሰማይ በር የመሳሰሉትን ወንጌላዊ ደስታዎችን ያጎናጽፋል።

ኢየሱስን የሚገናኙ ሰዎች በወንጌል ደስታ ልባቸው እና ሕይወታቸው የሞላል። እርሱ ያድናቸው ዘንድ ራሳቸውን ለእርሱ ያስገዙ ሰዎች ከኃጢኣታቸው ይነጻሉ፣ ከሐዘናቸውም ይላቀቃሉ፣ ከነበራቸው የውስጣዊ ባዶነት ስሜትና ብቸኝነት ይላቀቃሉ። ሁል ጊዜም ቢሆን በዛሬ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሱት ያ ገበሬ የነበረ ሰው እና ያ ነጋዴ ያገኙትን ዓይነት ደስታ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ደስታችን በድጋሚ ይወለዳል። ይህም ደስታ ኢየሱስ ለእኛ ቅርብ በሚሆንበት ወቅቶች እና አጽናኝ የሆነው ኢየሱስ በውስጣችን በሚኖርበት ወቅት የሚገኝ ደስታ ነው። የኢየሱስ በውስጣችን መኖር ልባችንን በመቀየር የወንድሞቻችንን ፍላጎቶች እንድንመለከት እና እንድንቀበላቸው በተለይም ደግሞ ደካማ የሆኑትን ሰዎች እንድንቀርባቸው ያደርገናል።

እያንዳንዳችን በቃላት እና እለታዊ በሆኑ ተግባራት ክቡር የሆነውን ሀብት፣ ክቡር የሆነውን የእግዚኣብሔር መንግሥት አብ በልጁ አማክይነት የሰጠንን ፍቅር መመስከር እንችል ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንጋል ማሪያም በአማላጅነቱዋ ትርዳን። 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.