2017-05-18 10:37:00

እውነተኛ ሰላም ሰው ሠራሽ የሆነ ሰላም ሳይሆን የእግዚኣብሔር ስጦታ ነው።


“እውነተኛ ሰላም ሰው ሠራሽ የሆነ ሰላም ሳይሆን የእግዚኣብሔር ስጦታ ነው”። ይህንን የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 8/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት የተወሰደ ነው። “መስቀል ያልታከለበት ሰላም የክርስቶስ ሰላም አየደለም” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በመከራዎች ውስጥ በምንሆንባቸው ጊዜያት ሁሉ ሰላምን የሚሰጠን ጌታ ብቻ መሆኑን ጨምረው የገለጹት ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያስተሙት ስብከት በዚሁ ጭብጥ ዙሪያ ያጠነጠነ እንደ ነበረም ተገልጹዋል።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

በእለቱ በተነበበው እና ከዩሐንስ ወንጌል 14፡27-31 ላይ ከተወሰደው “ሰላሜን እተውላችኃለሁ፣ ሰላሜን እሰጣችኃለሁ” በሚለው ሀረግ ላይ ትኩረቱን ባደረገው ስብከታቸው እውነተኛ ሰላም ሰጭ እግዚኣብሔር ብቻ ነው ማለታቸውም ተገልጹዋል። በእለቱ በቀዳሚነት በተነበበው እና ከየሐዋሪያት ሥራ 14፡19-28 በተወሰደው ምንባብ ላይ የተጠቀሰውን የቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ እና የባርናባስን መከራ እና ስቃይ በሚያመለክተው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ተመርኩዘው እንደ ገለጹት ቅዱስ ወንጌልን ለማወጅ በወጡበት ወቅት ብዙ መከራ ገጥሞዋቸው ነበር “ኢየሱስም በቃሉ እኔ የምሰጣችሁ ሰላም ዓለም እንደ ሚሰጣችሁ አይነት ሰላም አይደለም” ብሎ እንደ ነበረም በድጋሚ አስታውሰዋል።

“ዓለም የሚሰጠን ሰላም፣ ያለምንም መከራ የሚገኘውን ሰላም ነው” ያሉት ቅዱስነታቸው ይህም ሰው ሰራሽ የሆነ እና የምያረጋጋ ዓይነት ሰላም ነው፣ የዚህ ዓይነቱ ሰላም ደግሞ ከሰዎች ጋር ያለንን ግንኙነት እና ደኅንነት ጤናማ በማድረግ ምንም እንዳናጣ ያደርገናል፣ ጠቅለል ባለ አገላለጽ “ድኸው አልዓዛር በደጁ ተኝቶ በነበረበት ወቅት እርሱ ግን በቤቱ በድሎት የኖረውን፣ ራሱን በራሱ ገድቦ ከዚያ ባሻገር ማየት ተስኖት የነበረውን ሐብታም ሰው የነበረውን ዓይነት ሰላም ይመስላል” ብለዋል።

ዓለማችን የምያስተምረን የደነዘዘ የሰላም መንገድ እንድንከተል ነው፣ የሕይወታችን እውነታ የሆነውን መስቀል እንዳንመለከት ያደነዝዘናል። ለዚህም ነው ሐዋርያው ጳውሎስ ‘አንድ ሰው ወደ እግዚኣሐብሄር መንግሥት ለመግባት መከራ የበዛበትን መንገድ ማለፍ ግድ ይላለዋል’ ያለው በዚሁ ምክንያት ነው።  ነገር ግን በመከራዎች ውስጥ ሰላምን ማግኘት እንችላለን?  በእኛ በኩል ግን አይቻልም፣ የምያረጋጋ ሰላም፣ የሕሊና ሰላም፣ በአጠቃላይ ሰላማችንን በራሳችን ማረጋገጥ አንችልም፣ ምክንያቱም በመከራዎች ውስጥ ሕመም፣ በሽታ ወይም ሞት አለና። ነገር ግን ኢየሱስ የሚስጠን ሰላም ነጻ ስጦታ ነው፣ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ፣ የዚህ ዓይነቱ ሰላም ደግሞ በመከራዎች ውስጥ እና ከመከራዎች ባሻገር መዝለቅ ይችላል።

ቅዱስነታቸው ስብከትቸው በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት እግዚኣብሔር የሚሰጠን ሰላም “ወደ ፊት እንድንጓዝ የሚረደን ስጦታ ነው” ካሉ ቡኃላ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ሰላሙን ከሰጣቸው ቡኃላ እርሱ ግን በተቃራኒው በጌተ ሰማኒ ይገኝ በነበረው የአተክልት ሥፍራ “ራሱን ለእግዚኣብሔር ፈቃድ መስዋዕት አድርጎ በማቅረብ የተነሳ ይሰቃይ ነበር” ካሉ ቡኃላ ነገር ግን መጽናናትን ከእግዚኣብሔር አላጣም ነበር ቅዱስ ወንጌላችን እንደ ሚያስረዳን መልአክት ከሰማይ ወርደው ያጽናኑት ነበር”  ብለዋል።

“የእግዚኣብሔር ሰላም በሕይወታችን እውነታ ውስጥ የሚገባ፣ ሕይወትን የሚሰጥ እውነተኛ ሰላም ነው። ብዙ መከራዎች አሉ፣ ብዙ የታመሙ ሰዎች አሉ፣ በጣም ብዙ መጥፎ የሚባሉ ነገሮች አሉ፣ ብዙ ጦርነቶችም አሉ. . . ወዘተርፈ. . . ነገር ግን ወደ ፊት ቀድሞን በመጓዝ በመስቀል ላይ የነበረውን ጭንቀት እና መከራ እድንቋደስ ያደርገናል እንጂ በስጦታነት የተሰጠን በውስጣችን የሚገኘው ሰላም ግን መቼም ቢሆን አይጠፋም። ያለ መስቀል የሚገኝ ሰላም የክርስቶስ ሰላም አይደለም፣ የዚህ ዓይነቱ ሰላም ሊሸመት የሚችል ነገር ግን ብዙ የማይቆይ፣ ዘላቂ ያልሆነ  ዓይነት ሰላም ነው።

በምናደድበት ወቅት “ሰላሜን አጣለሁ” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ለክርስቶስ ሰላም ራሴን ዝግ በማደርግባቸው ወቅቶች ሁሉ ልቤ ይሸበራል” ያሉት ቅዱስነታቸው ምክንያቱም ሕይወትን ከነመስቀሉ እና መሰቀሉን ተከትሎ የሚመጣውን ሐዘን መቀበል ባለመቻላችን የሚመነጭ ስሜት ነው” ካሉ ቡኃላ እግዚኣብሔር የሰላምን ፀጋ ይሰጠን ዘንድ ልንለምነው ያስፈልጋል ብለዋል።

ወደ እግዚኣብሔር መንግሥት ለመግባት ብዙ መከራዎችን ማለፍ ይጠበቅብናል።  ያንን ውስታዊ ሰላም የሚሰጠንን የሰላምን ፀጋው ማጣት የለብንም። ይህንን በተመለከተ ቅዱስ አጎስጢኖስ “የአንድ ክርስትያን ሕይወት በዓለም ውስጥ በሚገጥሙት ስደት እና ከእግዚኣብሔር በሚመጣ መጽናናት መካከል የሚደረግ ጉዞ ነው” ብሎ ነበር። የዚህ ዓይነቱ ሰላም ጌታ ከመንፈስ ቁዱስ ጋር ለእኛ የሚሰጠን ስጦታ መሆኑን እንድንረዳ ያግዘን” ካሉ ቡኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.