2017-05-28 16:49:00

ር. ሊ. ጳ. ፍራንቸስኮ 19/05/2009 ዓ.ም. በሴሜን ጣሊያን የሚገኘውን የጄኖቫ ከተማ ጎበኙ።


ርዕስ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በግንቦት 19/2009 ዓ.ም. በሴሜን ጣሊያን በሚገኘው የሊጉሪያ ክልል ዋና ከተማ የሆነችውን ጄኖቫ እንደ ሚጎበኙ ተገለጸ። በዚህ ለአንድ ቀን በሚቆየው ሐዋሪያዊ ጉብኝት ለቅዱስነታቸው ከተዘጋጀው የጉዞ መርሃ ግብር መረዳት እንደ ተቻለው በቀዳሚነት ከጄኖቫ የሠራተኞች መሕበራት አባላት ጋር ተገናኝተው እንደ ሚወያዩ፣ በቀጣይነትም ከሊጉሪያ ክልል ከተወጣጡ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ገዳማዊያን ገዳማዊያት እንዲሁም ከዘርዐ ክህነት ተማሪዎች ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

በተጨማሪም  በጄኖቫ የሚገኘውን ጃኒና ጋዝሊን የተባለውን የሕጻናት ኦስፒታል በመጎብኘት ከሕጻናቱ እና ከወላጆቻቸው ጋር ቆይታን ማድረጋቸው የታወቀ ሲሆን በመጨረሻም እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር 1963 ዓ.ም. በ46 አመታቸው በተገደሉት የመጀመሪያው ካቶሊክ የአሜርካን ፕሬዚዳንት በነበሩት ጆን ኤፍ ኬኔዲ ስም በተሰየው አደባብይ ላይ መስዋዕተ ቅዳሴን እንደ ሚያሳርጉም ከወጣው የጉዞ መርሃ ግብር ለመረዳት ተችልዋል።

የቅዱስነታቸውን ጉብኝት በደስታ እና በተስፋ በመጠባበቅ ላይ የነበሩ በጃኒና ጋዝሊን የሕጻናት ኦስፒታል የሚገኙ ሕጻናት ለቅዱስነታቸው ስጦታዎችን እና መልእክቶችን ማዘጋጀታቸውም ታውቁዋል።

ባለፈው ረዕቡ እለት የጄኖቫ ሬዲዮ ጣቢያ ይህንን የቅዱስነታቸውን ግብኝት አስመልክቶ ከእርሳቸው ጋር በቀጥታ መሰመር ባደረገው ቃለመጠይቅ ቅዱስነታቸው “በጃኒና ጋዝሊን የሕጻናት ኦስፒታል ውስጥ በመታከም ላይ የሚገኙ ሕሙማን ሕጻናት ባስተላለፉት መልዕክታቸው እንደ ገለጹት “ውድ ሕጻናት በታላቅ ፍቅር ሰላምታዬን አቀርብላችዋለሁ” ማለታቸውን የዘገበ ሲሆን በቃለ መጠይቁ ላይ እንደ ተገለጸው በዚህ ጃኒና ጋዝሊን በተባለውን የሕጻናት ኦስፒታል የምያደርጉት ቆይታ ለሕጻናቱ ቅርብ በመሆን እና በተለይም ሕጻናቱን በማዳመጥ ላይ ትኩረት የሚሰጥ እንደ ሆነም ተገልጹዋል። ቅዱስነታቸው ከጄኖቫ ሬዲዮ ጋር ባደርጉት ቆይታ ጨምረው እንደ ገለጹት “ጌታ ሁል ጊዜም ቢሆን በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ለሚገኙ እና እርዳትውን ለሚሹ ሰዎች ሁሉ ቅርብ ነው” ካሉ ቡኃል ቅዱስነታቸው ለሕሙማን ሕጻናት እና ለቤተሰቦቻቸው ጸሎት እንደ ሚያደርጉም መናገራቸውም ተገልጹዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.