2017-05-05 15:26:00

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ "ቅዱስ ወንጌልን ለማብሰር መሄድ፣ ማዳመጥ እና ደስተኛ መሆን ያስፈልጋል" ማለታቸው ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በሚያዝያ 26/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት ቤተ ክርስቲያን በእግሩዋ በመቆም እና ወደ ፊት በመጓዝ በመቅበዝበዝ ላይ የሚገኙትን ሕዝቦች ሁሉ በደስታ መስማት ይኖርባታል ማለታቸው ተገለጸ።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለው ምልክት በመጫን ማደመጥ ትችላላችሁ!

 

በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ በተጠቀሰው የሐዋሪያት ሥራ መጽሐፍ በመጀመሪያዎቹ 8 ምዕራፎች ውስጥ “ጠቅለል ባለ ሁኔታ የቤተ ክርስቲያንን ታሪክ መመልከት እንችላለን” ያሉት ቅዱስነታቸው እነዚህም ስብከት፣ ጥምቀት፣ መንፈሳዊ ለውጥ፣ ተዐምራት፣ ስደት፣ ደስታ እንዲሁም “በቤተ ክርስቲያን የበጎ አድራጉት ተጋብራት የተሳተፉ ነገር ግን በስተመጨረሻ ቤተ ክርስቲያንን ያጭበረበሩዋት” ሐናንያና ሰጲራ (የሐዋሪያት ሥራ 5:1-11) የመሳሰሉ የራሳቸው ጥቅም ብቻ ለማስከበር ቤተ ክርስቲያንን የተቀላቀሏትን ክፉ የሚባሉ ኃጢያተኛ የሆኑ ሰዎችን ጨምሮ አቅፎ የያዘ ታሪክ ይገኝበታል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን የጀመሩት በዚሁ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ በመመርኮዝ እንደ ነበረ የታወቀ ሲሆን ይህንንም ምርኩዝ በማድረግ በእለቱ ወደ ተነበበው ምንባብ መሻገራቸውም ተጠቁሙዋል። ጌታ ከመጀመሪያ ጊዜ አንስቶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር አብሮ እንደ ነበረ በአጽንት በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህንንም አብሮነቱን ኢየሱስ በሚፈጽማቸው ተዐምራት ደቀ መዛሙርቱ ማረጋገጥ ችለው እንደ ነበረም ጠቅሰው  በተለይም ደግሞ ክፉ በሚባሉ ወቅቶች ሁሉ በፍጹም ብቻቸውን ጥሎዋቸው አይውቅም ነበር ብለዋል።

በመቀጠልም በእለቱ በተነበበው የመጀመሪያ ምንባብ (የሐዋሪያት ሥራ 8:26-40) ላይ በተጠቀሱት ቃላት ላይ ተመርኩዘው ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በቀዳሚነትም መንፈስ ቅዱስ ፍሊጶስን “ተነስ እና ሂድ” ብሎት እንደ ነበረ አስታውሰው ይህም አባባል “የቅዱስ ወንጌል ተልእኮ ምልክት ነው” ካሉ ቡኃላ ይህም የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ እና መጽናኛዋ ሊሆን የሚገባው ቅዱስ ወንጌልን መስበክ መሆኑን ያሳያል ብለዋል።

“ቅዱስ ወንጌልን ለመስበክ ‘ተነስ እና ሂድ ነው እንጂ የሚለው፡ በተቃራኒው ‘በቤትህ ውስጥ ሁነህ ተረጋግተህ ተቀመጥ’ በፍጹም አይለንም። ቤተ ክርስቲያን ለጌታ ታማኝ ለመሆን ከፈለገች “ተነስ እና ሂድ!” እናዳለው ሁሉ በእግሮቹዋ መቆም እና መጓዝ ይኖርባታል። በእግሮቹዋ የማትቆም እና ወደ ፊት የማትጓዝ ቤተ ክርስቲያን የታመመች ቤተ ክርስቲያን ናት”።

ይህም ተግባር ቤተ ክርስቲያን ልቦናዊ እና መንፈሳዊ ቀውስ ውስጥ እንድትገባ በማድረግ ራሷን በራሷ ክርችም አድርጋ እንድትቆልፍ ያደርጋታል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ይህም ቤተ ክርስቲያንን የሐሜት እና የቁሳቁሶች ዓለም ውስጥ በመክተት፣ ራሱዋን በራሱዋ እንድትከረችም በማድረግ በአጠቃላይም አድማስ የለሽ እንድቶን ያደርጋታል ብለዋል። ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን መነሳት እና ወደ ፊት መሄድ ይጠበቅባታል፣ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ረገድ ብቻ ነው ወንጌልን በብቃት ማብሰር የምትችለው ብለዋል።

“ተነስ እና ወደ ሰረገላው ሂድ!” በማለት መንፈስ ቅዱስ ለፍሊጶስ የተናገረው ቃል ላይ ባተኮረው ሁለተኛው አስተንትኖዋቸው ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት በሰረገላው ላይ የነበረው የአይሁድ ሐይማኖት ተከታይ የነበረ እና እግዚኣብሔርን ለማምለክ ወደ ኢየሩሳሌም የመጣ ኢትዮጲያዊ ጃንደረባ እንደ ነበረም አውስተዋል። በሰረገላው ላይ ሆኖ በሚጓዝበት ወቅት የትንቢተ ኢሳያስን መጽሐፍ እያነበበ እንደ ነበረ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው መንፈስ ቅዱስ ፍሊጶስን ወደ እዚያ ሰው እንዲሄድ አድርጎት እንደ ነበረ ጠቅሰው ቤተ ክርስቲያን ልባቸው በመቅበዝበዝ ውስጥ የሚገኙትን ያንዳንዱን ሰው ቀርባ ማዳመጥ ይኖርባታል ብለዋል።

“ሁሉም ሰዎች በመልካም ነገር ይሁን በክፉ ልባቸው በመቅበጥበት ላይ ይገኛል፣ ረፍት የለሽ ሆነዋል። ይህንን መቅበጥበጥ አዳምጡ።  ሂድና እምነቱን አስቀይረው በፍጹም አላለም። ነገር ግን “ሂድ እና አዳምጠው” ነበር ያለው። “ተነስ እና ሂድ” የሚለው የመጀመሪያው ደረጃ ሲሆን፣ “ሂድ እና አዳምጥ” የሚለው ደግሞ ሁለተኛው ደረጃ ነው። ሰዎች ምን እንደ ሚሰማቸው የማደመጥ ችሎታ? ሰዎች በልባቸው የሚሰማቸውን ስሜት? ሰዎች ምን እንደ ሚያስቡ? መቅበዝበዛቸው ከየት እንደ መነጨ ለማወቅ እነዚህን ጥያቄዎች መመለስ ይጠበቅብናል። ሁላችንም ብንሆን ይህ የመቅበዝበዝ ስሜት አለን። የቤተ ክርስቲያን ሁለተኛ ተግባሩዋ መሆን የሚገባው የሚቅበዘበዙ ሰዎችን መፈለግ ሊሆን ይገባል”።

ፍሊጶስ ወደ እርሱ እየቀረበ መምጣቱን ባዬ ጊዜ በማንበብ ላይ የነበረውን የነብዩን ቃል እንዲያስረዳው ሰረገላው ላይ እንዲወጣ የጠየቀው ይህ ኢትዮጲያዊ ጃንደረባ እንደ ነበረ በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ፍሊጶስም በታላቅ “ትህትና” መስረዳት ወይም መስበክ ጀምሮ ነበር ብለዋል። በዚህ ሰው ልብ ውስጥ የነበረው የመቅበዝበዝ ስሜት በፍሊጶስ ማብራሪያ ምላሽ በማግኘት የልቡን ተስፋ አለምልሞ ነበር ያሉት ቅዱስነታቸው ይህም ሊከሰት የቻለው በቅድሚያ “ፍሊጶስ አብሮት በመሆን በሚገባ ስላደመጠው ነው” ብለዋል።

ይህ ኢትዮጲያዊ ጃንደረባ በሚያዳምጥበት ወቅት ጌታ በእርሱ ውስጥ ተግባሩን ያከናውን ነበር በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በዚህም የተነሳ ቀደም ሲል በትንቢተ ኢሳያስ መጽሐፍ ውስጥ ስያነበው የነበረው መልእክት ኢየሱስን የሚመለከት መሆኑን ተረድቶ ነበር ብለዋል። ቀስ በቀስም በኢየሱስ ላይ ያለው እምነት እያደገ በመምጣቱ የተነሳ ወንዝ ባለበት ስፍራ በደረሱበት ወቅት መጠመቅ እንደ ሚፈልግ ገልጾ ነበር ያሉት ቅዱስነታቸው “ይህ ኢዮጲያዊ ጃንደረባ ፍሊጶስን አጥምቀኝ ብሎ የጠየቀው ጌታ በውስጡ ሆኖ ይሠራ ስለነበረ ነው” ብለዋል። ፍሊጶስ ይህንን ኢትዮጲያዊ ጃንደረባ ካጠመቀው ቡኋላ በመንፈስ ቅዱስ ተነጥቆ ተሰወረ በማለት ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ይህም ኢትዮጲያዊ ጃንደረባ ጉዞውን በደስታ ተሞልቶ እንደ ቀጠለም ገልጸዋል። “የክርስቲያን ደስታ” የሚለው ሀረግ በእለቱ በተነበበው የመጀመሪያ ምንባብ ውስጥ የሚገኝ በሦስተኛው ፍሬ ሐሳብ ነው ካሉ ቡኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.