2017-04-18 08:10:00

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳስት ፍራንቸስኮ በፋሲካ እለት ለሮም እና ለመላው ዓለም ያስተላለፉት መልእክት።


በትላንትናው እለት ማለትም በሚያዝያ 8/2009 ዓ.ም. የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሤ በዓል በደመቀ መልኩ መከበሩ ያታወቃል። ይህንንም በዓል ለመታደም በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ተገኝተው በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የተመራውን መስዋዕተ ቅዳሴ መታደማቸውም ይታወቃል። ቅዱስነታቸው ካሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ በመቀጠል ልማዳዊ በሆነ መልኩ በታላላቅ በዓላት ወቅት የሚያቀርቡት በላቲን ቋንቋ “Urbi et Orbi” በአማሪኛው ለከተማው (ማለትም ለሮም) እና ለዓለም በተሰኘው ልማዳዊ የሆነ መልእክታቸውን ማስተላለፋቸውም ተገልጹዋል።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባስተላለፉት መልእክታቸው እንደ ገለጹት “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሣኤው ከኃጢያት ባርነት እና ከሞት ነፃ አውጥቶን የዘልዓለም ሕይወት በርን ከፍቶልናል” ብለዋል። በሁሉም ዘመናት አሉ ቅዱስነታቸው በሁሉም ዘመናት “ከሞት የተነሳው እረኛችን በዓለም በረሃማ ስፍራዎች በመቅበዝበዝ ወንድም እና እህቶቹን ያለምንም መታከት ይፈልጋቸዋል” ያሉት ቅዱስነታቸው “የጠፉትን፣ የተሰደዱትን የመውጫ በር አጥተው የሚኳትኑትን ሰዎች ሁሉ ለመፈለግ የወጣል፣ በተለመደው ወይም አዲስ የባርነት ቀንበር ሰላባ የሆኑትን ሁሉ ወደ እርሱ ያመጣቸዋል፣ ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ሕፃናትን እና ታዳጊዎችንም ይንከባከባል” ብለዋል።

“ከሞት የተነሣው እረኛችን እናት ሀገራቸውን አስገዳጅ በሆነ መነ መልኩ፣ በጦርነት በሽብር ጥቃት፣ በርሃብ እና ጨቋኝ የሆነ አገዛዝ ምክንያት ጥለው ከሚሰደዱ ሰዎች ጋር አብሮ ይራመዳል” ያሉት ቅዱስነታቸው በዓለም ዙሪያ የሚገኙ መሪዎች ግጭቶችን እና የሕገወጥ የመሣሪያ ዝውውር ይገታ ዘንድ እንዲሰሩ አጋጣሚውን ተጠቅመው ከሙታን በተነሣው ጌታ ስም የተማጽኖ ጥሪአቸው አቅርበዋል።

ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባስተላለፉት መልክታቸው በመካከለኛው ምስራቅ በተለይም በሶሪያ እየተካሄደ የሚገኘውን አውዳሚ የሆነ ጦርነት እንዲያበቃ ጥሪ ማድረጋቸው የታወቀ ሲሆን በቅርቡ በአሌፖ ክልል በደረሰው የቦንብ ጣቃት የበርካታ ሰዎችን ነብስ ማጥፋቱን አስታውሰው “በስደተኞች ላይ የተፈጸመ በጣም አስከፊ የሆነ ጥቃት” መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው በአፍሪካን አህጉር ውስጥ በሚገኙ በደቡብ ሱዳን፣ በሱዳን፣ በሶማሊያ እና በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፖብሊክ “በቀጣይነት የሚደረጉ ግጭቶችን ሕዝቡ በጽናት እንዲቃወም እንዲሁም በተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች የሚታይ የምግብ እጥረት እንዳለ አውስተው” ከሞት የተነሳው ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር ይሆን ዘንድ ጸሎታቸው መሆኑንም ገልጸዋል።

የላቲን አሜርካ ሀገሮችን በተመለከተ የተናገሩ ቅዱስነታቸው ማንኛውንም ግጭቶች እና አለመግባባቶችን በድርድር ይፈቱ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።

ቅዱስነታቸው የአውሮፓን ሀገራትን በተመለከተ ትኩረት ሰጥተው እንደ ተናገሩት በኢኮኖሚ አለመረጋጋት ምክንያት አንድ አንድ የአሮፓ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ አስጥ እንደ ሚገኙ ጠቁመው ይህም በወጣቶች ዘንድ ከፍተኛ የሆነ የሥራ አጥነት አደጋ እየደቀነ መምጣቱን ጠቁመው ከሙታን የተነሳው ጌታ ተስፋ ይሆናቸው ዘንድ ተማጽነዋል።

ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው ማጠናቀቂያ ላይ እንደ ገለጹት “ጨላማችንን ያስወገደው፣ ከሞት የሰወረን ከሙታን የተነሣው ጌታ ለዓለማችን እና ለዘመናችን ሰላምን ይስጥልን” ካሉ ብለው ቡራኬን ስጥተው ተሰናብተዋል።  

 








All the contents on this site are copyrighted ©.