2017-07-24 15:35:00

"በመልካምና በክፉ ነገሮች መካከል ያለውን ድንበር የሚከፋፍለው መስመር የሚያለፈው በእየአንዳንዳችን ልብ ውስጥ ነው”


“ሁላችንም ኃጢኣተኞች በመሆናችን የተነሳ በመልካም እና በክፉ ነገሮች መካከል ያለውን ድንበር የሚከፋፍለው መስመር የሚያለፈው በእየ አንዳንዳችን ልብ ውስጥ ነው” ይህንን ቀደም ሲል የታደማችሁትን ቃል የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ሲሆኑ፣ ይህንንም የተነጋሩት በትላንትናው እለት ማለትም በሐምሌ 16/2009 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ነጋዲያን፣ ምዕመናንና የሀገር ጎብኝዎች በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ መሰረቱን ባደረገው አስተንትኖዋቸው ከተናገሩት የተወሰደ ነው።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

በእለቱ ቅዱስነታቸው ያደረጉት አስተንትኖ በላቲን የርስዓተ አምልኮ አቆጣጠር እና ደንብ መሰረት ከማቴዎስ ወንጌል 13:24-43 ላይ በተወሰደው የእንክርዳድ ምሳሌ ላይ መሰረቱን ያደረገ እንደ ነበረም ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ይህም “በዓለማችን ውስጥ በአሁኑ ወቅት እየተንጸባረቁ የሚገኙትን ችግሮች በማመልከት “እነዚህም ችግሮች የሚቀረፉት እግዚኣብሔር በምልአት ሲገለጽ ብቻ መሆኑንም ገልጸው “እግዚአብሔር ለእኔ ምን ያህል ትዕግስት ነው የሚያሳየኝ?” የሚለውን ጥያቄ እያንዳንዳችን ለራሳችን ማቅረብ የሚገባን ጥያቄ ነው ብለዋል።

“በዚሁ የእንክርዳዱ ምሳሌ ላይ የተጠቀሰው የእርሻው ባለቤት እግዚኣብሔርን ይወክላል፣ በዚህ ምሳሌ ውስጥ የተጠቀሰው ጠላት ደግሞ ሰይጣንን ይወክላል” በማለት አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው መልካም የሆነውን ዘርና መልካም ያልሆነ የእንክርዳድ ዘር፣ ሁለቱንም ዓይነት ዘሮች የዘሩ ሁለት ዓይነት ሰዎች በዚህ ምሳሌ ውስጥ መጠቀሳቸውን አስታውሰው አገልጋዮቹ ወደ የእርሻው ባለቤት ቀርበው “ታዲያ ሄደን ይህንን እንክርዳድ እንድንነቅል ትፈልጋለህን?” ብለው በጠየቁት ጊዜ የእርሻው ባለቤት “አይሆንም እንክርዳዱን ስትንቅሉ፣ ስንዴውንም አብራችሁ ትንቅላላችሁ፣ ሰለዚህ ተውአቸው እስከ መከር ጊዜ ድረስ ስንዴውም እንክርዳዱም አብረው ይብቀሎ ብሎ እንደ መለሰላቸው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ኢየሱስ ይህንን ምሳሌያዊ አነጋገር ተጠቅሞ በእዚህ ዓለም ውስጥ የሚገኙ መልካም የሚባሉ ነገሮች እና ክፉ ነገሮች ለመለየት በሚያዳግት ሁኔታ የተሳሰሩ መሆናቸውን እና ክፉ የሚባሉ ነገሮችን ሙሉ ለሙሉ ነቅሎ ከዓለም ለማጥፋት የማይቻል መሆኑን ለማሳየት ፈልጎ የተጠቀመው ምሳሌ እንደ ሆነም ገልጸዋል።

“ይህንን ማድረግ የሚችለው እግዚኣብሔር ብቻ ነው፣ ይህንንም የሚያደርገው በመጨረሻው የፍርድ ቀን ላይ ነው “በማለት አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ስለዚህ አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ የሰዎችን ነጻነት በአሻሚነትና በተቀነባበረ ስብዕና የሚያሳይ በመሆኑ የተነሳ በተለይም ደግሞ የክርስቲያኖች ነጻነትን በተመለከተ ማለት ነው በእነዚህ እና እነዚን በመሰሉ የተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ በመልካም እና በክፉ ነገሮች መካከል ያለውን ልዩነት በትክክለኛው መንገድ ውስኖ ለመለየት ያዳግታል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በእለቱ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች እንደ ገለጹት ውሳኔ ማድረግ እና ትዕግስት በሚሉት ሁለት ተቃራኒ የሆኑ ባሕሪያትን ለማገናኘት መሞከር እንደ ሚገባቸው ጠቅሰው ይህም እንክርዳድ ሳይሆን መልካም የሆነ የስንዴ ሰብል ለመሆን መላው ኃይላቸውን አስተባብረው መወሰን እንደ ሚኖርባቸው አበክረው ገልጸዋል።

በእለቱ ቅዱስነታቸው በማቴዎስ ወንጌል ላይ በተጠቀሰው የእንክርዳዱ ምሳሌ ላይ ተመርኩዘው ያደረጉት አስተንትኖ መአከሉን ያደረገው “ሁላችንም ኃጢኣተኛ መሆናችንን ማወቅ ይኖርብናል” በሚል ጭብጥ ዙሪያ ያጠነጠነ እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን መልካም እና ክፉ የሚባሉ ነገሮች አንድ የተወሰነ ሥፍራ ወይም ደግሞ የተወሰኑ የሰው ልጆች  ብቻ ላይ የሚገኙ ነገሮች እንዳልሆኑ እንድንገነዘብ ዛሬ ጌታ ይረዳናል ብልዋል።

ሁል ጊዜ ከእኛ ውጭ የሚታዩትን ክፉ ነገሮችን የምንመለከት ከሆንን እኛ ራሳችን ውስጥ የሚገኘውን ኃጢኣት ለመመልከት ፍላጎት ሊኖረን በፍጹም አይችልም ያሉት ቅዱስነታቸው በእርግጥ ከኃጢኣታችን የሚያነጻን እና በአዲስ የሕይወት ጎዳና ላይ እንድንራመድ የሚረዳን ጸጋ የሚሰጠን ኢየሱስ ብቻ መሆንኑን ጠቅሰው ሚስጢረ ንሰሐን ጌታ የሰጠን ከኃጢኣቶቻችን ሁሉ እንድንነጻ ስለፈለገ ነው ብለዋል።

በዓለም ውስጥ ያሉትን ክፉ ነገሮች ቢቻ ሳይሆን መልካም የሆኑትንም መመልከት እንችል ዘንድ፣ የሰይጣንን ተግባራት በማጋለጥ፣ በተለይም ደግሞ ታሪክን መቀየር በሚችለው በእግዚኣብሔር ተግባራት በመታመን መጓዝ እንችል ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ትረዳን ዘንድ መማጸን ያስፈልጋል ካሉ ቡኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን አስተንትኖ አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.