2017-06-14 16:59:00

ወጣት እምነትና ጥሪን መለየት በተሰኘው ርእስ ዙሪያ ለሚመክረው ሲኖዶስ ድረ ገጽ (ድረ ጣቢያ)


የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት እ.ኤ.አ. በወርሓ ጥቅምት 2018 ዓ.ም. ወጣት እምነትና ጥሪን መለየት በሚል ርእስ ሥር እንዲካሄድ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የጠሩት ሲኖዶስ ማሰናጃ የሚሆን የገዛ እራሱ ድረ ገጽ (ድረ ጣቢያ) እ.ኤ.አ. ከሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ላገልግሎት መዋሉ የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት ያሰራጨ መግለጫ የጠቀሱ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አመለከቱ።

ይኽንን ወጣት እምነትና ጥሪን መለየት በሚል ርእስ ሥር የሚመክረው 15ኛው ጠቅላይ መደበኛው ሲኖዶስ ማሰናጃ  youth.synod2018.va በሚል አድራሻ የተደረሰው ሲሆን፡ ዋና ዓላማውም በመላ ዓለም የሚገኙት ወጣቶች ሊካሄድ ስለ ተወሰነው ሲኖዶስ በተመለከተ ለሚሰጡት መግለጫዎችና ዜናዎች ተቀባይ ብቻ ሳይሆን በዚህ እነርሱን ማእከል በማድረግ እንዲወያይ በተጠራው ሲኖዶስ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ማሳተፍ የሚል መሆኑ የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት ያሰራጨው መግለጫ የጠቀሱት ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ እያይዘውም፡ ድረ ገጹ በቀጥታ ወጣቶችን የሚመለከት ይድረስ ለወጣት ትውልድ በሚል እ.ኤ.አ. እስከ ህዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም. ባለው የጊዜ ገደብ ውስጥ ብቻ መልስ የሚሰጥበት በጣልያንኛ በእንግሊዝኛ በፈረንሳይኛና በፖርቱጋል ቋንቋዎች የመጠይቅ ሰነድ የተኖረበት መሆኑ ገልጠዋል።

የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የተጠራው ሲኖዶስ በመላ ዓለም የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ጉኤዎች አማካኝነት በሚያቀርበው መጠይቅ በሁሉም ደረጃዎች ሕዝበ እግዚአብሔር እያሳተፈ ሲሆን፡  ወጣቱ በዚህ ወጣቱ ማእከል በሚያደርገው ሲኖዶስ በበለጠ ማሳተፍ የላቀ ምክንያት ያለው በመሆኑም፡ ስለዚህ ለሚካሄደው ሲኖዶስ በቀጥታም ሆኖ በተዘዋዋሪም ወጣቱን ማሳተፍ ለማሰናጃው ሂደት አቢይ ግባት መሆኑ አምኖበት ከወጣቱ መልስ የሚሰጥበት መጠይቅ እንዲታከል የማድረጉ ምክንያት ለይቶ በሰጠው መግለጫ እንዳብራራው ጂሶቲ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.