2017-05-03 17:11:00

ጳጳሳዊ የስነ ምርምርም ተቋም ምሉእ ዓመታዊ ጉባኤ


“በመካከለኛ የኑሮ ደረጃ የሚተዳደረው የኅብረተሰብ መደብ ሲፈርስና ለከፋ ችግር ሲጋለጥ በሕዝባዊ ተሳትፎ ላይ የሚጸናው የዴሞክራሲ ስርዓት ለከፋ አደጋ ይጋለጣል” ሲል የስነ ምርምር ጳጳሳዊ ተቋም እ.ኤ.አ. ከሚያዝያ 28 ቀን እስከ ግንቦት 2 ቀን 2017 ዓ.ም. “ወደ ሕዝባዊ ተሳታፊነት ለመድረስ፡ ማሕበራዊና ባህላዊ ስብስብነት (ተወሃዶነት) እንዲኖር ወደ ሚያደርግ አዲስ መንገድ ማቅናት”  በሚል ጠቅላይ ርእስ ሥር ባካሄደው ዓውደ ጉባኤ ባወጣው የፍጻሚ ሰነድ ላይ እንዳሰመረበት የጉባኤ የፍጻሜ ሰነድ ዙሪያ በቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አስታወቁ።

የተቋሙ የበላይ ኃላፊ ብፁዕ አቡነ ማርቸሎ ሳንቸዝ ሶሮንዶ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፥

“ሕዝባዊ ተሳትፎ አንድ ጦቢያ ማለትም የማይጨበጥና የማይደረስ ምኞት አይደለም። ስለዚህ ከባህላዊና ከማኅበራዊ ተሳትፎነት ተወሃዶነት (ስብስብነት) ውጭ የሚያደርግ ሁነት መዋጋት ያስፈልጋል። የዚህ ዓላማም በኅብረተሰብ ዘንድ ሰዎችንና ማኅበረሰቦችን ማካተት ሲሆን የማካተቱ ጉዳይ በኋይል በማስገደድ ወይንም ደግሞ አንድ ዓይነት በሆነ ተጨባጭ ልዩነቶችን ግምት በማይሰጥ መሥፈርት አማካኝነት ሊከወን አይገባውም”

ይህ ቅዉም ሃሳብ የተካሄደው ዓውደ ጉባኤ ባወጣው የፍጻሜ ሰንድ ውስጥ በስፋት እንዳብራራው በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ባስደመጡት ንግግር እንዳመለከቱ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ ይጠቁማሉ።

“እርግጥ ነው እስከ አሁን ድረስ ብዙ ድሎች ተጨብጧል። ነገር ግን በሥራ ዘርፍ የእራስ ጥሪና ብቃት ተገቢ ግምት የመስጠቱ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ተቻይ ሆነዋል ለማለት አይቻልም፡ እንዲህ በመሆኑም በሰብአዊ መብትና ክብር የሁሉም እኩልነት እውቅና በመስጠት የወንድማማችነት መሠረተ ደንብ ወይንም መርህ እግብር ላይ ማዋል የእያንዳንዱ መለያና ልዩ የሚያደርገው ጥሪ ተገቢ ሥፍራ ለመስጠት ያስችላል”  ያሉት ብፁዕ አቡነ ሳንቸስ ሶሮንዶ ይኸ ሃሳብም በፍጻሜው ሰነድ በስፋት ተብራርቶ እንደሚገኝ ማስታወሳቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አያይዘው በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተገኝተው ንግግር ያሰሙት በተካሄደው ዓውደ ጉባኤ የጥናት ጽሑፍ ያቀረቡት በኢጣኢያ ቦሎኛ በሚገኘው መንበረ ጥበብ የስነ ማኅበራዊ መምህር ፒየርፓውሎ ዶናቲ፥

“በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታትና በብዙ የኤውሮጳ ክልል አገሮች ሃብት በጥቂቱ እጅ ከቀን ወደ ቀን እጅግ እየተከተረና ይህ ዓይነቱ ጥቂቱን የኅብረተሰብ ክፍል የሃብት ተጠቃሚ የሚያደርገው አካሄድ የመቀጠል ስጋቱም በመካከለኛ የኑሮ ደረጃ የሚተዳደረውን  ወደ ድኽነት እያስገባው ያለው ጉዳይም ለሕዝብነት ፖሊቲካ (populism) በር እየከፈተ ነው፡ ይኽ ደግሞ በአሁኑ ሰዓት የሚፈጠሩት የፖለቲካ ሰልፎች ወደ ሥልጣን እያመጣ ነው። ለሕዝባዊ ተሳታፊነት እንቅፋት የሚሆነው የእኵልነት መጓደል ሳይሆን ያለው ድኽነት ለመቅረፍ ሰዎችን ከተፈጥሮ ሃብት ተጠቃሚነት መብት የሚያገልና ሃብት ትምህርት ባህል ሕንጸ በጥቂቱ እጅ ቁጥጥርና ለጥቂቱ የኅብረተሰብ ክፍል ብቻ የማድረጉ ሂደት ነው”

ካሉ በኋላ በመቀጠል ንግግር ያስደመጡት በደቡብ አፍሪቃ የናዛልም መንበረ ጥበብ መምህር ፓውሉስ ዙሉ ይላሉ፥

“ሕዝብ የሃብት ተጠቃሚ ከሚደረገው ጥረት ጋር አብሮ የሃይማኖት ነጻነት ጥበቃ መካተት ይኖርበታል። የሃይማኖት ነጻነት በሌለበት  አገር የሕዝቦችና የዜጎች ተሳትፎ እጥያቄ ውስጥ ይገባል። እንደ አብነትም በዓለም ካሉት አሸባሪያን ውስጥ 88 መቶኛው የሚሸፍነው ከዚያ የሃይማኖት ነጻነት ከሚጣስበትና አንድ ሃይማኖት አምባ ገነናዊ ከሆነበት ክልል ነው የመጣው፡ ስለዚህ ሃይማኖት ሌላውን ለመነጠል ከተጠቃሚነት መብት ሊያገል ይችላል በሌላው ረገድም፡ የሃይማኖት ልዩነት ኅብረ ሃይማኖት ባለበት ክልል ደግሞ ሃይማኖት ሳይሆን የፖለቲካ ሥርዓቶች ሌላውን ከተሳፊነት መብት የሚያገሉ ሆነዋል። ይኽ ደግሞ የአገር ሃብት ለሁሉም የማዳረሱን ሂደት ያሰናክላል። ስለዚህ ሌላው በመነጠሉ ድርጊት ሃይማኖትና እንዲሁም የፖለቲካ ስልቶች ተጠያቂ የሚያደርጋቸው ኃላፊነት አላቸው” እንዳሉ ጂሶቲ ገልጠዋል።

የዚህ ጳጳሳዊ የስነ ምርምር ተቋም ሊቀ መንበር ፕሮፈሰር ማርጋረት አርከር በተሰጠው ጋዜጣዊ መለጫ በመሳተፍ “ድኻው የኅብረተሰብ ክፍል እራሱን ነጻ ለማወጣት የሚያግዙት ሁኔታዎች ሊፈጠርለትና መሣሪያዎች ሊቀርቡለት ይገባል” የሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ ተንተርሰው ባስደመጡት ንግግር፥

“በዚህ በ20ኛው ክፍለ ዘመን በ19ኛው ክፍለ ዘመን ማብቅያም ባለፉት ዘመናትም ጭምር ድኽነት ለመቅረፍና በድኽነት የሚሰቃዩትን ከድኽነት ለማላቀቅ እንደ መፍትሔ ሆኖ የቀረበው መሠረታውያን ነገሮች ማቅረብ ከሚለው ጋር የተጣመረ ነው። ምግብ ልብስ መጠለያ፡ በተለያዩ ቁምስናዎችም አልባሳትንና ምግብ ለድኾች እየተባለም ይስበሰባል የተለያዩ የተራድኦ ማኅበራትም መሠረታዊ አስፈላጊ ነገሮችን በማቅረብ መርሐ ግብር ሲጠመዱ ያታያል ሆኖም ለሰው ልጅ መሠረታዊ አስፈላጊ ነገሮች ብቻ ማቅረብ ድኻው የኅብረተሰብ ክፍል ሰብአዊ ጥያቄው ሁሉ ምላሽ አግኝቷል ለማለት አይቻልም። ማኅበራዊ ተሳታፊነቱን ማረጋግጥም አይቻልም። ምክንያቱም የድኻው ዕለታዊ ትግሉ የቀን ኑሮን ማቸነፍ ላይ ታጥሮ ስለ ሚቀር ነው”

የሚል ህሳብ ላይ በማነጣጠር በዚያ የፍጻሜው ሰነድ ተጠቃሎ የሚገኘው ሰዎችን ከማኅበራዊ ተሳትፎ ውጭ የሚያደርጋቸው ጉዳይ በስፋት ማብራራታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.