2017-05-26 15:41:00

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው "ኢየሱስን ለዓለም ማወጅ የአንድ ክርስትያን ተቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል" ማለታቸው ተገልጸ።


ኢየሱስን ለዓለም ማወጅ የአንድ ክርስትያን ተቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል፣ አንድ ክርስትያን ይህንን ለመተግበር ሁል ጊዜም ቢሆን ፊቱን ወደ ሰማይ ቀና በማድረግ በቅድሚያ ከክርስቶስ ጋር ያለውን ሕብረት መግለጽ ይኖርበታል። ይህንን ቀደም ሲል የሰማችሁትን ሀገረግ የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ሲሆኑ በዛሬው እለት መለትም በግንቦት 18/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ካሰሙት ስብከት የተወሰደ ነው።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

በዛሬው እለት ሲነበቡ የሰማናቸው የእግዚኣብሔር ቃላት (የዩሐንስ ወንጌል 16፡20-23) የክርስትያን ጉዞ ምን መሆን እንዳለበት ይጠቁማሉ በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የመጀመሪያው ቃል ማስታወስ የሚለው እንደ ሆነ ጠቅሰው ይህም ከሙታን የተነሳው ጌታ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ገሊላ እንዲሄዱ አዙዋቸው እንደ ነበረ እና በገሊላ ደቀ መዛሙርቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሙታን ከተነሳውን ጌታ ጋር ተገናኝተው እንደ ነበረም ገልጸዋል።

እያንድ አንዳችን በሕይወታችን ዘመናችን ይህንን የገሊላ ግንኙነት የመሰሉ ገጠመኞች በሕይወታችን ውስጥ የገጥሙናል፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢየሱስ ራሱን ለእኛ ይገልጥልናል፣ እርሱን እንድናውቀው፣ ስለ አወቅነውም ደስ እንድንሰኝ ያደርገናል፣ ይህም እርሱን እንድንከተል ያበረታታናል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው አንድ መልካም ወይም ጥሩ የሚባል ክርስትያን ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ከኢየሱስ ጋር የተገናኘንበትን ቀን እና በቀጣይነትም የነበሩንን ግንኙነቶች ሁሉ ማስታወስ ያስፈልጋል፣ ይህም ተውስታ በፈትናዎች ውስጥ በምንገባባቸው ወቅቶች ሁሉ እርግጠኞች በመሆን ፈተናዎችን እንድንጋፈጥ የረዳናል ብለዋል።

“ወደ ሰማይ መመልከት በዓለም ውስጥ ጠንክረን እንድንቆም ይረዳናል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በዚህም መሰረት በዛሬ ምንባባት ወስጥ በሁለተኛነት የተጠቀሰው እና አንድ ክርስትያን ልያውቀው የሚገባው ቃል “ጸሎት” የሚለው ቃል ነው ያሉት ቅዱስነታቸው ምንም እንኳን ኢየሱስ ወደ ሰማይ በማረጉ የተነሳ ከእኛ በአካል ቢለየንም በመንፈስ ግን ከእኛ ጋር በመሆን ለእኛ ማማለዱን ይቀጥላል ብለዋል። ኢየሱስ የእኛ አማላጅ በመሆን ለእኛ ሲል ተሰቃይቶ የቆሰለውን የቁስሉን ጠባሳ፣ ለእኛ ደኅንነት ሲል የከፈለውን ዋጋ ጭምር ለአብ ያሳየዋል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ስለዚህም ሰማያዊ የሆኑ ነገሮችን ማሰላሰል እንድንችል ይረዳን ዘንድ፣ ጸሎት ማድረግ እንድንችል የሚረዳንን ጸጋ የሰጠን ዘንድ፣ ከኢየሱስ ጋር በጸሎት የምናደርገው ትስስር ይጨመር ዘንድ ጸጋውን እንዲሰጠን ልንለምነው ይገባል ብለዋል።

በዛሬው የእግዚኣብሔር ቃል ውስጥ በሶስተኛነት የቀገለጸውና አንድ ክርስትያን ሊያውቀው የሚገባው ቃል ዓለም የሚለው ቃል ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በትላንትናው እለት በተነበበልን የወንጌል ቃል ውስጥ እንደ ተጠቀሰው ኢየሱስ ወደ አባቱ ከማረጉ በፊት ደቀ መዛሙርቱን “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፣ ሁሉንም የእኔ ደቀ መዛሙርት አዱርጉዋቸው” ብሎ እንደ ነበረ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ስለዚህም የአንድ ክርስትያን ተግባር ሊሆን የሚገባው ይህንን የኢየሱስን ቃል በዓለም ውስጥ ማወጅ እና በክርስቶስ ደም መዋጀታችንን፣ እርሱ ወደ እዚህ ምድር የመጣው ጸጋውን ሊሰተን መሆኑንና በተጨማሪም ሁላችንንም ከእርሱ ጋር በአባቱ ፊት እንደ ሚያኖረን ማወጅ ይገባል ብለዋል።

እነዚህ ማለትም ማስታወስ፣ ጸሎት እና ወደ ዓለም የሚደረግ ተልእኮ የሚሉት ሦስት ቃላት በሕይወታችን ውስጥ የሚታዩትን ሦስት ቦታዎች ያመለክታሉ በማለት ስብከታችውን የቀተሉት ቅዱስነታቸው እኛም ኢየሱስን ለመገናኘት ወደ ገሊላ፣ ወደ መንግሥተ ሰማይ እና ወደ ዓለም የምናደርገውን ጉዞ ይወክላሉ ብለዋል።

“አንድ ክርስቲያን ወደ እነዚህ ሦስት አቅታጫዎች ማምራት ይኖርበታል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “መቼ እንደ ተመረጥኩኝ እና መቼ ከእርሱ ጋር እንደ ተገናኘውኛ እንዳልረሳ” የማስታወስን ጸጋ እርሱ እንዲሰጠን ይህንን ጸጋ ከእርሱ መጠየቅ ያስፈልጋል ብለዋል። በመቀጠልም አንድ ክርስትያን ወደ ሰማይ እየተመለከተ መጸለይ ይገባዋል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም ኢየሱስ አማላጃችን ይሆን ዘንድ ያግዘናል ብለዋል። በሦስተኛ ደረጃ አንድ ክርስትያን ለተልዕኮ ወደ ዓለም መሄድ ይኖርበታል ይህም እርሱ ራሱ በቀዳሚነት የሕይወት ምስክርነት በመስጠት፣ ከዚያም ለሌሎች ቅዱስ ወንጌልን መመስከር ይገባዋል ብለዋል።

የዛሬው ቅዱስ ወንጌል እንዲህ ይላል “ይህንን የመሰለ የክርስትያን ኑሮ በምትኖሩበት ወቅት ሁሉ በመጨረሻው ቀን ልባችሁ በደስታ ይሞላል፣ ደስታችሁንም የሚወስድባችሁ ማንም የለም” (ዩሐንስ 16፡23) እንደ ሚል በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ማንም ሰው ደስታችንን በፍጹም ሊነጥቀን አይችልም ምክንያቱም ከኢየሱስ ጋር አድርገነው የነበረው የመጀመሪያ ግንኙነት ትውስታ አለን፣ ኢየሱስ በመንግሥተ ሰማይ እንደ ሚኖር እና ለእኛ እንደ ሚያማልድ እርግጠኞች ስለሆን፣ በዚህም በመተማመን እና ጥንካሬን በማግኘት ከራሳችን በመውጣት እና ከራሳችን ባሻገር በመሄድ  የእኛ ሕይወት መሰረቱን ያደረገው ከሙታን በተነሳው እና ሕያው በሆነው በኢየሱ ክርስቶስ ላይ መሆኑን እንድንመሰክር ስለሚረዳን ነው ብለዋል።

ትውስታ፣ ጸሎት እና ተልዕኮ የሚሉትን ሦስት የክርስትያን ሕይወት አመላካች ቃላትን በሚገባ ማስታወስ እና መረዳት እንድንችል ጌታ ጸጋውን እንዲሰጠን እና ማንም ሰው ሊነጥቀው በማይችለው ደስታ ተሞልተን ወደ ፊት መጓዝ እንድችል ይረዳን ዘንድ ጸጋውን እንዲያበዛልን ልንለምነው ያስፈግላ ካሉ ቡኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.