2017-05-24 16:39:00

በየቀኑ የሚደረግ የመንፈሳዊ ለውጥ ጉዞ ከዓለም መንፈስ ተላቆ ኢየሱስን በደስታ ወደ ማወጅ እንድቀየር ያደርጋል ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 15/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት ሰማዕታት የሌሉባት አንድ ቤተ ክርስትያን ታማኝ ልትሆን አትችልም ማለታቸው ተገለጸ። እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ1980 ዓ.ም. በላቲን አሜሪካ በሚገኘው ሳልቫዶር በሚባል ሀገር በወቅቱ የሀገሪቷ ሊቀ ጳጳስ የነበሩ ኦስካር ሮሜሮ የድሆች መብት ይክበር ዘንድ በተደጋጋሚ ጥሪ በማድረጋቸው የተነሳ በወቅቱ በነበረው የሀገሪቷ አገዛዝ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ደርሶባቸው እንደ ነበረ የሚታውቅ ሲሆን በመጨረሻም እንደ የአሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር 1980 ዓ.ም. በጦር መሳሪያ ተመተው መገደላቸውን ይታወሳል። ልድኾች አልኝታነታቸውን በመግለጻቸው እና የድኾች መብት ይከበር ዘንድ ሰላማዊ የሆነ ተቃውሞ በማደረጋቸው የተነሳ በመገደላቸው ከቤተ ክርስትያን የብጽህና መረግ  የተሰጣቸው መሆኑም የሚታወስ ሲሆን ቅዱስነታቸው በትላንትናው እለት በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙት ስብከት ሰማዕቱን ሊቀ ጳጳስ ኦስካር ሮሜሮ ሕይወት ዙሪያ ያጠነጠነ እንደ ነበረ ተገልጹዋል።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ብጹዕ ሊቀ ጳጳስ ኦስካር ሮሜሮ የነበራቸውን መንፈሳዊ ቅንዐት እና ለፍትህ መስፈን ያደረጉትን ከፍተኛ ተጋድሎ በድጋሚ በማስታወስ  ያልሞቀች ወይም ያልቀዘቀዘች “ለብ ያለች ቤተ ክርስትያን” አባል መሆን አደገኛ ጉዳይ መሆኑን ለምዕመናን ጨምረው የገለጹት ቅዱስነታቸው ምዕመናን ምቹ የሆነ የሕይወት አካሄዳቸውን በመተው ጤናማ የሆነውን እና ኢየሱስ በደስታ የመሰከረውን የአኗኗር ዘይቤ ሊከተሉ ይገባል ብለዋል።

የቅዱስነታቸው ስብከት በቀጣይነት ትኩረቱን አድርጎ የነበረው በእለቱ በቀዳሚነት በተነበበው እና ከሐዋሪያት ሥራ 16፡16-34 ላይ በተጠቀሰው የሐዋሪያው ጳውሎስ እና ሲላስ በፊልጵስዩስ ከተማ በነበሩበት ወቅት ወደ ቤተ መቅደስ በመሄድ ላይ በነበሩበት ጊዜ ወደ ፊት የሚሆነውን ነገር በጥንቆላ የሚናገር ርኩስ መንፈስ ያደረባት አንዲት አገልጋይ ልጃገረድ ጳዎሎስ እና ሲላስ ስያልፉ ባየችበት ወቅት “እነዚህ ሰዎች የልዑል እግዚኣብሔር አገልጋዮች ናቸው! እነርሱ የደኽንነት መንገድን ያበሥሩአችኃል” ብላ በታልቅ ድምጽ በጮኸችበት ወቅት ጳውሎስ ተበሳጭቶ በእርሱ አድሮ የነበረውን እርኩስ መንፈስ “በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከእርሷ እንድትወጣ አዝዤሃለው” ብሎ ከእርኩስ መንፈስ ነጻ አድርጉዋት እንደ ነበረ የጠቀሱት ቅዱስነታቸው ይህም ተግባራቸው የከተማይቷ ነዋሪዎች መንፈሳዊ ለውጥ እንዲያደርጉ መንገድ የከፈተ እንደ ነበረም ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

በድኅንነት ታሪክ ውስጥ ተመሳሳይ የሆኑ ሁኔታዎች ተፈጥረው እንደ ሚያቁ በመጥቀስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የእግዚኣብሔር ሕዝቦች ዝም በሚሉበት ወቅቶች እና ተግዳሮቶችን ለመጋፈጥ ዝግጁ በማይሆኑባቸው ወቅቶች ሁሉ ዓለምን ወደ ማገልገል ይቀየራሉ ብለዋል።

በዚህ ዓይነት አጋጣሚዎች ውስጥ ሁሉ  እውነትን በመናገራቸው የተንሳ የአንድ አንዶቹን  ሰዎች ምቾት በመንሳታቸው የተነሳ ስደት የደረሰባቸው ልክ እንደ ጳውሎስን የመሳሰሉ  ነብያትን እግዚኣብሔር ይልክልናል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “በቤተ ክርስትያን ውስጥ የዓለማዊነት መንፈስ በሚንጸባረቁባቸው ወቅቶች ሁሉ ይህንን የሚቃወሙ ሰዎች ሁል ጊዜም ቢሆን ደም በለበሰ ዓይን እንደ ሚመለከቱዋቸው እና ከቤተ ክርስትያን እንደ ሚያገሉዋቸውም ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት “ብጹዕ ሊቀ ጳጳስ ኦስካር ሮሜሮ እውነት በመገራቸው የተነሳ ለሞት መዳረጋቸውን፣ በተመሳሳይ መልኩ በቤተ ክርስትያን ታሪክ ውስጥ እውነትን በመናገራቸው የተነሳ የሚሰደዱ ሰዎችን ሁሉ ዛሬ ማሰብ ያስፈልጋል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ምክንያቱ ክፉ መንፈስ ሁሉም ነገር ልብ የሆነ እንዲሆን ያደርጋል፣ ተግዳሮቶችን የማትጋፈጥ ቤተ ክርስቲያን እንድትሆን ያደርጋል፣ በጥቅማጥቅሞች ጀርባ የምትሽከረከረ ቤተ ክርስትያን እንድትሆን ያደርጋል፣ በምቾት ብቻ የምትኖርና ለብ እንዳለ ውሃ የሆነች ቤተ ክርስትያን እንድትሆን ያደርጋል ብለዋል።

በየቀኑ የሚደረግ የመንፈሳዊ ለውጥ ጉዞ ከዓለም መንፈስ ተላቆ ኢየሱስን በደስታ ወደ ማወጅ እንድቀየር ያደርጋል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ጥቅማጥቅሞችን ብቻ ከሚያጋብስ እምነት  ተላቀን ኢየሱስ ጌታ መሆኑን በደስታ ወደ ሚመሰክር እምነት መቀየር ይኖርብናል ብለዋል።

ጌታ ቀጣይነት ያለው መንፈሳዊ ለውጥ እንድናመጣ ጸጋውን ይሰጠን ዘንድ እርሱን መለመን ያስፈልጋል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ለብ ካለ የአኗኗር ዘይቤ ተላቀን በደስታ ኢየሱስ ጌታ መሆኑን ማወጅ እንድንችል ይረዳን ዘንድ መጸለይ ያስፈልጋል ካሉ ቡኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.