2017-07-27 11:14:00

በጳውሎስ 6ኛ የተጻፈው “Humanae Vitae" የተሰኘው ሐዋሪያዊ ምልእክት 50ኛ አመት በመዘከር ላይ ይገኛል።


እንደ የአውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በሐምሌ 25/1968 ዓ.ም (የዛሬ 50 አመት ገደማ ማለት ነው) በወቅቱ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ጳውሎስ ስድስተኛ በላቲን ቋንቋ ሁማና ቪቴ በአማሪኛው ሲተረጎም ሰባዊ ሕይወት በሚል አርእስት 10 ገጾች ያሉት ሐዋሪያዊ ምልእክት ማሳተማቸው ይታወሳል።

ይህ በላቲን ቋንቋ “Humanae Vitae” በአማሪኛው ሰባዊ ሕይወት በሚል አርእስት የታተመው ሐዋሪያዊ መልእክት የሰው ልጆች ሕይወት የሚመለከት ሐዋሪያዊ መልእክት ሲሆን በተለይም ደግሞ የትዳር ሕይወትን እና በትዳር ሕይወት ውስጥ የሚፈጥሩ ልጆች ተፍጥሮአዊ ሂደት በተከተለ ምልኩ መፈጠር እንደ ሚገባቸው የሚያሳስብ ሐዋሪያዊ መልእክት መሆኑም ይታወሳል። በተለይም በአስገዳጅ እና አደገኛ በሆነ የጤና እክል ባሻገር የሚካሄድውን የጽንስ ማስወረድ በከፍተኛ ደረጃ የሚቃወም ሐዋሪያዊ መልእክት ነው።

በአሁኑም ጊዜ ይህ Humanae Vitae” በአማሪኛው ሰባዊ ሕይወት በሚል አርእስት ሁለተኛው የቫቲካን ጉባሄ ከተጠናቀቀ ከ3 አመታት ቡኃላ የታተመው የጳውሎስ ስድስተኛ ሐዋሪያው መልእክት 50ኛ አመቱ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ እንደ ሚገኝ የተገለጸ ሲሆን በተለይም ይህ የዛሬ 50 አመት የታተመው ሐዋሪያዊ መልእክት ዛሬ ባለው የማኅበረሰብ ክፍል ውስጥ ሊኖረው የሚችለውን አዎንታዊ ወይም አሉታዊ የሆነ እንድምታ አጣርቶ ለማወቅ የተለያዩ ጥናቶች በመደረግ ላይ ይገኛሉ።

በሮም በሚገኘው በቅዱስ ጳውሎስ ሁለተኛ የስነ-ሕይወት የነገረ መለኮት ተቋም ውስጥ በአባ ጂልፍሬዶ ማሬኞ መሪነት በዚህ ሐዋሪያዊ መልእክት ዙሪያ ጥልቅ የሆነ ጥናት እየተካሄደ እንደ ሚገኝ የታወቀ ሲሆን ይህ Humanae Vitae” በአማሪኛው ሰባዊ ሕይወት የተሰኘው ሐዋሪያዊ መልእክት በብዙዎቹ ዘንድ ትንቢታዊ የሆነ ሐዋሪያው መልእክት እንደ ሆነ ተደርጎ ይቆጠራል።

ይህንን በተመለከተ ከሬዲዮ ቫቲካን ጋር ቆይታ ያደርጉት አባ ጂልፍሬዶ ማሬኞ እንደ ገለጹት ይህ ሐዋሪያዊ መልእክት ከ50 አመታት ቡኃላ ባለቺሁ የአሁኗ ቤተክርስቲያን ውስጥ ጠቃሚ የሆነ አስትዋጾ እያበረከተ እንደ ሚገኝ ጠቅሰው በተለይም ደግሞ ስነ-ሕይወትን በተመለከተ በትዳር ውስጥ የሚፈጠሩ ልጆች ተፈጥሮአዊ የሆነ ሂደትን ጠብቆ መምጣት ይኖርባቸዋል የሚለው አመለካከት በታዳር ሕይወት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ቦታ የተሰጠው መሆኑንም ገልጸው ይህም ለብዙ ጊዜያት ይህንን ግንዛቤ ሚዛኑን በጠበቀ መልኩ በነገረ መልኮታዊ አስተምህሮ ለመረዳት አዳግቶ የቆየ ጉዳይ እንደ ነበረም ጨምረው ገልጸዋል።

ይህ Humanae vitae በአማሪኛው ሰብዓዊ ሕይወት የተሰኘው ሐዋሪያው ምልእክት በይዘቱ በሁለት ባለትዳሮች መካከል ያለው ልዩነት የማይነጣጠል ዘላለማዊ የሆነ ግንኙነት መሆን እንዳለበትና በተጨማሪም በትዳር ውስጥ የሚፈጠሩ ልጆች ተፈጥሮአዊ ሂደት በተከተለ መልኩ መምጣት እንደ ሚገባቸው፣ በተጨማሪም ሰው ሰራሽ የወልዲ መከላከያ መጠቀም አስፈላጊ አለመሆኑን አበክሮ የሚያሳስብ መሆኑን በመግለጽ፣ ይህ ሐዋሪያዊ መልእክት አሁን ባለንበት ዘመን ከሚታየው ነባራዊ ሁኔታ ጋር እንዴት አጣጥሞ መሄድ ይችላላል? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው በሮም ከተማ የሚገኘው የቅዱስ ጳውሎስ ሁለተኛ የስነ-ሕይወት ነገረ መለኮት ተቋም ውስጥ የሚካሄድውን ምርምር የሚያስተባብሩት አባ ጂልፍሬዶ ማሬኞ ይህ ጉዳይ አሁን ካለው ነባራዊ እውነታ ጋር ተጣጥሞ እና ዋና ዋና የሚባሉ እሴቶችን ጠብቆ እንዲሄድ የሚያስችል ጥናት እየተደረገ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።

የሁለተኛው የቫቲካን ጉባሄ ካጸደቃቸው 16 ሰንዶች መካከል ባላቲን ቋንቋ “Gaudium et Spes” በአማሪኛው ደስታና ተስፋ በሚለው ሰንድ ውስጥ ቤተክርስቲያን ነባራዊ የሆነውን የማኅበረሰቡን ተጨባጭ እውነታ ከግምት ባስገባ መልኩ በቀዳሚነት በምስጢረ ተክሊል የተፈጸመ ታዳርንና ቤተሰብን የመከባከብ ኃልፊነት እንደ ተጣለበት የገለጹት አባ ጂልፍሬዶ የክርስቲያን ማሕበረሰብ የተጠራው በጊዜው እና በወቅቱ ያሉትን የኅብረተሰብ ክፍል ለመገናኛት መሆኑን ጨምረው ገልጸው ሰብዓዊ የሆነ ተግዳሮቶቻቸውን ከግምት ባስገባ መልኩ ክርስቲያናዊ እሴቶችን ጠብቆ መጓዝ እንድችሉ መርዳት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.