2017-06-02 16:35:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ቤተሰብ ዓለም ወደ ሰብአዊነት በበለጠ እያደገ እንዲሄድ የሚያደርግ እርሾ ነው


“ኤውሮጳ ልዩ ድንቅና እጹብ ሃብቷ ቤተ ሰብ ነው” ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአገረ ቫቲካን በሚገኘው በቀለመንጦስ የጉባኤ ኣዳራሽ የኤውሮጳ የካቶሊካውያን ቤተሰቦች ፈደራላዊ ማኅበር ባሰናዳው ዓውደ ጉባኤ የሚሳተፉትን ተቀብለው በለገሱት መሪ ቃል አበክረው “ቤተ ሰብ የኅብረተሰብ ማእከል ነው” እንዳሉ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።

ቤተሰብ ለዓለም እርሾ ነው

ቅዱስነታቸው በለገሱት ምዕዳን ይኸ ከተቋቋመ ጥቂት ዓመታት እያስቆጠረ ያለው በ 14 የኤውሮጳ አገሮች የሚገኙትን ካቶሊክ አቢያተ ሰብ ማኅበራትን የሚያቅፈው የኤወሮጳ ካቶሊካውያን ቤተሰቦች ፈደራላዊ ማኅበር፥ “ቤተሰብ የኅብረተሰብ በለጠ ወንድማማችነት ወደ የሚኖርበት ማንም ተነጥሎና ለብቻው ተትዎ  ወደ ማይኖርበት ሰብአዊነት እንዲያድግ የሚያደርግ እርሾ መሆኑ ሊታመን ይገባዋል”

ቤተሰብ ጸጋ ውብነትና ኃሴት ነው

የበሮማ ውል በሚታወቀው ለኤወሮጳ ኅብረት መሠረት የሆነው ሰነድ ፍርርም ዝክረ 60ኛው ዓመት ምክንያት ቅዱስነታችው ለመንግሥት አካላት ባስደመጡት ንግግር፥ ኅብረቱ ለተሟላ የቤተሰብ እድገት አገልጋይ መሆን አለበት በማለት ያሰመሩበትን ሃሳብ አስታውሰው። በዚያ የፍቅር ሓሴት በተሰየመ ሓዋርያዊ ምዕዳን ዘንድ ቤተሰብ በተፋቅሮ መኖር በመፈቃቃር ውስጥ ያለው የግኑኝነት ውበነት ነው በማለት የገለጡ ሃሳብ አስታውሰው ይኽ የኤውሮጳ ካቶሊክ ቤተሰቦችን የሚያቅፈው ፈደራላዊ ማኅበር አበክሮ የሚያስተጋባውና የሚኖረው ምዕዳን እንዲሆን ማሳሰባቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

ቤተሰብ ለጋራ ጥቅምና ለሰላም ዓምድ ነው

ለተሟላ ማኅበራዊ እድገት መረጋገጥ በማኅበራዊ ኅብረ ኅዋስ የቤተሰብ ህልውና መደገፍ ወሳኝ ነው። የቤተሰብ አባላት አንድነትና በመላ ኅብረተሰብ ለመደጋገፍ ዓላማ ለጋራ ጥቅምና ለሰላም መረጋገጥ ቤተሰብ ዓምድ ነው።

የግኑኝነት ባህል

“ቤተሰብ የሰዎች ጥምረት ነው ይኽ ደግሞ ለሰው ዘር ቤተሰባዊ መሆን መሰረት ነው። በመሆኑም ለግኑኝነት ባህል ማእከል ነው። እናንተ የምታቀርቡትና የምታስፋፉት የቤተሰብ አርአያ በአንድ ርእዮተ ዓለም ላይ የጸና የርእዮተ ዓለም ተገዥ ሳይሆን በዚያ በማይታበለውና በማይሻረው የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ላይ የቆመ ነው። ስለዚህ ይኽ ጉዳይ ለኤውሮጳ የሕዝባዊ ቤተሰብ መሠረት ነው”።

ያሉት ቅዱስ አባታችን አያይዘው፥ ቤተሰብ በትውልድ መካከል ቃል ኪዳን ነው

“ቤተሰብ በትውልድ መካከል ላለው ትሥሥር ማእከል የተዘክሮ የወቅቱና የመጻኢ ማእከል ነው፡ የዚህ ፈደራላዊ ማኅበር አገልግሎትም ቅዱስ ለሆነው ሕይወት አገልግሎ ነው። በተለይ ደግሞ ለተናቁት ለተቸገሩት በከፋ አደጋ ውስጥ ለሚገኙት ሁሉ ወላጅ አልባ ለሆኑት ለስደተኞች በዚህ ሕይወት ለአደጋ በተጋለጠበት ሁሉ በመሰማራት የሕይወት ባህል መስካሪ፡ በሕይወት ባህል ዙሪያ የሚያንጽ ለእነዚያ ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ በመሆን ሕይወት ከመጸነስ እክሰ ባህርያዊ ሞት ሊከበርና ሊጠበቅ እንዳለበት የሚመሰክር ነው”

እንዳሉ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን፥ “አዲሱን ትውልድ ለመደገፍና በተሟላ ሂደትና ብቃት ዕለት በዕለት በሚያደርገው ጉዞ ሁሉ ለመሸኘት እንዲቻል በቤተ ክርስቲያንም ሆነ በማኅበራዊ ዘርፍ ሁሉ ብቃት ባለው በፈጠራ ችሎታ የዳበረ ስልት እንዲኖርና እንዲሁም ለዚህ ማስፈጸሚያም የሚውል በቂ ሃብት እንዲቀርብ” ጥሪ በማቅረብ የለገሱት ምዕዳን ማጠቃለላቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.