2017-03-24 17:01:00

ብፁዕ ካርዲናል ሳንድሪ፥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለክርስቲያን ብርታት ነው


በኢየሩሳሌም የሚገኘው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ዙሪያ የተገነባው የቅዱስ መቃብር ሥፍራ ቤተ መቅደስ ህዳሴ ለሁሉም ማኅበረ ክርስቲያን በተለይ ደግሞ ለመካከለኛው ምሥራቅ ማኅበረ ክርስቲያን ብርታት መሆኑ የምስራቅ ስርዓት ተከታይ አቢያተ ክርስቲያን ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ሊዮናርዶ ሳንድሪ ለአንድ ዓመት የተካሄደው የቅዱስ መቃብር ቅዱስ ሥፍራ ኅዳሴ መጠናቀቅ ምክንያት በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱ የቫቲካን ርዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አመደዮ ሎሞናኮ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

ይኽ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር የታቀበበት ቅዱስ ሥፍራ እ.ኤ.አ. በ 1808 ዓ.ም. አጋጥሞት በነበረው የእሳት ቃጠሎ አደጋ ምክንያት ለመጀመሪያ ጊዜ መታደሱና ቀጥሎም በ 1927 ዓ.ም. በዚያ ቅዱስ መቃብር ቅዱስ ሥፍራ የሚገኝበት ክልል አጋጥሞ በነበረው ርእሰ መሬትና እንዲሁም በአካባቢው ባለው እርጥበት እዘል ያየር ጠባይ ብሎም በቅዱስ ሥፍራው በሚበራው ሻማ በሚለቀው ጭስ የቤተ መቅድሱ ግንብ መፈረካከስና በጥቁር ጭስ መበከል እንዳስከተለበት ሆኖ ከዚህ ሁሉ ከደረሰበት ጉዳት ለማላቀቅ ይኸው ለአንድ ዓመት ሲካሄድ የቆየው ሕድሳት ተጠናቆ እ.ኤ.አ. መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም. መከፈቱ የገለጡት ልኡክ ጋዜጠኛ ሎሞናኮ አያይዘው፥  ቤተ መቅደሱ ዳግም ለመክፈት የተፈጸመው ስነ ሥርዓት የተለያዩ የቤተ መቅደሱ አቃቢያ ሦስቱ አቢያተ ክርስቲያን በጋራ ያቀረቡት ሲሆን ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንን ወክለው በስነ ሥርዓቱ የምስራቅ ሥርዓት ተከታይ አቢያተ ክርስቲያን ጉዳይ ለሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ለዮናርዶ ሳንድሪ ልኡክ በመሆን የተገኙት የኢየሳሌም ሐዋርያዊ መስተናብር ብፁዕ አቡነ ጁዘፐ ላዛሮቶ መሆናቸውና ብፁዕነታቸው ብፁዕ ካርዲናል ሳንድሪ ያስተላለፉት መልእክት በተካሄደው መንፈሳዊ ስነ ሥርዓት ማንበባቸውንም ገልጠዋ።

ብፁዕ ካርዲናል ሳንድሮ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያስተላለፉትና በኢየሩሳሊም ሐዋርያዊ መስተናብር ብፁዕ አቡነ ላዛሮቶ አማካኝነት የተነበበም ሲሆን። የዚያ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ መቃብር ሥፍራ የሚገኝበት ቤተ መቅደስ አቃብያን ለሆኑት ለሁሉም አቢያተ ክርስቲያን በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ስም ምስጋና ማቅረባቸውንና ቤተ መቅደሱን ለእምነት ምስክርነት በሚበቃ ፍቅር የውይይት መንፈስ ለሚያጎላ የሚያቀርቡት ቤተ መቅደሱን የማቀብ አገልግሎት ለማኅበረ ክርስቲያን ትልቅ ድጋፍና ለገዛ እራሱም ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መሆኑ በማብራራት ለዳግመ ሕዳሴ ድጋፍ ላቀረቡት ሁሉም ምስጋና ማቅረባቸው ሎ ሞናኰ ሲገልጡ፥ ሁሉም በዚያ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተቀበረበት ቅዱስ መቃብር ከተለያዩ የዓለማችን ክልል የሚነግዱት ምእመናን በእምነት የሚጸኑበትና ልብን የሚያበራ ስቃይ መከራንም ሁሉ ባሸናፊነት መወጣት ሞትን አሸንፎ በተነሳው ኢየሱስ ክርስቶስ ታምነው ባሸናፊነት የሚወጡ መሆናቸው የሚመሰክሩበት ቅዱስ ሥፍራ ነው እንዳሉ አስታውቋል።

በቅድስት መሬት የቅድስት መንበር ንብረት አቃቤ አባ ፍራንቸስኮ ፓቶንም በበኵላቸው ያንን ቅዱስ የመቃብር ሥፍራ የሚያስተዳድሩ ሦስቱ አቢያተ ክርስቲያን ለህዳሴው መረጋገጥ የሰጡት አስተዋጽኦ በአቢያተ ክርስቲያን መካከል ያለው ትብብር የሚመሰክርና ባንድ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚኖረው እምነት ማእከልነት የሚያረጋግጥ ነው ብለው መቀራረብ መተማመን የሚከወንበት የተቀደሰ ስፍራ ነው እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሎሞናኰ አያይዘው፥ የግሪክ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ተዎፍሎስ ሦስተኛ በበኩላቸውም ቅዱስ መቃብር የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን የሚያገናኛቸው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላቸው አንዳዊ እምነት የሚመሰከርበት ሥፍራ ነው ስለዚህ ይኽ የጋራው እምነት በተስፋ ሊደረስ ለሚፈለገው ውህደት ተጨባጭ ትእምርት ነው እንዳሉ ያመለክታሉ።

የአርመን ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኑርሃን ማኑጊያን በበኩላቸውም ይኽ ቅዱስ ስፍራ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሆነውን ፍቅርን ያማከለ አዲስ ትእዛዝ እንዲኖር የሚያሳስብ ነው የአርመን የግሪክ ስርዓት የምትከተለው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ውጭ ሌሎች በቅድስት መሬት የሚገኙት አምስት አቢያተ ክርስቲያን ጭምር በዚህ በቅዱስ ሥፍራ ቦታ እንዲሰጣቸው የሚል ጥሪ በማቅረብ አስከትለውም የመላ አርመን ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ጋረጊን በበዓሉ ምክንያት ባስተላለፉት መልእክት፥ ቅዱሱን ሥፍራ ለማሳደስ ሁሉም አቢያተ ክርስቲያን ያሳዩት ትብብር በፍቅር ላይ የጸናው ያ እውን እንዲሆን የሚታሰበው የአቢያተ ክርስቲያን ውህደት ከወዲሁ የሚመሰክር ነው በማለት ያሰመሩበትን ሃሳብ ጠቅሰው ውህደት ለማረጋገጥ እንትጋ እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሎሞናኰ አስታውቋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.