2017-05-01 16:52:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፥ ለገዳማውያን፡ ተስፋን የሚዘሩና የአገናኝ ድልድይ ገንቢዎች እንዲሆኑ ተማጸኑ


እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 29 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ካይሮ በሚገኘው የእግር ኳስ ሜዳ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው እንዳበቁም በከተማይቱ ወደ ሚገኘው የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ሕንፃ ተመልሰው በመሄድ በግብጽ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳትና የቅዱስነታቸው የቅድስት መንበር ሸኚዎቻቸውንም ጭምር ባሳተፈ የምሳ መዓድ ተቋድሰው እንዳበቁ፡ በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠ ልክ ሁለት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ በክፍለ ከተማይቱ ማአዲ ተብሎ በሚጠራው ክልል ወደ ሚገኘው የግብጽ የእስክንድሪያ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሊዮነ አቢይ ወደ ተሰየመው የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት በመሄድ ከግብጽ የሚገኙት ልኡካነ ወንጌል የውሉደ ክህነት አባላት ገዳማውያንና የዘርአ ክህነት ተማሪዎችና ደናግል ያሳተፈ የጸሎት ሥነ ስርዓት መርተው ምዕዳን መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጃንካርሎ ላ ቨላ አስታወቁ።

ቅዱስ አባታችን እዛው የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት እንደረሱ እንደ ሺሕ አምስት መቶ ካህናት ገዳማውያን ደናግል የዘርአ ክህነት ተማሪዎች በተገኙበት ፊት የቃለ እግዚአብሔር ሊጡርጊያ ከመምራታቸው በፊት የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት ዋና አለቃ አባ ቶማ አድልይ ለቅዱስነታቸው የእንኳን ደህና መጡ መልእክት አስደምጠው ኣንዳአበቁም መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 120 (121)፥

            “ዓይኖቼን ወደ ተራሮች አነሣሁ፡ ረዳቴ ከወዴት ይምጣ? ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው …”

ወንጌል ማቴዎች ምዕ. 5, 13-16

            “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ…”

ተነቦ እንዳበቃም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍርንቸስኮ በለገሱት ቃለ አስተንትኖ፥

“እኛ ያ የድህነታችን ትእምርት ለሆነው ቅዱስ መስቀል እንሰግዳለን፡ ከመስቀል የሸሸ ከትንሣኤ ይሸሻል”

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዚያች ዛሬ ለስብከተ ወንጌል እጅግ አስቸጋሪ ሆና ባለቸው አገረ ግብጽ የጋራ ውይይት እግጅ የተወሳሰበባት ያሸባሪያን ዛቻ እጅግ ያየለባት ኅልው የሆነባት አገር ፊት ሆነው ሁሉም ገዳማውያን የዘርአ ክህነት ተማሪዎችና ደናግል እነዚያን አሉታዊ ሁኔታዎችን በጽናት እንዲያሸንፉ አደራ ብለው፥

“እናተ አወንታዊ  ኃይለ ግፊት ናሁችሁ ለምትኖሩበት ኅብረተሰብ ብርሃና ጨው ሁኑ፡ የምድር ባቡሩን ወደ ፊት እንዲል የሚያደግ አወንታዊ ግፊት ሁኑ። ቀጥ ብሎ ወደ ፍጻሜውና ወደ ግቡ ማቅናት ነው። ተስፋን የሚዘሩና አገናኝ ድልድይ የሚገነቡ የውይይትና የስምምነት መሣሪያ ሁኑ”  ብለው በማስከተልም ውፉያን ካህናትና ደናግል ሁሉ መቋቋም ያለባቸውን የተለያዩ ፈተናዎችን ሲዘረዝሩ፡ በቅድሚያ በሚነፍሰው ነፋስ መዋዠቅና መገፋት ሳይሆን መመራት ማለትም፥ “መልካም እረኛ በጎችን የመምራት ሃላፊነት አለበት። ወደ ለመለመ መስክና ወደ ውሃ ምንጭ የሚመራ እንጂ በሚታየው በሚከሰተው መዋዥቅ መደናግሮችና ጨለምተኝነት የሚገፋ መሆን የለበትም”  እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ላቨላ አስታወቁ።

ያልተስተካከለ ብዙ ችግር ያለበትን ሁሉ በመመልከት ያነሰውንና የጎደለውን ሁሉ በማሰብ የሚያግረመሩሙ እንዳሆኑ ውፉያንን ሲመክሩ፥

“ውፉይ በመንፈስ ቅዱስ የተቀባ እንቅፋትና ችግርን ሁሉ ወደ መልካም አጋጣሚ የሚቀይር እንጂ የሚያጋጥሙ ችግሮችና መሰናክሎች ሁሉ ሰበብ ወይን ማመኻኛ የሚያደግ አይደለም። የሚያጉረመርም ለገምተኛ ሥራ የማይወድ ነው፡”

የሐሜት የምቀኝነት እራስን ሁለመናህን ከሌሎች ጋር ለመልካምነት ሳይሆን የበላይነትን ለማሳየት ለመመጠን የማነጻጸሩ ተግባር ሁሉ ማግለል እንደሚያስፈልግ ያሳሰቡት ቅዱስ አባታችን ያንን እጅግ አደገኛ የሆነውን፥

“ፈረዖናዊንት የተሰየመው ፍተና እርሱም፤፡ ይኽ ልብን ለጌታና ለወንድሞች የማደንደንና የመቆለፍ ፈተና፡ በሌሎች ላይ የበላይ  ሌሎችን ለራስ ክብርና ልእልና ረግጦ መግዛትና ከማገልገል ይልቅ መገልገል ይገባኛል ከሚለው ፈተና አደራ እራስችሁ ጠብቁ”  ካሉ በኋላ የለገሱት ቃለ ምዕዳን ሲያጠቃልሉ፥ ውፉያን ሁሉ አለ ብሶል ግብ አልባ ሆነው እንዳይጓዙ ሲመክሩም፥

“አንድ ውፉይ ሞቃታማ ወይንም በራዳማ ሳይሆን በእግዚአብሔርና በዓለምተኛው ሕይወት ተከፋፍሎ ያንን የመጀመሪያውን ፍቅር ዘንግቶ ሲኖር እውነተኛ መለያውን ያጣል። በበለጠ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ስንጸና እጅግ ሃብታሞችና ፍሪያማዎች እንሆናለን። የኢየሱስ ክርስቶስን እንድንሆን እነዚያ ግብጽ ያደለችንን ቅዱሳኖች ሁሉ ስንመለከት ቅኑ ትክክለኛውን እውነተኛው እርሱም እግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያንን እንዲሁም ወንድሞችን ለማገልገል የሚመራውን መንገድ ጋር እንገናኛለን፡ በዚህ መንገድም የዓለም ብርሃንና የምድር ጨው ለመሆን ትበቃላችሁ። ማለትም ለገዛ እራሳችሁ ለሌሎች ለአማኞችና ለኢአማንያንን በተለይ ደግሞ ለአንዚያ ለተናቁት በጠና ድኽነት ለተጠቁት ለተረሱት እንደ ጥራጊ ለሚታዩት በከተሞችና ከኅልውና ውጭ ተደርገው ለሚታዩት የድኅነት መሣሪያ ትሆናላችሁ”

በማለት የለገሱት ቃለ ምእዳን ማጠቃለላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ላ ቨላ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.