2017-04-12 16:54:00

የክርስቲያን ተስፋ የሚመነጨው ከክርስቶስ መስቀል ነው


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች የጠቅላላ አስተምህሮ  እንደ ሚያደርጉ ያታወቃል። የዚህ ጠቅላላ አስተምህሮ አካል በሆነው በዛሬው በሚያዚያ 4/2009 ዓ.ም. ያስተላአፉት አስተምህሮ ከዚህ ቀደም “የክርስቲያን ተስፋ” በሚል አርእስት ስያስተላለፉት ከነበረው አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ነበረም ጨምሮ ተገልጹዋል።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ቅዱስነታቸው በዛሬው እለት ያስተላለፉትን የጠቅላላ አስተምህሮ ጠቅላላ ይዛት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ።

 

በአለፈው እሁድ እለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በታላቅ ክብር በሐዋሪያቱ እና በሕዝቡ ታጅቦ ወደ ኢየሩሳሌም መግባቱን ተመልክተናል። እነዚህ ሕዝቦች በኢየሱስ ላይ ተስፋቸውን ጥለው ነበር። በዙዎቹ እርሱ የፈጸመውን ተአምራት እና ታላላቅ ምልክቶችን በማየታቸው የተነሳ ታላቅ ኃይል እንዳለው በማመን በመጨረሻም ከጠላቶቻቸው ነጻ እንደ ሚያወጣቸው አስበው ነበር።

በተቃራኒው ከነዚህ ሰዎች መኃል፣ ከጥቂት ቀናት ቡኃላ ኢየሱስ  ተዋርዶ፣ ሞት ተፈርዶበት እና በመስቀል ላይ ይሰቀላል ብሎ ያሰበ ሰው ነበር ወይ? ምድራዊ የሆነ የእነዚ ሰዎች ተስፋ በመስቀል ሥር ዋጋ ቢስ ሲሆን እናያለን። እኛ ግን ተስፋችን በድጋሚ የተወለደው በመስቀሉ አማካይነት እንደ ሆነ በእርግጠኛነት እናምናለን። ይህም ከዓለም ተስፋ የተለየ አዲስ እና ልዩ የሆነ ተስፋ ነው። ታዲያ ይህ ምን ዓይነት ተስፋን ነው የሚገልጸው?

እውነት እውነት እላችኃለሁ የስንዴ እንክርዳድ በመሬት ላይ ወድቃ ካልሞተች በስተቀር ብቻዋን ትቀራለች ከሞተች ግን ብዙ ታፈራለች” (ዩሐንስ 1224) ብሎ ኢየሱስ ኢየሩሳሌም ከገባ ቡኃላ የተናገረው ቃል ይህንን ሁኔታ በይበልጥ ለመረዳት ያግዘናል።

እስቲ በመሬት ላይ የወደቀች አንድት ትንሽዬ ዘርን ወይም የስንዴ ፍሬን እንመልከት፡ ራሱን በራሱ ዝግቶ ከቆዬ ምንም ነገር ሊከሰት አይችልም፣ ነገር ግን ሲበተን ወይም ሲከፈት ግን ለአንድ ችግኝ ሕይወት ይዘራል፣ ያብባል ከዚያም ቡኃላ ፍሬ የሚያፈራ ሰብል ይሆናል።

ኢየሱስ ለዓለም አዲስ ተስፋን አምጥቱዋል፣ ይህንንም ያመጣው ልክ ቀደም ሲል እንዳየነው እንደ አንድ ትንሽዬ ዘር፣ በመካከላችን በመገኘት ራሱን ዝቅ አድርጎ ሰማያዊ ክብሩን በመተው በመካከላች ተገኘ፡ወደ ምድርም ወረደ ይህም በቂ አይደለም።  ፍሬ ለማፍራት ስለፈለገ ኢየሱስ ጥልቅ የሆነውን ፍቅር በመግለጽ በመሬት ውስጥ ተቀብሮ ፍሬ እንደ ሚያፈራ ዘር እርሱም ራሱን ለሞት አዘጋጀ። በዚህ ራሱን በከፍተኛ ሁኔት ዝቅ ባደረገበት እና ታላቅ የሆነውን ፍቅሩን በገለጸበት ሁኔታ ነውተስፋችን ማበብ የጀመረው።ይህም ልያብብ የቻለው በፍቅር ኃይል ነው።  ምክንያቱም ፍቅርሁሉን ችሎ ይታገሳል፣ ፍቅር በሁሉም ላይ ተስፋ ያደርጋል” (1 ቆሮንጦስ 137) ተብሎ እንደ ተገለጸው የሕግዚኣብሔር ሕይወት የሆነው ፍቅርን ማስካት ችሉዋል። የፋሲካ በዓልም እንዲሁ ነው። ኢየሱስ ሁሉምን ነገር ራሱ በመቀበል ለኃጢያታችን ስርዬትን ለሞታችን ትንሣኤን፣ ለፍርሃታችን ደግሞ በእመነት ቀይሮታል።

አዎን! ተስፋችን ሁልጊዜም በመስቀል ላይ ነው የሚወለደው ያልኩዋችሁም በዚሁ ምክንያት ነው   አዎን! በኢየሱስ አማካይነት ጨለማችን ሁሉ ወደ ብርሃን፣ ሽንፈታችን ሁሉ ወደ ድል፣ ሐዘናችንን ደግሞ ወደ ተስፋ ይቀየራል። ቀስ በቀስ በኢየሱስ ተስፋ ምድረግ ስንጀምር ዓለምን ማሸንፍ የምንችለው እንደ ዘር ስንሞት እና ራሳችንን ዝቅ ስናደርግ ነው። ከዚህ የተሻለ ክፉን ነገር የማሸነፊያ እና ለዓለም ተስፋ የመስጫ መንገድ የለም።  እስቲ ንገሩኝ ይህ ጉዳይሁሉንም ነገር የማጣት አመክኒዮ መስሎ አይታያችሁም?” እንዲሁ ነው የሚመስለው፣ ምክንያቱም የሚወድ ሰው ስልጣኑን ያጣል፣ የሚለግስ ሰው አንድ ነገር ይጎለዋል ወይም ያጣል። በተጨባጭም የአንድ የሞተች ዘር ወይም ትሁት የሆነ ፍቅር አመክኒዮ የእግዚኣብሔር ሕይወትን ይመስላል፣ በዚህም መንገድ ብቻ ነው ፍሬ ማፍራት የሚቻለው።

ይህንንም ተጨባጭ ሁኔታ በራሳችን ውስጥም የምናየው ሀቅ ነው። በዙ በምንሰበስብበት ወቅት ሁል ጊዜም ተጨማሪ ነገሮችን እንመኛለን፣ ከዚያም የተሻሉ በዛ ያሉን ነገሮችንም እንፈልጋለን በዚህም መንገድ እንቀጥላለን መቼም ቢሆን የእርካታ ስሜትን አናገኝም። ይህንንም ጉዳይ ኢየሱስየራሱን ሕይወት የሚወዳት ሁሉ ያጣታል” (ዩሐንስ 1225) በማለት ግልጽ በሆነ መሆነ መንገድ ነግሮናል። ስለዚህም ራሱን የሚወድ እና ለራሱ ፍላጎቶች ብቻ የሚኖር ሰው ራሱን ብቻ ያበለጽጋል ስለዚህም ሁሉምን ነገር ያጣል። ነገር ግን እውነታን የሚቀበል፣ ለማገልገል ዝግጁ የሆነ እግዚኣብሔር በሚወደው መልኩ የሚኖር ሰው፣ አዎን እርሱ አሸናፊ ነው፣ ራሱን እና ሌሎችንም ያድናል፣ ለዓለምም የተስፋ ዘር ይሆናል።

በእርግጥም ይህ እውነኛ ፍቅር በመስቀሉ ውስጥ የሚያልፍ ፍቅር ነው፣ እንደ ኢየሱስም መስዋዕት መሆንንም ይጠይቃል። የመስቀልንም መንገድ ልንጓዝበት ግድ የሚለን መንገድ ነው፣ ነገር ግን ግማሹን ሳይሆን ሙሉውን መንገድ፣ ገሚሱ ደግሞ በፋሲካ የሚገኝ ክብር ነው።ሴት ልጅ በምትወልድበት ጊዜ የምጥ ቀኑዋ ስለደረሰ ታዝናለች፣ ከወለደች ቡኃላ ግን በዓለም ላይ ሕጻን ስለተወለደ ከመደሰቷ የተነሣ ጭንቀቷን አታስታውሰውም” (ዩሐንስ 1621) በማለት በዚህም መልኩ ኢየሱስ የመጨረሻውን ራት ከሐዋሪያት ጋር በተቋደሰበት ወቅት የተወልንና ሊረዳን የሚችል አንድ ትልቅ ገጽታ ትቶልን አልፏል። አዎን ሕይወትን መስጠት እንጂ ሕይወትን ለራሳችን ማቆየት ደስታን አይሰጠንም። ፍቅር ተስፋችን ወደ ፊት እንዲቀጥል የሚረዳን ሞተር ነው።

ወድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ

በዚህ ወቅት አስተማሪያችን የሆነው እና ራሱን እንደ ስንዴ ዘር አድርጎ በማቅረብ ሞቶ ሕይወት የሰጠንን ኢየሱስን ማሰብ ይገባናል። እርሱ ነው የተፋችን ዘር። የተስፋችን ምንጭ የሆነውን የመስቀሉን ሚስጢር እናሰላስል። ቀስ በቀስም በኢየሱስ ተስፋ ማድረግ ማለት አሁንም ቢሆን ከኢየሱስ የፋሲካ ሚስጢር በመማር በሞት ሕይወት እንደ ሚገኝ መገንዘብ እንችላለን።  በኢየሱስ መስቀል ፊት በመቆም መስቀሉን በመመልከትበአንተ ሁሉንም እናገኛለን፣ በአንተ ሁሌም ተስፋ ማድረግ እችላለሁ፣ አንተ የእኔ ተስፋ ነህ!” እንበለው።

 

የተወደዳችሁ ታዳሚዎቻችን ቀደ ሲል ስትከታተሉት የቆያችሁት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በሚያዝያ 4/2009 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ካስተላለፉት የጠቅላላ አስተምህሮ የተወሰደ ነው።

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.