2017-06-02 16:23:00

ብፁዕ ካርዲናል ስተላ፥ ወጣት ካህናት በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ልብ ውስጥ ናቸው


የካህናት ጉዳይ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል በኒያሚኖ ስተላ በዚህ በሳቸው በሚመራው ቅዱስ ማኅበር ባሰናዳው ዓውደ ጉባኤ የሚሳተፉትን በመሸኘት ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር ተገናኝተው ውይይት በማካሄድ መሪ ቃል ተቀብለው ልክ እንደተሰናበቱ ከቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ ያንን የዛሬ 47 ዓመት ገደማ Ratio fundamentalis - መሰረታውያን አመክንዮ (መመዘኛዎች) በሚል ርእስ ሥር ከኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ውሉደ ክህነት ማእከል ያደረገ ሰነድ ግምት የሰጠ “Ratio fundamentalis institutionis   መሠረታዊ አመክንዮ ለክህነታዊ ሕንጸት”  በሚል ርእስ ሥር የካህናት ጉዳይ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ያወጣው ስለ የካህናት ሕንጸት ጉዳይ የሚዳስስ በክህነታዊ ሕንጸት ማእከላዊ መሠረተ ነገሩ ለይቶ በአጽንዖት የሚተነትን፡ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ስለ ካህናትና ክህነት ዙሪያ ወጣት ካህናቶችን ተቀብለው የሰጡት ምዕዳን ኣስትንፋሶ ያደረገ ሰነድ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በበዓለ ጽንሰታ ለማርያም ይፋ መደረጉ አስታውሰው፥ ሰነዱ የካህናት ሕንጸት የሚጀምረው ገና ወጣቱ የመንበረ ታቦት አገልጋይ እያለ ነው። በርግጥ ሕንጸቱ ወደ ሰማያዊ አብ እስከ ምንመለስበት ቀን ካለ ማቋረጥ የሚቀጥል ቢሆንም የሕንጸቱ ደረጃ የመንበረ ታቦት አገልጋይ ከዛም የዘርአ ክህነት ተማሪ እያለም ክህነት ከተቀበሉ በኋላም ቋሚ ሕንጸት እየተባለ ተከፋፍሎ የሚቀርብ ነው። ለብፁዓን ጳጳሳትና የካህናት ሕንጸት አለቆች ይኸንን ኃላፊነት በጥንቃቄና በጠና መንፈስ ይወጡት ዘንድ አሳስበናል። ምክንያቱም ዛሬ በቤተ ክርስቲያንና በኅብረተሰብ ፊት አንድ ካህን ለመላ ሕይወት የሚል ኃላፊነት ያለው ለማቅረብ መልካም አመራረጥ መልካም ሕንጸትና ቅንና ተገቢ ማስተዋልና ግንዛቤ ይጠይቃል።  ይኽ ደግሞ በመጀመሪያ የጥሪው ወቅት የሚከወን ሆኖ በመቀጠልም ሕንጸቱ የተጠራው በክህነት ሕይወት መኖር ከጀመረም በኋላ መከወን ይኖርበታል፡ ሕንጸቱ ቀጣይ ነው። በዚያ Ratio fundamentalis - መሰረታውያን አመክንዮ (መመዘኛዎች) ዘንድ እንደተመለከተው ሕንጸት ቀጣይና ምሉእ መሆን አለበት። ስለዚህ ሰነዱ ያሰመረበት ሕንጸት የቀለም ትምህርትና የማሰብ ችሎታ ለማዳበር ላይ ያነጣጠረ ሳይሆን ሰብአዊና መንፈሳዊ ሕንጸት የሚል ሃሳብ ያጣመረ ነው። ደረጃ በደረጃ የመለየት ማለትን የማስተዋል ብቃት ከፍ ማድረግ ያስፈልጋል። ጥሪን የመለየት ወይንም የማስተዋል ተግባር ቅዱስ አባታችን ብዙውን ጊዜ ደጋግመው ስለ ካህናት ሕንጸት ስለ የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ሕንጸት ሲናገሩ አበክረው የሚገልጡት ሃሳብ ነው።

ብፁዕ ካርዲናል ስተላ በሳቸው የሚመራው ቅዱስ ማኅበር አባላቱን ሸኝተው ከቅዱስ አባታችን ጋር ባካሄዱት ግንኙነት፥ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የወጣት ካህንት ሰብአዊ መንፈሳዊ ትርታ የሚያዳምጡ መሆናቸው በቅርብ ለመረዳት መቻላቸውና። ስለዚህ ‘ጸልዩ ተጓዙ የፈጠራ ችሎታ ይኑራችሁ። አዲስነትን አትፍሩ’ ብሏል የጋለ ስሜት የጋለ መንፈስ የሚያዳምጥ ልብ እንዲኖር ያሳስባሉ ወጣት ካህናት የር.ሊ.ጳ. የብፁዓን አቡኖቻቸውና የእረኞቻቸው የአበይት ካህናት ድጋፍ የሚያፈልጋቸው መሆናቸውንም አበክረው ያሳሰቡት።   

ሕንጸት ሲባል አንቀጸ ትምህርት ማስረጽ ማለት ሳይሆን የኢየሱስ ሰውነት ማቅረብ ማለት ነው፡ ኢየሱስን ማቅረብ ማለት ነው። ስለዚህ ታናጪው ወጣት ክፍት ልብ ሊኖረው ያስፈጋል። አንድ ወጣት በዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት በሚቆይባቸው ስድስት ስምነት ዓመታትም ይሁን ጭምብል ያጠለቀ አለ ጠሊቅ አስመሳይ ሕይወት በመኖር ሊያሳልፈው ይችላል፡ ስለዚህ መሠረታዊው ነገር ወጣቱ ልቡን ከፍቶ ከኢየሱስ ጋር ወዳጅነት እንዲመሰርትና በዚህ ሂደትም ምሉእ ሰብአዊና መንፈሳዊ ሕንጸት እየተጎናጸፈ እንዲያድግ ማድረግ ነው፡ ሕንጸት በጥልቀት ያንን ስነ ቀለማዊ እድገቱና የማሰብ ብቃቱን ብቻ ሳይሆን ሰብአዊ ገጽታውን ከነካው፡ የልብ መለወጥን እየታደለ  ሕይወቱን ወደ ኢየሱስ ሕይወት እያቀረበ ኢየሱስን በመምሰል እያደገ ከሆን መለየትና ማስተዋል። የክህነት ሕንጸት ሊያስፈራን አይገባም።

ቅዱስ አባታችን ደጋግመው ስለ ተስፋ ይናገራሉ። ተስፋ ርእስ ያደረገ ስብከት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ቃለ ምዕዳን ለግሰዋል። ስለዚህ “ፍርሃት ጭንቀት ጨለምተኛነትን”  እንዲወገድ ነው። ወደ ጌታ እንሂድ ወደ ወንጌላዊ ትምህርት ቤት እናቅና ኢየሱስ የሚለንም ዘወትር ከእናንተ ጋራ ነኝ ነው ካሉ በኋላ በመጨረሻም ብፁዕነታቸው ፥ ከቅዱስ አባታችን ጋር በተካሄደው ግንኙነት ቅዱስነታቸው ያተኮሩበት ነገር ስለ የወጣቱ ጥሪ የሚል ሃሳብ ነው። መጽሓፍ ቅዱስ በዚህ ዓይነት የጥሪ ታሪክ የተሟላና እጅግ ሃብታም መሆኑ አብራርተዉታል። ስለዚህ ይኽ ደግሞ ጥሪ በመጽሓፍ ቅዱስ ላይ ሊማከል ይገባዋል ለማለት ነው ሲሉ ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.