2017-06-16 15:29:00

“ደካሞች፣ ለጥቃት ተግላጮች፣ ኃጢኣተኞች እንደ ሆንን ልብ ልንል ይገባል”።


“ደካሞች፣ ለጥቃት ተግላጮች፣ ኃጢኣተኞች እንደ ሆንን እና የእግዚኣብሔር ኃይል ብቻ የሚያድን እና የሚፈውስ መሆኑን ልብ ልንል ይገባል”። ይህ የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ሲሆኑ በዛሬው እለት ማለትም በሰኔ 9/2009 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ካሰሙት ስብከት የተወሰደ ነው።

“ማንኛችንም ብንሆን ራሳችንን በራሳችን ማዳን አንችልም” በማለት የእለቱን ስብከት የጀመሩት ቅዱስነታቸው ለመዳን የእግዚኣብሔር ኃይል በከፍተኛ ሁኔታ ያስፈልገናል ብለዋል። በእለቱ በላቲን የስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት በቀዳሚነት ከተነበበው እና ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ ላይ “ይህንን ክቡር ነገር እንደ ሽክላ ዕቃ ሆነን ይዘነዋል” (2ቆሮንጦስ 4፡7) ተብሎ በተጠቀሰው ስለ ክርስቶስ ምስጢር በሚገልጸው ቃል ላይ ተመስርተው “ሸክላ ዕቃ፣ ደካሞች እና ኃጢኣተኞች መሆናችንን ልብ ልንል ይገባል ብለዋል። ያለእግዚኣብሔር ኃይል በፍጹም ወደ ፊት መጓዝ አንችልም በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ክቡር የሆነው ክርስቶስ እንደ ሸክላ ዕቃ ተሰባሪ በመሆኑ በደካማነታችን ውስጥ እንኳን ይገኛል፣ ምክንያቱም የእግዚኣብሔር ኃይል የማዳን፣ የመፈወስ እና ተመልሰን በእግራችን እንድንቆም የማድረግ ኃይል ስለ አለው ነው ብለዋል።

ሁላችንም ብንሆን ለጥቃት የተጋለጥን፣ እንደ ሸክላ ዓቃ ተሰባሪ፣ ደካሞች በመሆናችን የተነሳ  ከእነዚህ ነገሮች መፈወስ ይኖርብናል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ሐዋሪያው ጳውሎስ “ወዳጆች አጥተናል፣ ተመተናል፣ ተሰድበናልም”  በማለት ደካማ መሆናችንን ገልጾታል ያሉት ቅዱስነታቸው ይህ ተሰባሪ የሸክላ ዕቃ እንደ ሆንን ያሳያል ብለዋል።  ይህም ለጥቃት የተጋለጥን መሆናችንን ያሳያል ያሉት ቅዱስነታቸው በሕይወት ውስጥ በጣም አስቸጋሪ የሆነ ተግባር የሆነው ለጥቃት ተጋላጮች መሆናችንን አለማወቃችን ነው ብለዋል። አንዳንድ ጊዜም ለጥቃት ተጋላጭ መሆናችንን ሌሎች ሰዎች እንዳያዩብን ስለምንፈልግ ለመደበቅ እንሞክራለን  አንዳንዴም የመኳኳያ ግብዐቶችን በመጠቀም ለመሸፈን እንሞክራለን በማለት ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት “ይህም እኛን ወደ እብሪት፣ ኩራት፣ በቀላሉ የማንሰበር እና ለጥቃት ተጋልጭ እንድልሆንን እንዲሰምን በማድረግ ደኅንነትን በራሳችን ኃይል እንደ ተጎናጸፍን እና ራሳችን በራሳችን ምልአት እንዳለን እንዲሰማን ወደ ሚያደርገን ጎዳና ይመራናል ካሉ ቡኃላ የሚያድነን የእግዚኣብሔር ኃይል ብቻ ነው ካሉ ቡኃላ ምክንያቱም የኛን ለጥቃት ተጋላጭነትን በተመለከተ ሐዋሪያው ጳውሎስ “በየአቅጣጫው መከራ ደርሶብናል ግን አንሸነፍም” ብሎ ለጥቃት ተጋላጭ መሆናችንን እንደ ገለጸ ሁሉ የሚያድነው የእግዚኣብሔር ኃይል ከእኛ ጋር ስላለ መቼም ቢሆን አንሸነፍም ብለዋል።

ለጥቃት ተጋላጭ መሆናችንን ማወቃችን እኛን ልያስደነግጠን ይችል ይሆናል  ተስፋ ሊያስቆርጠን ግን አይገባም ምክንያቱም ተስፋን የሚሰጠን እግዚኣብሔር ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ብዙ ጊዜ ተሰደናል ነገር ግን ወዳጆች አጥተን አናውቅም፣ ተመትተን እንወዳቃለን ነገር ግን አንሞትም”፣ ከሚለውን የሐዋሪያው ጳውሎስ ቃል ጠቅሰው ሁል ጊዜም ቢሆን የሸክላ ዕቃ በሚለው እና የእግዚኣብሔር ኃይል በሚለው  ቃላት መካከል ጥብቅ የሆነ ግንኙነት በመኖሩ የተነሳ ምንም እንኳን ተሰባሪ የሸክላ ዕቃ ብንሆንም በውስጣችን ክቡር የሆነ ነገር እንዳለ ማወቅ ይኖርብናል ብለዋል።

ሐዋሪያው ጳውሎስ በዚሁ መልኩ “እንድናስብ፣ ምክንያታዊ እንድንሆን በዚህ መልኩ ብቻ የእግዚኣብሔርን ቃል መስበክ እንደ ሚገባን ያስተምረናል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ሁል ጊዜም ቢሆን ተሰባሪ የሆንን የሸክላ ዕቃ እንደ ሆንን ነገር ግን ውስጣችን ክቡር እና ውድ የሆነ ነገር እንዳለ መገነዘብ ይስፈልጋል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማጠቃለያ ላይ እንደ ገለለጹት በመልካም ስሜት ተነሳስተን “ለጥቃት ተጋላጭ፣ እንደ ሸክላ ዕቃ ተሰባሪ፣ ደካሞች እና ኃጢኣተኛ “ መሆናችንን መገነዘብ ያስፍልጋል ካሉ ቡኃላ ተሰባሪ የሸክላ ዕቃ መሆናንን ስንቀበል ብቻ ነው “ወደር የሌለው የእግዚኣብሔር ኃይል ወደ እኛ መጥቶ ምልአት፣ ደኅንነት፣ ደስታ እና በመዳናችን እንድንደስት” የሚያደገን ክቡር እና ውድ የሆነ ጌታን መቀበል የምንችለው በዚሁ መልኩ ብቻ ነው ካሉ ቡኃል ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.