2017-04-12 15:57:00

ቅዱስ አባታችን በካይሮ የሚያካሂዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት ለተለያዩ ሃይማኖቶች ውስጠ ግኑኝነት አወንታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ይነገራል


እ.ኤ.አ. ግንቦት ወር 2016 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአገረ ቫቲካን ከግብጹ የአል አዝሃር መንበረ ጥበብ አቢይ መምህር ሼክ አሕማድ ሙሓማድ አል ጣየብ ጋር ተገናኝተው እንደነበር የሚዘከር ሲሆን፡ በዚህ በያዝነው ወር እ.ኤ.አ. ከሚያዝያ 28 ቀን ስከ ሚያዚያ 29 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱነታቸው በካይሮ ሊያካሂድት ታቅዶ ባለው ሐዋርያዊ ጉብኝት አማካኝነት በተለያዩ የዓለማችን ክልል ለሚገኙት ለምስልምና ሃይማኖት መንፈሳዊ መሪዎች ተደራሽ እንደሚሆኑና ጉብኝቱም ለሃማኖትም ሆነ ለፖለቲካው ዓለም ኃይለኛና አወንታዊ ተጽእኖ ሊኖረው እንደሚችል ከተለያዩ አካላት ከወዲሁ አስተያየት እየተሰጠበት ሲሆን፡ ይኸንን ሁሉ በማጣመር ነዋሪነታቸው በታላቅዋ ብሪጣንያ የሆነው በአገሪቱ ለሚገኘው የምስልምናና የክርስትና እምነት የጋራው ጉባኤ በሁለተኛ የሊቀ መንበርንት ኃላፊነት በማገልገል ላይ የሚገኙት የህንድ ዜጋ ከሆኑት ቤተ ሰብ በአፍሪቃ አገረ ማሊ የተወለዱ በአሁኑ ሰዓት በእንግልጣር በምትገኘው በለይሰስተር ከተማ የሚኖሩና የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ የግኑንኝነት ባህል ጉዳይ በተመለከተ ጥልቅ ተመክሮ ያላቸው የቀድሞ የአል አዝሓር መንበረ ጥበብ ተማሪ የነበሩት ሼኽ ኢብራሂም ሞግራ፥ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ከሚያዝያ 28 ቀን እስከ ሚያዝያ 29 ቀን 2017 ዓ.ም. በግብጽ ያካሂዱታል ስለ ተባለው ከዓል አዝሓር መንበረ ጥበብ አቢይ መምህር ሼክ አሕማድ ሙሓማድ አል ጣየብና በግብጽ ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ታዋድሮስ ዳግማዊ የጋራ ግኑኝነት በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር በስልክ ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥

በቅድሚያ ዓል አዝሓር መንበረ ጥበብ በዓለም ጥንታዊ የምስልምና ሃማኖት መንበረ ጥበብ ከሆኑት ውስጥ ባልሳሳት ይላሉ አንደኛ ወይንም ደግሞ ሁለተኛ ተብሎ የሚነገርለት መሆኑ አስታውሰው፡ መንበረ ጥበቡ በግብጽ ብቻ የታጠረ ሳይሆን ዓረብና ዓረብ ባልሆኑ አገሮች በጠቅላላ በምስልምናው ዓለም አቢይ ተጽእኖ ያለው ተቋም ነው፡ ስለዚህ የምስልምናው ዓለም ለሚከተለው እምነት የሚመሰረቅበት በሃይማኖቱ ዙሪያ ለሚሰጥበት ውሳኔ (orientation and judgments) መሠረት ነው ብለዋል።

ሃማኖትን ተገን በማድረግ በተለያየ መልኩ የሚታየው ፖለቲካዊ ግጭት ርእስ ዙሪያ ለቀረበላቸው መጠይቅ ሲመልሱ፡ በግብጽ ይላሉ በሙስሊሙና በክርስቲያኑ ማኅበረሰብ መካከል ያለው የጋራው ግንኙነትና ኑሮ ጥንታዊና ሰላማዊም ነው። ይኽ ደግሞ እውነት መሆኑ በአል አዝሓር መንበረ ጥበብ ተማሪ እያሉ በግብጽ ባሳለፉት ዓመታት ያረጋገጡት ገጠመኝ መሆኑ ገልጠዋል።

በአሁኑ ሰዓት እየታየ ያለው ዓመጽ በእውነቱ እጅግ አስጊና ዘግናኝ ነው። ግጭቱ ፖለቲካዊ እንጂ ከሃማኖት ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም። ስለዚህ ሃማኖት የተካባ ወይንም ሃይማኖትን ሽፋን ያደረገ ፖለቲካዊ እቅድ ነው ካሉ በኋላ፥ በዚህ በያዝነው ወር ቅዱስ አባታችን በግብጽ የሚያካሂዱት ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት በዚያ በምስልምና ሃይማኖት ማእከል ተብሎ በሚነገለት ክልል የሚያካሂዱት ጉብኝት በተለያዩ የዓለማችን ክልል ለሚገኙት ለምስልምና ሃይማኖት መንፈሳዊ መሪዎች ተደራሽ የሚያደርጋቸው ኃይለኛ መርሃ ግብር ነው። ይኽ ደግሞ ግብጽ ከምዕራቡ ዓለም ጋር መልካም ግኑኝነት ያላት በሌላው አነጋገር ደግሞ እስራኤልና አረቡን ዓለም የምታገናኝ ድልድይ በመሆንዋ በዚህ በካይሮ በዓበይት የሃይማኖት መሪዎች መካከል የሚካሄደው ግኑኝነት ለፖለቲካ አካላት በተለያየ ዘርፉ አቢይ ተጽዕኖ እንደሚኖረው አያጠራጥርም ካልይ በኋላ የሰጡት ቃለ መጠይቅ ሲያጠቃልሉ፥ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያላቸው አክብሮትና ወዳጅነት ገልጠው ለቅዱስነታቸው መልካሙን ሁሉ እመኛለሁ፥ “የዓል አዝሃር የበላይ የሃይማኖት መሪ እንዲሁም የግብጽ የፖለቲካ አካላት ቅዱስነታቸው ለሚያሰሙት ቃል፡ ለሚለግሱት ምክር  ጀሮንና ልብን ሰጥተው በጽሞና በማዳመጥ እግብር ላይ የሚያውሉት እንዲሆኑም ከወዲሁ እመኛለሁ” ብለዋል።   








All the contents on this site are copyrighted ©.